ዶክተር አቢይና ለውጡ የት አሉ? - ግርማ በላይ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ዶክተር አቢይና ለውጡ የት አሉ? – ግርማ በላይ

1 min read
1

ግርማ በላይ (gb5214@gmail.com)

ናስሩዲን የተባለ ግብጻዊ አለቃ ገ/ሃና ነበረ፡፡ ብዙ ቀልዶች እንዳሉት ይነገርለታል፤ አንዳንዶቹንም አንብበናል፡፡ አንዱን እዚህ ላስታውስና ወደ ቁም ነገሬ ልግባ፡፡ ናስሩዲን ሦስት ኪሎ ሥጋ ገዝቶ ወደ ቤቱ ይገባል፡፡ ሥጋውን ለሚስቱ ሰጥቶ ጓደኞቹ ጋር ሊዝናና ከቤቱ ወጣ ይላል፡፡ ሲመለስ ሥጋውን ካስቀመጠበት ያጣዋል፡፡ ሚስቱ ያንን ሥጋ  ለእራታቸው ሠርታው እንደሆነና እንዳልሆነ ይጠይቃታል፡፡ እርሷ ግን “ድመቷ በላችሁ” ትለዋለች፡፡ ናስሩዲን ያኔ ይናደድና ድመቷን አፈፍ አድርጎ ሚዛን ላይ ያስቀምጣታል፡፡ ሲመዝናት ልክ ሦስት ኪሎ ትሆናለች፡፡ ሚስቱ ላይ አፍጥጦ “ስሚ አንቺ ሴትዮ! ሥጋውን ድመቷ በላችው ብለሽኛል፡፡ ድመቷን ስመዝናት ግን ሦስት ኪሎ አናቱ ላይ ሆነች፡፡ ስለዚህ የመዘንኩት በድመቷ ሆድ ውስጥ የሚገኘውን ሥጋ ከሆነ ድመቷ የት አለች? የመዘንኩት ድመቷን ከሆነ ደግሞ ሥጋው የት አለ?” ብሎ ያፋጥጣታል፡፡ መልስ አልነበራትም፡፡ ለምን ቢባል ሥጋውን ሴትዮዋ ቅርጥፍ አድርጋ በልታው ነበረና፡፡

በሀገራችን እፍ እፍ የተባለለት ለውጥ መጣ ተባለ፡፡ ብዙዎቻችን በፍቅር ነሆለልንለት፡፡ “የማያዛልቅ ባል ቅንድብ ይስማል” እንዲሉ ሆኖ “ልዘላችሁ ወይንስ ልቀፋችሁ?” ይለን የነበረው የለውጡ ሞተር ዘዋሪ ኢሕአዲግ-ሠራሹ ዶክተር አቢይም በወረት ፍቅር ብዙዎቻችን የምንሆንለትን እስክናጣ ድረስ ገና በቅጡ ባልተለማመደበት የመሪነት ግርማ ሞገሥን በማሳመሪያ ንግግሩ አናወዘን፡፡ “በርሱ የመጣ ባይኔ መጣ” እስክንል በሞኝ ፍቅር ሆድ ይገትር ዓይነት “ፎንቃ” አብዛኞቻችን ተዘረርንለት፤ ከአምላክ ባልተናነሰ እግሩ ሥር ወድቀን ሰገድንለት፤ ውስጡን ስለሚያውቅ በከንቱነታችንና በጅልነታችን እርሱም ታዝቦን ከት ብሎ ሣቀብን፡፡ የሀገራችንን ስም  ለመጥራት እንኳን የሚጠየፉ መሪዎች ወንበር ላይ ተቀምጦ በደቂቃዎች ውስጥ ሠላሣና ዐርባ ጊዜ “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” ሲል በርግጥም ልባችን ቢሠወርለት አያንሰውም – ይህን መሳይ ሰው ስንናፍቅ ብዙ ዘመን ባጅተን ነበርና፡፡ እርሱ ግን “ድመት መንኩሳ…” እንዲሉ ያደገበትንና የተሾመበትን ዓላማ ውሉን አልሳተምና ቀስ እያለ የጭቃ ጅራፉን ያኖጋው ጀመረ፡፡ ለውጡም ጥቂት እስረኞችን በመፍታትና በቃላት ድለላ ብቻ ሚሊዮኖችን በማፍዘዝ ተጠናቀቀና ለይቶለት ከነኮተቱ ገደል ገባ፡፡ በኬኛ ፖለቲካ የተጀመረው ጉዞ አሁን አሁን አማራን ወደ ማጥቃት ተሸጋግሮ የአማራን መብት ተከራካሪዎችን አከርካሪ መምታቱን ተያያዘው፡፡ አማራን ቤተስኪያን እንደገባች ውሻ ከያለበት ማሳደዱን በስፋትና በምልዓት ገፍቶበታል፡፡ መጨረሻውን ለማየት ያብቃን እንጂ የአቢይ መንግሥትም ልክ እንዳባቱ እንደወያኔው መንግሥት የአማራን ዝርያ ከየቦታው በማጥራቱ ሥራ ላይ ተጠምዷል፡፡ ያደለው በሀገር ልማትና ዕድገት ላይ ይሠማራል – ይሄኛው ግን በዘረኝነት ላይ፡፡

