የአማርኛ ትምህርት በጀርመኑ ሀምቡርግ ዩንቨርሲቲ (University of Hamburg) መቶ ዓመት አስቆጠረ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

የአማርኛ ትምህርት በጀርመኑ ሀምቡርግ ዩንቨርሲቲ (University of Hamburg) መቶ ዓመት አስቆጠረ

1 min read

በጀርመን ሀገር ከሚገኙ ዝነኛ ዩንቨርስቲዎች አንዱ የሆነዉ የሀምቡርግ ዩንቨርሲቲ የተመሰረተበትን መቶኛ ዓመት በማክበር ላይ ይገኛል። በዩንቨርሲቲዉ የአማርኛ ቋንቋ  ትምህርት ሲሰጥም መቶ ዓመቱን ይዟል።

“አማርኛ ቋንቋ በጀርመን ዩንቨርሲቲዎች በ1919 ዓ/ም መሰጠት ይጀምር እንጅ ቀደም ሲልም ቢሆን ኢትዮጵያ ለጀርመኖች ትልቅ የምርምርና ጥናት ሀገር ሆና ነው የቆየችዉ። ኢትዮጵያ የራሳቸዉ ፅህፈት፣ ታሪክ፣ ነፃ የመንግሥት አወቃቀር፣ ጥንታዊ ስልጣኔ ካላቸዉና ነፃነታቸዉን ጠብቀዉ ከቆዩ ጥቂት ሃገራት መካከል አንዷ በመሆኗ ጀርመናዉያኑ ምሁራን ከ17ኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነበር በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ማድረግ የጀመሩት።

የጀርመን ተመራማሪዎች በግዕዝ ቋንቋ የተጻፉ የብራና መጻሕፍት፣ ገድላት፣ ዜና መዋዕላትና የታሪክ መፃህፍት ላይ ሀተታና ትርጉም እንዲሁም ንፅፅራዊ ጥናት ያደርጉ የነበረ ሲሆን በአማርኛ ቋንቋም ሂዎብ ሉዶልፍ የተባለ ጀርመናዊ የአማርኛ ሰዋሰዉ ለመጀመሪያ ጌዜ ማሳተሙን ዶክተር ጌቴ ያስረዳሉ።

በሀምቡርግ ዩንቨርሲቲ የአንኮበሩ መምህር ወልደ ማርያም ደስታ ከጎርጎሮሳዊዉ 1919 እስከ 1925 ዓ/ም የአማርኛ ቋንቋን ሰዋሰዉ፣ ሥነ-ጽሑፍና ንግግርን ‘ኦጉስት ክሊንገን ሄቨን’ ከተባሉ ጀርመናዊ ፕሮፌሰር ጋር በመሆን ካስተማሩ ወዲህ በዩንቨርሲቲዉ ባለፉት መቶ ዓመታት በርካታ ምሁራን ቋንቋዉን አስተምረዋል።”

ምንጭ:-
የጀርመን ድምፅ ራዲዮ DW Amharic
ግንቦት 8፣ 2011 ዓ.ም (ለትውስታ)