ዘ-ሐበሻ, Author at ዘ-ሐበሻ: Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ዘ-ሐበሻ

ኑዛዜው ጥያቄ ነው – ምትኩ አዲሱ

ፕሮፌሰር መስፍን “ኑዛዜ” በተሰኘ ግጥም ያልተጠበቀ ጥያቄ ትተውልን አልፈዋል። ኑዛዜአቸውን ይፋ ያደረጉት ሰኔ 2005 ዓ.ም. በ “የሚወለዱበት … መሬት” ጽሑፋቸው ነው። “በራሴ በኩል አውጥቼ አውርጄ ውሳኔ ላይ ከደረስሁ ቆይቻለሁ፤ መቀበር አልፈልግም … ለህልፈት ስበቃ የሬሳን ፈቃድ የሚፈጽም ከተገኘ … አቃጥሉልኝ ሬሣዬን ..” ብለዋል። ኑዛዜአቸው የምር ነው ወይስ የምሬት? ሬሣ ማቃጠል ምን ማለት ነው? ጠያቂውንና ጥያቄውን ቀጥለን እንመለከታለን። –—–ሙሉውን በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ —–   —  

አዲዬስ ኢኮኖሚክስ! በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የነፍስ ወከፍ ገቢ አንድ ሽህ ዶላር (37 ሽህ ብር ) በዓመት! ሚሊዮን ዘአማኑኤል

አዲዬስ ኢኮኖሚክስ! የዶክተር አብይ አህመድ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ  ኢትዮጵያን ሊበታትናት የደረሰውን ጥልቅ የብሔር ስንጥቆች ክፍፍል ብሎም የኃይማኖትና ዘር ጭፍጨፋ (ጆኖሳይድ) ስጋት ውስጥ

“ሁላችንም ሰው ነን “ ።ብለን ካላመንን ሠላምን አናገኛትም –  መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

የህሊናቸውን እውነት የልቦናቸውን ኃቅ  የካዱ። ሰው በየምእተ ዓመቱ ያደረገውን የውህደት ጉዞ እና “መካለስ” ከታሪክ እየተረዱ ፣ ሐሰተኛ  የሆነ የፖለቲካ ጥቅም የሚያሥገኝ ትርክት በመፍጠር የሚያወናብዱ። በሰው የኖሩ  መሥተጋብር እና ራስን በህይወት የማቆየት ትግል ወቅትም፣እሥከ ሞት የሚያደርሱ ግጭቶች ፣ጦርነቶች፣ ፍልሰቶች እንደነበሩ እየተረዱ፣ ለዘላቂ ምቾታቸው በማድላት ፣ለሆዳቸው ሲሉ ኃቅን የሚከዱ እና ሐሰተኛ ትርክትን በየቀኑ በማምረት እና ህዝብን በክፉ ወሬ በማሥጨነቅ “እኛ ከሌለን ባዶ!” የሚሉ የዳቢሎስን ካባ የለበሱ ፖለቲከኞች በዚች ሀገር በዝተዋል። እናም እነዚህ የዳቢሎሥ ካባ ለባሾች፣ኃቅን በመናገር እና ገንቢ ሂስ ከመሰንዘር እና ሰዎችን ወደቀናው ጎዳና ከማምጣት ይልቅ ፣ በ27 ዓመት ውሥጥ ተዘርቶ ያደገው የጎሣ፣የቋንቋ እና የልዩነት ፖለቲካ ቀጣይነት እንዲኖረው አውቀውም ሆነ ሰያውቁ የፕሮፖጋንዳ