ለውጥማ አለ፡፡ አምናና ታች አምና ብዙ ዜጎች እንደነገሩም ቢሆን እንጀራ ቀምሰው ያድሩ ነበር፡፡ አሁን ግን ጤፉ አራት ሽህ ብርን ሊነካ ጥቂት ብሮች ቀርተውታል፤ አምስት ሊትር የምግብ ዘይት ብር 450 ነው፤ ነጭ ሽንኩርት በኪሎ ከብር 160 በላይ ነው፤ ቀይ ሽንኩርት ሊያውም መተከል ቻግኒ ላይ (የሀበሻው) ብር 65 ነው፤ ኪሎ ሙዝ ብር 30 ነው፤ ብርቱካን  ጣፋጩ ከብር 100 በላይ ነው፤ አንድ ጉርሻ እማይሞላ ፉርኖ ዳቦ ብር 3 ነው … አልቆልናል፡፡ ኑሮው የሰማየ ሰማያትን መስኮትና በሮች ጣጥሶ ሽቅብ ተወንጭፏል፡፡ ሽሮ ፈሰስ በተራ ቡና ቤት ሰባ ብር ስትባል ክትፎውን ስንት እንደሚሉህ አስበው – ከምናብህ ውጪ ነው፡፡ የእያንዳንዱ ዕቃና የአገልግሎት ዋጋ እንደሮኬት ተተኩሷል፡፡ እልም ያለ ገጠር ለመስክ ሥራ ብትወጣ ለውኃ የቀረበ መናኛ ጥብስና ዱለት እንደቅደም ተከተሉ ብር 80 እና 50 ነው፡፡ አንድ ሊትር የታሸገ ውኃ ብር 15 ነው፡፡ ተራ አልጋ በትንሹ 100 ብር ነው፡፡ ለሻይና ለቡና እንዲሁም ለአንድ ሁለት ሦስት ቢራ በያንዳንዱ 17 ደምርልኝና የቀን ወጪህን አስላው፡፡ የውሎ አበልህ ግን በቀን ግፋ ቢል 250 ቢሆን ነው – ባለ130ም አለ፡፡ ስንት ደመርክልኝ? ቁርስን በማሰብ ብቻ ዘለኸው ብር 310 ገደማ መጣልህ? አዎ፣ ሕዝብን በኑሮ ውድነት መጥበስ አንዱ የአቢይ መንግሥት ግልጽ ተልእኮ ነው – የሚገርመው ነገር ኑሮው በየደቂቃው ሲያሻቅብ አንድም የመንግሥት አካል ጅቦቹንና ዓሣሞቹን “ሃይ” አይልም፤ ምክንያቱም ሀገሪቱም ሕዝቡም ባለቤት የላቸውም – ያልታደለ ሕዝብ – ያልታደለች ሀገር፡፡ ደመወዙ ብር 2000 ሆኖ ኑሮው ብር 15000 የሚጠይቅበት ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ የቀን አበልህ ብር 130 ሆኖ በብር 400 እና 500 ሥራህን አከናውነህ እንድትመለስ የሚጠበቅብህ አእምሯቸው የመከነ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሞሉባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ እንደኛ በዕውቀትም በሀብትም ያጣ የነጣ ድሃን መግዛት ደግሞ አሳፋሪ ነው፡፡ ስለዚህ እነአቢይ ማፈሪያዎች ናቸው፡፡ በመሠረቱ ሁለት በመቶ ለማይሆን ነጋዴና ሙሰኛ የመንግሥት ቴክኖክራት የቆመ መንግሥት 98 መቶኛ የሆነውን ድሃ ሕዝብ መብት ሊያስብር አይችልም፡፡ የሀብታሞች አሽከር ነው፡፡

