“አማራን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው” በሚል ሰብሳቢ መርህ አለም አቀፍ የአማረ ህብረት አቀፍ ጉባኤ እንዲሳተፋ ተጠርተዋል – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

“አማራን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው” በሚል ሰብሳቢ መርህ አለም አቀፍ የአማረ ህብረት አቀፍ ጉባኤ እንዲሳተፋ ተጠርተዋል

1 min read
1

ቀን–መስከረም 1ቀን 2019 ዓ.ም
ቁጥር—ዓአህ/08/001
ለተወደዱ—–ባሉበት
ጉዳዩ፤ አስቸኳይ ጉባኤ
በአማራው ሕዝብ ላይ የሚካሄደው ግፍና በደል እየተባባሰ ሂዷል። የዚህን ታላቅ ሕዝብ ህልውና አስጠብቆ ሕዝቡን ከእርስ በእርስ እልቂት እና እናት አገራችንን ከመበታተን ለመታደግ፤ “ አማራን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው” በሚል ሰብሳቢ መርህ አለም አቀፍ የአማረ ህብረት ባዘጋጀው ሁሉን አቀፍ ጉባኤ እንዲሳተፋ ይህን የአገር አድን ጥሪ ለእርሰዎም ልከናል።
የሁለት ቀኑ ጉባኤ ዋና ዓላማ አዲስ ድርጅት ለመመስረት አይደለም። የአማራውን ሕዝብ በአንድ ጃንጥላ ስር በማስተባበር በኢኮኖሚያዊ፤ ማህበረሰባዊ፤ ፓለቲካዊ፤ ዲፕሎማሲያዊና በተዛመዱ ጉዳዮች ላይ ተመካክሮና ተናቦ፤ ውጤት የሚያስገኙ ተግባሮችን በተቀናጀና ስልት ባለው መልክ ስኬታማ ለማድረግ ነው። “ድር. ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ ተባብሮ ከመስራት ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።
ልዩ ልዩ የአማራ ማህበረሰባዊ፤ ፖለቲካዊ፤ መንፈሳዊና ሌሎች ድርጅቶች፤ በአዲስ አብሮና ተባብሮ የመስራት መንፈስ፤ አደረጃጀትና መመካከር ያሉትን ድርጅቶች ማጠናከር፤ አብረውና ተደጋግፈው እንዲሰሩ አንድ ወጥ የሆነ ማእከላዊነት እንዲመሰረትና በአማራው ላይ እየተካሄደ ያለውን ግፍና በደል፤ የፈጠራና የሃስት ትርክት ከሚጠቀሙ ኃይሎች የሚደርስበትን ድርብና ድርብርብ ጭቆና በአጭር ጊዜ ውስጥ መቋቋም ወሳኝ ነው። ለዚህም፤ አግባብ ባለው የአቅጣጫና የተግባር ፍኖተ ካርታ ላይ ስምምነት መደረግ አለበት።
በአማራው ላይ የተከሰተውን ችግር ለመወጣት የምንችለው በጋራ ስንሰራ ብቻ ነው። ለዚህም፤ አንድ አለም አቀፍ አስተባባሪ አካል መመስረቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ ስላለው እርሰዎም ሆኑ ድርጅቶዎ በዚህ ጉባኤ ላይ በመገኘት ለአማራው ወገናችን ተቆርቋሪነተወን እንዲሳዩና ወገኖቻችን የማዳን ታሪካዊ ግዴታዎትን እንዲወጡ በማክበር ጠርተነወታል።
ከስላምታ ጋር
ዶ/ር አምባቸው ወረታ
የአለም ዓቀፍ አማራ ህብረት እስተባባሪ ሊቀመንበር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
የስብስባ ቀን– መስከረም 14 እና 15
ቦታው- 2601 Evarts St. N.E Washington DC, Zip code 20018