በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ ሰኔ 15 ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከሰጠው መግለጫ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ ሰኔ 15 ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከሰጠው መግለጫ

1 min read
15

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 70 ተጠርጣሪዎች መያዣ ወጥቶባቸው 31ዱ በቁጥጥር ስር ውለዋል

የ147 ሰዎችን ቃል መቀበል ተችሏል

የ22 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ ታግዷል

ወንጀሉን ከሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለመፈፀም ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል

ጥቃቱ በብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ መሪነት የተፈጸመ ነው

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ማጣራት ተደርጎ ከተጠርጣሪዎቹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣

በርካታ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ የውጭና የሃገር ውስጥ ገንዘብ፣ 5 ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በርካታ ቁሳቁሶች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል

በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ 4 ጠባቂዎችን ጨምሮ 8 አጃቢዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል

የፌዴራል ፖሊስ፣ መከላከያና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች የተቃጣውን ጥቃት ቀልብሰውታል

ድርጊቱ መንግሥትን በኃይል ለመቆጣጠር የታቀደ የመፈንቅለ መንግሥት ነበር

15 የሰው ሕይወት ሲያልፍ 20ዎቹ ቆስለዋል

ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በተንቀሳቀሱት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅት ተደርጓል።

 (ጌጡ ተመስገን)