ተጨማሪ

እሳት አቃጠለኝ! – በላይነህ አባተ

ጠላቴ ሌት ተቀን ሴራ ሲያሴርብኝ፣ በጨለማው ዘመን ብርሃን ከጅሎኝ፣ አጠንክሬ አካሌን ጨምቄ አይምሮዬን፣ በአስታቡልቡል ዘዴ እሳትን ፈጠርኩኝ፡፡ የፈጠርኩት እሳት እኔን እያሞቀኝ፣ ጨለማን ገሽልጦ ሌባውን ሲያሳየኝ፣ ድል ስላበሰለ ለዓመታት ደስ አለኝ፡፡ የድሉን እንጀራ ተምጣድ ሳልስበው፣ እባብ አፍ አውጥቶ ኢሳት ሲሳይ ሲለው፣ እንደ ሄዋን ስቶ ወዲያው አሳረረው፡፡ እንጨት ለቃቅሜ የቀለብኩት እሳት፣ ዕጸ-በለስ ጎርሶ እባብ የጠራው ለት፣ እሳቱ ሲሳይ ነው ይማሰል ያለ ወቅት፣ በነበልባል ምላስ ገረፈኝ በክህደት፡፡ በለስ የቀመሰ ትዕዛዝን አፍርሶ፣ እባብን የላሰ ሰማእት አምላክ ክዶ! መወርወሩ አይቀርም በጥንተ ሐብሶ! ድሮም እኔ አማረ እጄ አመድ አፋሽ ነው፣ የፈጠርኩት እሳት እያቃጠለኝ ነው! በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) የካቲት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

ተጨማሪ

‹የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የኃይማኖትና የዘር ጭፍጨፋ በማውገዝ ለተመድ ክስ አቀረቡ!!!›

ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም October 18, 2020 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መጠቃት የእስልምና፣ ፕሮቴስታንትና ካቶሊኮች እምነት ተከታዬች ጥቃት ነው! የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር  ሰርጌይ ላሮቭና የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብፁዕ አብነ ማትያስ በዓለማችን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ተከታዬች ብዛት ሩስያ በመቶ አንድ ሚሊየን አንደኛ ስትሆን ኢትዮጵያ አርባ ሦስት ሚሊዮን ተከታዬች ሁለተኛ ናት፡፡ የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን አሰቃቂ የኃይማኖትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም፣ ኤስኤኤ ቴሌቪዝን ስፊ ስርጭት በመስጠት ለሩስያ ህዝብ መረጃውን አጋርተዋል፡፡ ለፓን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሶሳይቲ ዳሬክተር ለጆርጅ ኤሌክስናደር ሪፖርት ያደረጉት ኢትዮጵያኖች ዲያቆን ሠለሞን ክብሪያና አቶ ምንተስኖት ደስታ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ተደጋጋሚ የተቀናጀ ጥቃት መፈጸሙን በማስረጃ አስደግፈው አሳይተዋል፡፡ የሩስያ ኦርቶዶክስ

ተጨማሪ

የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ የፊታችን ጥቅምት 9 እንደሚጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ

 በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም ለማስወገድ የ1ወር የንቅናቄ ዘመቻ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ የተፋሰሱ ልማት ከፍተኛ ምክር ቤት 8ኛው ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ነው። በንቅናቄ ዘመቻው ሁሉም ክልሎች፣ የፌዴራል ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ተሳታፊ ይሆናል ተብሏል። አረሙን የማስወገድ ንቅናቄው ”ህዳሴ ግድብ ያለአባይ፤ አባይ ደግሞ ያለጣና ማሰብ አይቻልም” በሚል ማዕቀፍ የሚካሄድ መሆኑን ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት። ንቅናቄውን ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁም ነው የተገለፀው። አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2013 (ኢዜአ)

ተጨማሪ

“ተጨፈኑ እናሞኛችሁ ” የብልጠት የፖለቲካ ጨዋታ እንዲቆም ማድረግ አገርን ከጥፋት ፤ ህዝብን ከሞት እና ስደት መታደግ ነዉ – ማላጅ

