አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ተጓዙ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ተጓዙ

1 min read
2

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለከነገ በስቲያ አሜሪካ በጠራችው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውይይት ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማምሻውን ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ተጉዘዋል።

አቶ ገዱ ወደ ዋሽንግተን የተጓዙት የአሜሪካ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ስቴቨን መንቺን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት እንዲያደርጉ ባደረጉት ግብዣ መሰረት ነው።

በዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄደው ውይይት ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያላትን አቋም እንደምታስረዳ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

EBC