በአፋን ኦሮሞ ከ39 ሺ በላይ ተማሪዎች በአዲስ አበባ እየተማሩ መሆኑን የከተማው ትምህርት ቢሮ ገለጸ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

በአፋን ኦሮሞ ከ39 ሺ በላይ ተማሪዎች በአዲስ አበባ እየተማሩ መሆኑን የከተማው ትምህርት ቢሮ ገለጸ

1 min read
3

በአዲስ አበባ ከ39 ሺ በላይ ተማሪዎች በአፋን ኦሮሞ እየተማሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ውስጥ ባሉት በተለያዩ ክ/ከተሞች 39 ሺህ 365 ተማሪዎች በአፋን ኦሮሞ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ትምህርት አስተባባሪ አቶ አብዩ በየነ እንደገለጹት፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት የአፋን ኦሮሞ ትምህርት በከተማው ውስጥ በተወሰኑ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ቆይቷል፡፡

ከበላፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ በከተማ መስተዳድሩ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በአፋን ኦሮሞ ትምህርት እንዲሰጥ በተደረገው ጥረት በአሁኑ ወቅት በ126 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከ39 ሺ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአፋን ኦሮሞ እየተከታተሉ እንደሆነ መገለጹን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

በወይንሸት ካሳ/ ( ኢፕድ)