በኢትዮጵያ  የመንግስት ስርዓት ፀረ ኅዝብ እና አንድነት ኃይሎችን በተለያዩ የሃይል እና ጉልበት ግብዓቶች በማገዝ የብዙሃን ዜጋ ደህንነት ፣ በአገር ሰርቶ ሀብት እና ንብረት የማፍራት ብሎም በአገሪቷ በየትኛዉም ክፍል የመኖር ሠባዊ እና ህጋዊ የዜግነት መብት በማሳጣት እንደሁለተኛ ዜጋ በባይተዋርነት እንዲኖር ሲደረግ የረጅም ዓመታት የአገራችን ህዝቦች  ያሳለፉት “የቀይ/ነጭ  ታሪክ  ”እና  በክፋት እና ጥፋት ይዘቱ የዘመናችን  ወደር የለሽ የማይፋቅ ታሪካዊ ክስተት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በተለይም በኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያ አንድነት ላይ ጠንከር ያለ እይታ እና ይሁንታ ባላቸዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ከየትኛዉም የአገሪቷ ክፍል ከሚገኘዉ ማህበረሰብ የትዉልድ ሀረግ ይመዘዝ ከዚህ በተቃራኒ የማርያም ጠላት እየተባሉ እኛን ያየህ ተቀጣ እንዲሉ ተወልደዉ ዕትብታቸዉ በተቀበረበት ፣ ባደጉበት ፣ ወልደዉ ስመዉ

ተጨማሪ

ይድረስ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አማካሪዎችና በአጠገባቸው ላላችሁ ሙህራኖች በሙሉ – ከታምራት ይገዙ

መንደርደሪያ እስራኤል ሁሉ ያነግሡት ዘንድ ወደ ሴኬም መጥተው ነበርና ሮባዓም ወደ ሴኬም ሄደ። እንዲህም ሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮራዓም ይህን በሰማ ጊዜ እርሱም ከንጉሡ ከሰሎሞን ፊት ኮብልሎ በግብጽ ተቀምጦ ነበርና በግብጽም ሳለ ልከው ጠርተውት ነበርና ኢዮርባዓምና የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ መጥተው ለሮባዓም አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቃልልልን እኛም እንገዛልሃለን ብለው ተናገሩት። እርሱም ሂዱ በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ አላቸው። ሕዝቡም ሄደ ንጉሡም ሮባዓም ለዚህ ሕዝብ እመለስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ። እነርሱም ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸው መልስህም በገርነት ብትነግራቸው በዘመኑ ሁሉ

ተጨማሪ

ውሻ ሆይ! ይቅር በለኝ! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) “ውሻ በበላበት ይጮኻል!” የውሻ ባህሪ መስሎኝ አንተን ውሻውን በሰም ለበስ የወርቅ ግጥምና በንጥጥር ጦማር ሳነሳ ስጥልህ ኖሪያለሁ፡፡ ለሆዱና ለጥቅሙ ተንከባክቦ አሳዳጊውን ሕዝብና አገሩን የሚክድ ባለሁለት እጅ ፍጡር እንደ አሸን መፍላቱን ባለመገንዘብ ብዕሬን በአንተ እጅ ሳይኖረህ በትጉህ ሥራህ በምትታወቀው ሳነሳ ኖሬአለሁ፡፡ ውሻ ሆይ! በጦቢያ እርስ በርሳቸው የተገለባበጡ አራት ገዥዎችን በጌታነት እያቀያየሩ በጉርሻ ሎሌ የሆኑ ህሊና ቢሶች ፕሬዘዳንትና ሚኒሲቴር ሲባሉ እያየሁ “ውሻ በበላበት ይጮኻል!” እያልኩ እንዴት ልናገር እችላለሁ? ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል በአንገታቸው አንጠልጥለውና መንኩሰ ሞተ የምትልዋን ቆብ በራሳቸው ደፍተው በቤተክርስትያኗ አስራት ማጅራታቸውን ያሳባጡ ጳጳሳት በቤተክርስትያኗና በምዕመናኗ ላይ ለዘመቱ አሪዎስ ገዥዎች እጅ ሲነሱ እያየሁ “ውሻ በበላበት ይጮኻል!” እያልኩ ያንተን ስም

ተጨማሪ
/

የሕግ የበላይነትና የፍትህ ጉዳዮችን ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድርጎ መውሰድን የምንፀየፈው ነገር ነው – ናትናኤል ፈለቀ – የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

