በአዲስ አበባ በድጋሚ በለገዳዲ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ መሆኑ ተገለጸ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

በአዲስ አበባ በድጋሚ በለገዳዲ የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ መሆኑ ተገለጸ

1 min read
2

ለገዳዲ 44 ማዞሪያ አከባቢ ነዋሪዎችን ከቤታቸው በማስወጣት መኖሪያ ቤቶችን እያፈረሱመሆኑን በቦታው የሚገኙ ሰዎች መግለጻቸውን ስዩም ተሾመ ዘግቧል።

የፀጥታ ሃይሎች በአከባቢው ተገኝተው መኖሪያ ቤቶቹን በማፍረሱ ሂደት ተባባሪ መሆናቸውን ለማወቅ መቻሉን የገለጸው ይሄ ዘገባ አምና በተመሳሳይ ወቅት ቤት መፍረሱን አስታውሷል።

” ዘወትር ክረምት በመጣ ቁጥር የነዋሪዎችን ቤት የማፍረስ ሰይጣናዊ ድርጊት መቼ እንደሚለቀን አላውቅም። የሚመለከታቸው አካላት ይህን ጉዳይ በአስቸኳይ ሊያስቆሙ ይገባል። በዚህ ሰዓት የነዋሪዎችን ቤት ማፍረስ እብደት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ሊባል አይችልም።” ሲል የአንዳፍታ ነጻ ውይይት አዘጋጁ ስዩም ተሾመ አስተያየየቱን አክሎ ቅሬታውን አስፍሯል።

አምና በተመሳሳይ ወቅት በለገጣፎ ለገዳዲ የበርካታ ነዋሪዎች ቤት የፈረሰ ሲሆን የቤት ማፍረሱ አንድ ብሄር ላይ ያነጣጠረ እርምጃ መሆኑን ወቀሳ ሲቀርብበት መቆየቱ አይዘነጋም።

ቤታቸው የፈረሰባቸው ለረጅም ጊዜ በቤተክርስቲያን ተጠልለው የቆዩ ሲሆን በተደጋጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ቅሬታ ቢያቀርቡም ምላሽ ማጣታቸው አይዘነጋም። ቤታቸው የፈረሰባቸው አስተባባሪዎች የነበሩ መታሰራቸው መዘገቡ ይታወሳል።

የአምናው የለገጣፎ የነዋሪዎች ቤት ሲፈርስ የሚያሳዩ ፎቶ ግራፎች ተያይዘዋል ሼር ያድርጉት

ሕብር ሬዲዮ