ለውጥ የለም፡፡ ኢሕአዲግ እያለ ለውጥ አይኖርም፤ በሽታን የፈጠረ መድኃኒትን ሊፈጥር አይችልም – እንዲያ ከሆነ አያዎ ነው – paradox፡፡ ኢሕአዲግ ፀረ-ኢሕአዲግ ሊሆን አይችልም – “ብዔል ዘቡል ብዔል ዘቡልን አያወጣም” እንዲል መጽሐፉ በኢሕአዲግ የተከሰተ ችግር በኢሕአዲግ አይጠፋም፡፡ የጥገና ለውጥ ራሱም የሚታሰብ አይደለም፡፡ ሥልታዊ ማፈግፈግ አደረገ እንጂ ኢሕአዲግ ለዬት ባለ ቅርጹ እየገዛን ነው፡፡ ፈረስ አልተቀየረም፡፡ ጋላቢ መቀየሩ ግልቢያን አያስቀርም፡፡ በአዲስ ጉልበት፣ በአዲስ ተረኛ ጋላቢ እየተጋለብን እንገኛለን፡፡ ለተወሰኑ ጥቂት ሣምንታት ጋብ ብሎ የነበረው እሥራትና ግርፋትም ከተወሰነ ዕረፍት በኋላ ተመልሶ እንደ አዲስ ፋሽን ተይዟል፡፡ የታሳሪዎች ማንነት መለዋወጥ እንጂ እሥሩ ከበፊቱም አይሎ ቀጥሏል፡፡ በፊት ታሳሪ የነበሩ አሁን አሳሪ ሆነዋል፡፡ በፊት ታሳሪ የነበሩ አሁንም በታሳሪነት የቀጠሉ አሉ፡፡ ዕድል ነው፡፡ ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም፡፡ የሁለት ወገን ተበዳይ፡፡ ያለፈውም የአሁኑም የሚያሰቃዩት ምስኪን – አማራ፡፡ እናንጋጥ፤ እንጸልይ፡፡

ለውጥ አለ፡፡ ለውጡ በፊት አማራ ተሸቆጥቁጦም ቢሆን ባፈራት ቤትና ንብረቱ እንዲኖር ይፈቀድለት ነበር፡፡ በአሁኑ ድንቅ የለውጥ ዘመን ግን ኦህዲድና ኦነግ ይህን ዕድል ለአማራው ሊሰጡት አልፈለጉም – የሞኝ አሸናፊ ዱሮም መጥፎ ነው፤ የፈሪ ዱላም ዘጠኝ ነው፤ ፈሪ አያሸንፍ፤ ሞኝም አይርታ – ሲረታ እምቢ ብሎ ነውና፡፡ ስለዚህም ምድረ ኦነጎች በፈሪ ዱላቸው፣ በተሸናፊ-አሸናፊነት ሥነ ልቦናዊ ደዌያቸው እየተሰቃዩ አማራውን ከያለበት በማፈናቀልና ሀብት ንብረቱን በመቀማት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት ግን ሁሉም ኦሮሞዎች አለመሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡ እንዲህ የሚያደርጉት በጠላት ፕሮፓጋንዳ የተበከሉና ራሳቸውን ለውጭ ኃይሎች ፍላጎት መሣካት ያስገዙ ሆዳሞች ብቻ ናቸው፡፡ ጥይት በማይበሳው የ15 እና 20 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ አውቶሞቢሎች በቅንጦት እየተጓዙና የተምነሸነሸ ኑሮ እየኖሩ በእግሩ የሚሄድ አማራንና ኦሮሞን ለማጋጨት ሌት ከቀን የሚጥሩ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ቅጥረኞች እዚሁ መሀል አዲስ አበባ በፌዴራሉ የኦህዲድ መንግሥት የሚጠበቁ አይሁዶች ኢትዮጵያን ባወጣች እየቸበቸቡ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ከዚህ አንጻር ለውጥ አለ፡፡ በዚህ ለውጥ ደግሞ ተጠቃሚው ብዙ ነው፡፡