የዛሬ የዜጎች መድረክ ‹‹የቆይታ›› አምድ እንግዳችን የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናትናኤል ፈለቀ ናቸው፡፡ ናትናኤል ፈለቀ ተወልደው ያደጉት በአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዲሁም የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ ዞን ዘጠኝ ተብሎ ይጠራ በነበረው የአራማጆችና የጦማሪያ ቡድን ውስጥ አባል ነበሩ፡፡ በኮንስትራክሽን ቢዝነስ ባንክና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ዘለግ ላሉ ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በአሁኑ ሰአት በሙሉ ጊዜያቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው እያገለገሉ ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ፣ ኢዜማ ሊያደርገው አስቦት በነበረው ውይይት መደናቀፍ እንዲሁም ፓርቲያቸው ላይ ስለሚነሱ ትችቶች በሚመለከት የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተንላቸዋል፡፡ ቆይታችንን እንድታነቡት እንጋብዛለን፡፡ መልካም ንባብ! – ጥያቄ፡ አዲስ አበባ የ ኢትዮጵያ

ተጨማሪ

“ኢሳይያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያ የሰጣት የመቶ ዓመት የቤት ሥራ” ሲሳይ አጌና

” . . . ሻዕቢያ  ይበልጥ ያበሳጨን የብሄር ብሄረሰብ መብት እስከመገንጠል የሚለውን አንኳር አቋማችንን አለመቀበሉ ነበር”  ገብሩ አሥራት  ገጽ 116 “. . .ሻዕቢያ እና ምዕራባውያን መቼም ቢሆን የኦነግን የመገንጠል  አጀንዳ ሲደግፉ አይቼ አላውቅም” ዶ/ር ነጋሶ ገጸ 152 . . .  More importantly, the very systems of government established in Ethiopia and Eritrea after the fall of the Derg were significantly different and not much appreciated in each other’s capital.  Isaias especially thought Meles’ concept of ethnic federalism was misguided. . .   David Shinn የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ “ለኢትዮጵያ የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ሰጥታናታል” ብለዋል  የሚለውን ከሩብ ክፍለዘመን በፊት ጀምሮ  አብዝተን

ተጨማሪ

የአየር ኃይል ጉብኝት በኮለኔሉ ከአገር ሚስጥር አንፃር ሲፈተሽ

የአየር ኃይል ጉብኝት በኮለኔሉ ከአገር ሚስጥር አንፃር ሲፈተሽ

ተጨማሪ

አማራን ለጥቃት ከዳረጉ መሠረታዊ ችግሮች ጥቂቶቹ – ይነጋል በላቸው

ይህችን አጭር ማስታወሻ ካነበቡ በኋላ በምጠቁመው የድረ ገጽ አድራሻ ገብተው ዘመድኩን በቀለ የጻፈውን እጅግ ጠቃሚ መረጃ በአትኩሮት እንዲመለከቱ በትኅትና እጋብዛለሁ፡፡(https://welkait.com/?p=19074) ዓለምን ከጥንት ጀምሮ እየዘወራትና ወደሞቷ እያዳፋት ያለው የሤራ ፖለቲካና የመሠሪዎች ሸርና ተንኮል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በግሌ ይህን ዓይነቱን ሤረኝነት እጠላለሁ፡፡ በዚያም ምክንያት ወደ ፖለቲካው መድረክ መቅረብን አልወደውም፡፡ በዚህ መልክ የምንጨረጨረው ግን ያለ ሀገር መኖር የማይቻል በመሆኑና አንድ እንኳን አንባቢ ባገኝ የሚሰማኝን ለማስተላለፍ ነው – ቢያንስ እንደጣሊያኑ ሊቀ ጳጳስ ላለመሆን፤ ኢጣሊያ ሀገራችንን በወረረችበት ወቅት የነበሩት ሊቀ ጳጳስ በአንድ ታዛቢ እንደተተቹት “ዝም ማለት በሚገባቸው ወቅት ተናገሩ፤ መናገር በሚገባቸው ጊዜ ደግሞ ዝም አሉ”፡፡ ግፍና በደል በምድራችን ናኝቶ ሕዝብ እያለቀሰ ዝም ማለት ስህተት ነው፤

ተጨማሪ

እትዬ አበበችና ስዩም (የመሠረተ ትምህርት ትዝታዎች)  (ዘ-ጌርሣም)

