ጠሚ አብይ አህመድ አምቦ አበበች ደራራ ሆቴል ውስጥ ያደርገው የነበረውን ስብሰባ በጃዋር መሀመድ ደጋፊዎች ከሆቴሉ ውጭ የተቃውሞ ሰልፍ ስላደረጉ ስብሰባውን አቋርጦ በኤሊኮፍተር ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ እየተባለ ነው – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ጠሚ አብይ አህመድ አምቦ አበበች ደራራ ሆቴል ውስጥ ያደርገው የነበረውን ስብሰባ በጃዋር መሀመድ ደጋፊዎች ከሆቴሉ ውጭ የተቃውሞ ሰልፍ ስላደረጉ ስብሰባውን አቋርጦ በኤሊኮፍተር ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ እየተባለ ነው

1 min read
8

በጠቢቡ አማራ

ጠሚ አብይ አህመድ አምቦ አበበች ደራራ ሆቴል ውስጥ ያደርገው የነበረውን ስብሰባ በጃዋር መሀመድ ደጋፊዎች ከሆቴሉ ውጭ የተቃውሞ ሰልፍ ስላደረጉ ስብሰባውን አቋርጦ በኤሊኮፍተር ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ እየተባለ ነው። ተመልሷል።

ይህ የማን ሴራ መሰላችሁ የራሱ የአብይና የጃዋር (የኦነግ፣ ኦህዴድ፣ OMN) መሃመድ የጋራ እቅድ ነው። እኔ ብዙ የኦነግ እና የኦህዴድ ደጋፊዎች ጋር በአካል እከራከራለሁ። በሁሉም አቅጣጫ ወጥራችሁ ስትይዟቸው #የአብይን_መንግስት_ተቀባይነት ለማስረገጥ “…አብይ ፅንፈኛ ኦነግን ስለሚፈራ፣ ፅንፈኛ አሀይኸን ስለሚፈራ ወይም በዘዴ ለመያዝ፣ አብዛኛው የጃዋር ደጋፊ ስለሆነ፣ ከኦህዴድ አብዛኞቹን ጨምሮ ኦነግና ቄሮ የመገንጠል ስለሆነ ጥያቄያቸው እነሱን በመላ ለመያዝ እንጂ እሱ እኮ ንፁህ ነው፤ ዓላማውም የኢትዮጵያ አንድነት ነው…” እያሉ ይከራከሩለታል። ይኸን የሚያደርጉት በአማራውና በሌላው ብሔርና ህዝብ እየገጠመው ያለውን ተቃውሞ ለማለዘብ ነው። የሚሰሩትን ሰርተው እስኪጨርሱ አምነን እንድንቀበለውና እንድንደግፈው ነው።

ሀቁ ግን ቄሮንም ሆነ ለመጥፋት ተቃርቦ የነበረውን ኦነግን ከመሬት አንስቶ (ያለፈውን ሳናነሳ በድፍኑ/በሽፍንፍኑ ይቅርታ እናድርግ የሚል ውሃ የማያነሳ ማብራሪያ በመስጠት) ከፍተኛ የበጀትና የአመራር ድጋፍ በማድረግ ከዚህ ደረጃ ያደረሳቸው፣ አቅማቸውንና ቁጥራቸውን ያበዛው ማን ሆነና!!?!! ኦነግ ከኤርትራ በርሃ ወደ አገር ሲገባ በቁጥር ከ1,000 አይበልጥም ነበር፤ በመሣሪያ እዚህ ግባ የማይባል ነበር። ኦነግ አገር ውስጥ በገባበት ቅፅበት ጀምሮ ወታደራዊ ካምፖችን መስርቶ ወታደር ሲያሰለጥን፣ መሣሪያ ሲያስታጥቅ፣ ትጥቅ አልፈታም ሲል አብይ እንዳላየ ዝም አላቸው። በቀላሉ መምታት ወይም ማስቆም እየተቻለ 23 ባንኮችን ዘርፎ ቢሊየነር ሆነ፣ አማራንና ጋሞን በየቦታው ገደለ፤ አፈናቀለ።

ሌላውን ተውትና የአብይ መንግስት ከአገር መከላከያው ጋር እንዲሁም የኦሮሚያ መንግስት ከኦሮሚያ ልዩ ሀይል ጋር የኦነግን ምልምል አሰለጠኑለት። ኦነግ ከመንግስት ጋር ስልጣን እንዲጋራ ተደረገ። ኦነግ ትጥቅ አልፈታም አለ ተብሎ አብይ ሲጠየቅ “…ይኸ የምላስ ወለምታ ነው እንጂ ኦነግ ትጥቅ አልፈታም አይልም…” ብሎ ተከራከረ። እሱ ይህን ከማለቱ በፊትም ካለም በኋላ የኦነግ ጦር መሪው ዳውድ ኢብሳ ደጋግሞ “…ትጥቅ አንፈታም። ማን ነው ትጥቅ ፈቺ? ማን ነውስ ትጥቅ አስፈቺ? እንደውም መንግስት ራሱ ትጥቅ ይፍታ…” ብሎ ተመፃደቀ። አሁን ኦነግ እስከ አፍንጫው ድረስ #ዘመናዊና_ከባድ_መሣሪያ_ታጥቋል። ይኸኸ ነገር ለአብይ ፖለቲካ ስለማይመች (ሌላም ተጨማሪ ምክንያት አለ) የኦነግ ጦርን በጫካ የሚመራው በከተማ ካለው ከእነ ዳውድ ኢብሳ (ዋና መሪዎቹ) ጋር ‘ተለያይተና እነሱ አያዙንም፣ የእዝ ሰንሰለቱ ተቋርጧል’ የሚል መግለጫ እንዲሰጥ አደረጉት። እኛም ያለፈውን ስለማናስታውስ እንዲሁም መጪውን ቀድመን ስለማንረዳ በየዕለቱ የሚወረውሩልንን አጀንዳ እያራገብን አለን።

በጣም ከመደንዘዛችን የተነሳ “…አብይ ሆይ ጃዋር ለአንተም አይመለስም ነግረንህ ነበር…” የሚል አክቲቪስት ሁነናል -በተቀነባበረ ሴራ የተጋጩ እያስመሰሉ እንደሚሰሩ ማገናዘብ ወይም ማስታወስ ተስኖን። ለአብይ መንግስት ጃዋር አጥፊው ነው? አወ አጥፊው ነው። የሚያጠፋው ግን አብይን በመቃወም አይደለም – የአብይ መንግስት ጃዋርና ኦነግን የሚለግሱት ምክርና ስትራቴጂ ለጊዜው እንጂ በረጂም ጊዜ የማይሰራ ወይም የማያጠምድ ስለሆነ ነው።

አማራን፣ ሶማሌን፣ አፋርንና ጋሞን ለመግደል የማይታክተው የኦሮሚያ ልዩ ሀይልና መከላከያ ስብሰባው እስኪያልቅ ተቃውሞውን መቆጣጠር አቅቶት ወይም ተቃውሞ እያደረጉ ያሉትን ከፍታ ቦታ ላይ ካለው አበበች ደራራ ሆቴል 500 ሜትር (ወደ ጊንጭ አቅጣጫ) ፈቀቅ ማድረግ አቅቶት (አቅቷቸው) ነው #ጠሚ_አብይ_ስብሰባ_ለማቋረጥ_የተገደደው?

ስለዚህ ‘ጃዋር ጠላትህ ነው’ አይነት የጅል ፖለቲካ አትስሩ።