በገጣሚ ህሊና ደሳለኝ ላይ የተጀመረው ዘመቻና  የ ኤል ቲቪ ነውረኛ ዉንጀላ - ከአበበ ጉልማ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

በገጣሚ ህሊና ደሳለኝ ላይ የተጀመረው ዘመቻና  የ ኤል ቲቪ ነውረኛ ዉንጀላ – ከአበበ ጉልማ

1 min read
3

በኢትዮጵያ  የሚተላለፈው LTV World የተሰኘው ቴለቪዥን ሰሞኑን የኦሮሞ መብት ተከራካሪ ነኝ ከሚሉት አቶ ግርማ ጉተማ ጋር ባደረገው ቃለመጥይቅ በገጣሚ ህሊና ደሳለኝ ላይ የተደረገ ስም ማጥፋትና በአደባባይ የተደረገ ዉንጀላ ነበር። LTV World በዮቲዩብ Sep 18, 2019  ባሰራጨው ቃለመጠይቁ (7፡18 አካባቢ ያለውን ያዳምጡ) ወጣቷን ገጣሚ ያላለችዉን ብላለች በማለትና፣ በኢትዮጵያ ቀርቶ በሌላዉም አለም ነዉር የሆነን የብልግና ቃል በአደባባይ በመጠቀም፣ ስሟን ለማጥፋትና፣ የኦሮሞን ህዝብ በሌላው ላይ ለማነሳሳት ተጠቅሞበታል፡፡ ጋዜጠኛዋም ይሁን LTV ምንም ይቅርታ አልጠየቁም፡፡

ጠያቂዋና LTV የኢትዮጵያን ህዝብና ገጣሚ ህሊና ደሳለኝን በይፋ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል።   በአገራችን ለሚደርሰው ጥፋት OMN, LTV እንዲሁም እየቀረቡ ህዝብን ከህዝብ ለማጫረስ መርዘኛና ዘረኛ መልዕክት የሚያስተላልፉ ግለሰቦች፣ እንደ ጃዋር መሃመድ፣ በቀለ ገርባ እና ግርማ ጉተማ፣ ጸጋየ አራርሳ፣ ዶ/ር እዝቄል ጋቢሳ ያሉ በህግ ሊጠየቁ ይገባል።  ይህ ዘመቻ ኢትዮጵያን በማበጣበጥና እርስ በርስ በማዋጋት፣ ኢትዮጵያን ለዉጭ ጠላት አሳልፎ ለመስጠት ነው፡፡

መንግስት የዉጭ አገር ፓስፖርት ይዘዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እየመሩ ያሉትን ግለሰቦችና ድርጅቶች በትዕግስት መመልከቱ ወይም በአደባባይ በይፋ አለማዉገዙ የሚዘራዉን ከፋፍይ ትርክት የሚደግፍ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡   እነዚህን ግለሰቦችና ድርጅቶች ወደፍርድ እንዲቀርቡ ህዝቡ ሊጠይቅ ይገባል፡፡