በህይወት ላይ ብዙ ገጠመኞች አሉ፤አብዛኞቹ ሲረሱ አንዳንዶቹ ደግሞ ሁልጊዜ አብረው ይኖራሉ።ትዝታዎች ጥሩም መጥፎም ሲሆኑ ገጠመኝ የራስ ወይም የሌሎች መታሰቢያ ነው።በህፃንነት ዕድሜ ጭቃ አቡክቶ ውሃ ተራጭቶ ተኮራርፎና ተደባድቦ ተመልሶም ጓደኛ በመሆን በክፉ ወይም በበጎ የሚታሰቡ ሆነው በትምህርትና  በስፖርት ተወዳድሮ ማሸነፍና መሸነፍ ራሱን የቻለ ገጠመኝና ትዝታዎች ናቸው። የታሪክ ትረካወችም እንደ አቅራቢው ይለያዩ እንጅ የማይረሱና የህይወት ተጓዳኝ በመሆን ይቀጥላሉ።የታሪክ ትረካ ተሰጥዖ ይጠይቃል፥የራስን ወይም የሌሎችን ገፀ ባህሪያት ለመግለፅ ሥነ ጥበባዊ ስጦታ ይሻል፤ጥርስ የማያስከፍተውን ትረካ አሳምርው በማቅረብ ህይወት እየሰጡ የሚያዝናኑ ተራኪዎች የመኖራቸውን ያህል የደመቀ ህዝባዊ ትዕይንት የሚወጣውን ትረካ ባለቤቱን በማጣቱ አንገሸገሰኝ የሚሰኙ በርካታወች ናቸው።ሥነ ጥበብ መስታወት ነችና ባለቤት ትፈልጋለች። ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ የአንድ የትምህርት

ተጨማሪ

በሕገ መንግስቱ ላይ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጊዜ መገደብ አለበት” ተባለ

አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግስት አንቀጽ 70 ንዑስ አንቀጽ አራት የፕሬዚዳንት የሥራ ዘመን ስድስት ዓመት እንደሆነና አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዚዳንትነት ሊመረጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 72 በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ዘመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ነው የሚል ሲሆን የመመረጥ ገደብን አልጣለም። አሁን ላይ ሕገ መንግስትን በተመለከቱ ውይይቶችና መድረኮች ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመመረጥ ገደብ ሊቀመጥለት እንደሚገባ እየተገለጸ ነው፡፡ ለአብነትም ዛሬ ጥቅምት 05 ቀን 2013 ዓ.ም. በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዘጋጅነት ፣ በተካሄደ ውይይት ላይ ጉዳዩ ተነስቶ ነበር፡፡ በዚሁ ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን

ተጨማሪ

አቶ ልደቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር እንዲፈታቸው ፍርድ ቤት አዘዘ

አቶ ልደቱ አያሌው በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ጥቅምት 05 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው በተከሰሱበት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ሶስት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የምስክር ቃላቸው ተሰምቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም የሰማውን ምስክርነት መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ አቶ ልደቱ የተፈቀደላቸው የ100 ሺህ ብር ዋስትናን ተከትሎ ለምን እንዳልተፈቱ የጠየቀ ሲሆን የቢሾፍቱ ፖሊስ ሃላፊ ቀርቦ እንዲያብራራ የታዘዘውን ትዕዛዝም ፍርድ ቤቱ ተመልክቷል። ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ ዋስትናቸው ተከብሮ ከእስር እንዲለቀቁ በተደጋጋሚ ትዕዛዝ ቢሰጥም የቢሾፍቱ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አክብሮ እስካሁንም ሊፈታቸው አልቻለም፡፡ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረትም

ተጨማሪ

ወሎ ዩኒቨርስቲ በኪራይ አውሮፕላን የኬሚካል ርጭት እያደረገ ነው

የግብርና ሚኒስቴር ከኬንያ በኪራይ ባመጣው አውሮፕላን በወሎ አንበጣ በተከሰተባቸው የተለያዩ አካባቢዎች የጸረ-አንበጣ ኬሚካል ርጭት መደረጉን እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከኬንያ የመጡ ባለሙያዎችን በመደገፍ የማስተባበር ስራ መስራቱን ዩኒቨርሲቲው ገለጸ። ዩኒቨርስቲው በአንበጣ መንጋው ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ስነ ልቦናዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር አፋጣኝ ቀጥተኛ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ውሳኔ በቦርድ አመራሩ መወሰኑንም የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አባተ ጌታሁን (ዶ/ር) አስታውቀዋል። መንጋው ከተከሰተበት ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ከወልዲያ እና ሠመራ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር ሁኔታውን ስናጠናና ስንከታተል ነበር ያሉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አባተ ጌታሁን (ዶ/ር) ተማሪዎችን በማስተባበር ሰብል ሲሰበስቡ እንደነበረም ነው የገለጹት፡፡ የወሎ ዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አባተ ጌታሁን (ዶ/ር) አሁንም አንበጣውን ለመከላከል ከኬንያ በመጡ ባለሙያዎች በመታገዝ በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ተጨማሪ

የተመስገን መታሰር “እብሪተኝነት” ነው የምለው ለምንድነው? (ሙክታሮቪች)

ጋዜጠኛ ተመስገን በፍትህ መፅሄት ላይ ከውስጥ አዋቂ አገኘሁት የሚለው መረጃ “ወ/ሮ አዳነች አበቤ በአካውንታቸው ውስጥ 40 ሚሊየን መገኘቱን በመጥቀስ በፓርቲ ግምገማ ሲደረግባቸው እሳቸውም ማን ይህን ያህል ብር በአካውንታቸው እንዳስገባ እንደማያውቁ ሆኖም የሆነ የማያውቁት ግለሰብ ይህን ብር በአካውንታቸው ማስገባቱን አምነዋል” የሚል ነው። በመጀመሪያ ደረጃ መፅሄቱ ይህን መረጃ ሲያወጣ፣ እንዲህ አይነት መረጃ እንዲሁ በውስጠ አዋቂ በፓርቲ ግምገማ ተነሳባቸው በሚል ሳይሆን አካውንታቸው ውስጥ ይህን ያህል ብር መገኘቱን የሚያውቅ ሆኖም መረጃውን ማውጣቱ ቢታወቅ ስጋት የሚያድርበት ሰው ከሆነ እና ይህንም መረጃ ለእነፍትህ መፅሄት ያሳያቸው ቢሆን የበለጠ ታማኝነት ይኖረዋል። የውስጠ አዋቂውን አምነው ካወጡ ደግሞ የተሳሳተ መረጃ መሆኑን በሌላ ተቃራኒ መረጃ ከተሞገቱ ያወጡት መረጃው ስህተት መሆኑን አምነው

ተጨማሪ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ

የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ እና የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ምስጋን ዝናቤ ከቢሮአቸው በፖሊስ ተወስደው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መታሰራቸውን የተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጧል። ታሪኩ ደሳለኝ ለአሜርካ ድምፅ እንደገለፀው፤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የፖሊስ ደንብ ልብስየለበሱ እና ሲቪሎች ወደ መጽሔቱ ቢሮ ከደረሱ በኋላ ዋና አዘጋጁን አቶ ምስጋን ዝናቤንከያዙ በኋላ ወደ ተመስገን ደሳለኝ ስልክ እንዲደወል አድርገዋል። ተመስገንን እንደሚፈልጉት እና ወደ ቢሮ እንዲመጣ ከነገሩት በኋላ፤ ቢሮ ሲደርስሁለቱንም ይዘዋቸው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደወሰዷቸው ተናግሯል። ማምሻውን አዲስ አበባ ፖሊስ ሄደው መታሰራቸውን ከሩቁ እንዳረጋገጠም ተናግሯል።በጉዳዩ ላይ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።በነገው ዕለት ዘርዝር ያለ መረጃ ይዘን

