የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

1 min read

የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ደብረ ታቦር ወይንም ቡሄ በየዓመቱ በዛሬዋ ቀን የሚከበር በዓል ነው።

በዓሉ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዓቢይ በዓላት አንዱ ሲሆን አከባበሩም በበርካታ ባህላዊ ቁሶችና የምግብ አይነቶች የሚታጀብ ነው።

ሙልሙል ዳቦ ወይም ህብስት እና ችቦም የዚህ በዓል ማድመቂያዎች መሆናቸውን አከስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል ዛሬ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎችም እየተከበረ ይገኛል፡፡