ተጨማሪ

ዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቁጥራቸው የበዙ ፖሊሶች ከቢሮ ወሰዱት

ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ቁጥራቸው የበዙ ፖሊሶ ፍትሕ መጽሔት ወደሚገኝበት ቢሮ ከደረሱ በኋላ ተመስገን ደሳለኝን የት እንዳለ ጠየቁ። በወቅቱ እርሱ ቢሮ ውስጥ ስላልነበረ አዘጋጁ ወደ ተመስገን ደወለ። ከፖሊሶቹ ውስጥ አንዱ የአዘጋጁን ስልክ ተቀብሎ፤ እንደሚፈልጉት እና የት እንደሚገኝ ጠየቀው። – ተመስገንም ይዘው የመጡት መጥሪያ ወይም ክስ ካለ ቢሮ አስቀምጠው እንዲሄዱ ነገራቸው። የሚያናግረው ፖሊስ ግን የሚፈልጉት እርሱን እንደሆነና ያለበትን እንዲነግራቸው ጠየቁት። እርሱም “ግድ የለም እኔን ከፈለጋችሁኝ ቢሮ እመጣለሁ” የሚል ምላሽን ሰጥቶ ወደ ቢሮው ተመለሰ። እንደደረሰም፤ ተዘጋጅተው እየጠበቁት ስለነበር ጭነው ወሰዱት። – ጥቅምት 4/2013 ዓ.ም Tariku Desalegn Miki

ተጨማሪ

ከወገብ በላይ ታቦት፣ ከወገብ በታች ጣዖት!!!›› ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

የፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ “ ሜሪሜድስ አፈታሪክ ከወገቧ  በላይ ቆንጆ ሴት ተክለ ሰውነት ያላት፣ ከወገቧ በታች ዓሳ ቅርፅ ዳሌና እግሮች ያላት በስነውኃ  ውስጥ የምትኖር የሰው ምናብ ፍጥረት ናት፣ አንስትና ተባዕት ፆታ አላቸው፡፡ Mermaid, masculine merman, a fabled marine creature with the head and upper body of a human being and the tail of a fish. Similar divine or semidivine beings appear in ancient mythologies (e.g., the Chaldean sea god Ea, or Oannes). በሃገረ-ኢትዮጵያ ኤርትራ ባህረ ነጋሽ፣በቀይ ባህር፣ ምፅዋ ዳህላክ ደሴቶች ‹‹እንደ ሰው በምድር፣ እንደ ዓሳ በባህር›› የሚኖሩ ፍጡራኖች መኃል ጥይት የማይመታቸው ኢሳያስ አፈወርቂ አንዱ ናቸው ይባላል፡፡ ኢሳያስ በብሉይና አዲስ ዘመን የሚመላለሱ ከወገባቸው በላይ ወንድና ከወገባ

ተጨማሪ

“ኦሮሞ ካልሆንክ አታድግም፤ አትሾምምም!” አምባቸው ደጀኔ

ይሄ ድቅድቅ ጨለማ እስኪነጋ ስንትና ስንት ጉድ ተቆልሎ በየቀኑ ዕይታችንን እንደሚያደበዝዝ ወይ እንደሚጋርድ አላውቅም፡፡ አንድ ወቅት አንድ ጸሐፊ ወዳጄ “ፂላ ካልሆንክ አትሠራም” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ ጽፎ በዚሁ በድረገጽ ማንበቤ ትዝ ይለኛል፡፡ እኔም ከርሱ ኮረጅኩ፡፡ ከቀሪ እንስሳት በእጅጉ እንደሚበልጥ የሚታመንበት የሰው ልጅ ሠልጥኖ የትና የት በደረሰበት በዚህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘመን የኛ የፕሪካምፕሪያን ዘመን (Precambrian Era) የአውስትራሎፒቴከስ (Australopithecus)  ዝርያ ሰው መሳይ ዝንጀሮዎች ምን እየሠሩ እንደሆነ ጥቂት ላውጋችሁ፡፡ የሰው ሰውነቱ የሚረጋገጠው በግብሩ እንጂ በቅርጹ እንዳልሆነ እነዚህ ከዝንጀሮም ያነሱ ፍጡራን እያስመሰከሩ ነው፡፡ የትምህርት ትርጉም “የአስተሳሰብና የአመለካከት እንዲሁም የባሕርይ ለውጥ ማስገኘት ነው” የሚለው ነባር እሳቤ በነሱ ቤት በፍጹም አይሠራም – ለዚህም እንደዋቢ ዋናውን የደናቁርት

ተጨማሪ
1 2 3 840