ለውጥ የለም፡፡ ያ ሁሉ ወጣት ያለቀበት፣ ያ ሁሉ ሕዝባዊ ዐመጽ የተካሄደበት ለውጥ በአፈ ቅቤው ልበ ጩቤው አቢይ አህመድና ጓደኞቹ አማካይነት ተቀልብሷል፡፡ የነበረን ለማስቀጠል ያ ሁሉ ሰው መሞትና መሰቃየት አልነበረበትም፡፡ የነበረን የሊዝ ሥርዓት፣ የነበረን ዘረኛ ሥርዓት፣ የነበረን ሸፋፋና ወልጋዳ ሕገ መንግሥት፣ የነበረን የማያፈናፍን ቢሮክራሲ፣ የነበረን ከላይ እስከታች የተዘረጋ ሙስና፣ የነበረን አድልዖና መገለል፣ እግር ከወርች አሥሮን የነበረን መመርያና የዐዋጅ ጋጋታ፣ ለስደትና ለርሀብ ዳርጎን የነበረን የዘረኝነት አገዛዝ፣ … ለማስቀጠል አልነበረም ያ ሁሉ ሕዝብ የታገለው፡፡ ለውጥ መኖር ከነበረበት ይሄ ሕዝብ ያልተሳተፈበትና የአድልዖ ሁሉ መሠረት የሆነው ህገ መንግሥት ተብዬው ነገር በሕዝብ ይሁንታ ቢለወጥ ነበር፡፡ የወያው ህ መንግሥትም እንደህገ መንግሥት ተቆጥሮ አሥሬ “ህገ መንግሥት ተጣሰ፣ ህገ-መንግሥት ተጣሰ” እየተባለ መዘፈን የነበረበት ለውጥ የሚባል ነገር ባይከሰት ነበር፡፡ ሁሉም ነገር እንዳ በቀጠለበት ሁኔታ ለውጥ አለ ማለት በዜጎች ደም መቀለድ ነው፤ በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው፡፡ አሁን የሚታይ ግልጽ ነገር ቂጥኛም ከውርዴ ሲጫወትና ሲዶልት ነው፡፡ ምድረ አማራ-ጠል ቀፈታም  ከየአውሮፓና አሜሪካ ተጠራርቶ ኢትዮጵያን እንዴት መቃረጥ እንደሚቻልና አፍቃሬ ኢትዮጵያ የሆነውንና በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረውን በተለይ የአማራውን ጎሣ እንዴት ከምድረ ገጽ ማጥፋት እንደሚቻል በቤተ መንግሥት ቀን ከሌት ሲመክርና መመርያ ሲሰጥ ይውላል፤ ያድራል፡፡ ይህን እናውቃለን፡፡ ራሳቸውም እየነገሩን ነው፡፡ ስማቸውን እንደጊዜው ሁኔታ እየለዋወጡ ፀረ-ኢትዮጵያ አጀንዳቸውን በግላጭ እየተገበሩ ናቸው – እስስቶቹ፡፡ ጫካ ነበርን ባሉበት ጊዜ ብዙዎች ሀገር ወዳድ ዜጎችን በልዩ ዘዴ አስገድለውና ገድለው አሁን ደግሞ የቀሩዋቸውን ጥቂት ቅን አሳቢ ዜጎች ለማሰርና ደብዛ ለማጥፋት እየተጉ ነው፡፡ ስለዚህ ዘረኞችን ተክቶ የመጣ የዘረኛ ቡድን የሚያመጣው ውድመት እንጂ ደህና ነገር ባለመኖሩ አንዳችም ለውጥ የለም፡፡

ለውጥ አለ እንጂ፡፡ አለሳልሶ ወደ ሥልጣን የወጣው ጠ/ሚኒስትር ወደለየለት አምባገነን እየተቀየረ ነው፡፡ አለው እንለው የነበረውን ዕውቀትና የንግግር ችሎታ ወደጎን በመተው ወደ ብልጠትና የራስን ፍላጎት ለማሳካት በኃይልና በዛቻ ወደመምራት እየተሸጋገረ ነው፡፡ ነገሩ የየጁ ደብተራ ዓይነት መሆኑ ነው፡፡ ምክንያትና ተጠየቃዊ አካሄድ ሲከዳ ወደጉልበት መዞር የነበረና ያለም ነው፡፡ ሴትዮዋ ልጇ “እማየ ጣቴን አሳከከኝ” ብትላት “እኔም በአንድ ቀን አልተቆመጥኩም” አለቻት ይባላል፡፡ እነመንግሥቱ ኃ/ማርያምም፣ እነቦካሣም፣ እነኢዲያሚንም፣ እነጋዳፊም፣ እነሂትለርም፣ እነሙሶሊኒም፣ እነቢስማርክም፣ እነዚያድባሬም፣ እነካሙዙ ባንዳም፣ እነስታሊንም፣ እነፒኖሼም፣ እነኪም ኢል ሱንግም፣…. በአንድ አዳር አምባገነን አልሆኑም፡፡ አምባገነንነት ቀስ እያለ የሚከሰት የአእምሮ ቁምጥና ውጤት ነው፤ ክፉ የአእምሮ ስንኩልነት፡፡ አቢቹም አፋጠነው እንጂ ወደነዚህ “ሰዎች” ጎራ እንደሚቀላቀል ግልጽ ነበር – መነሻው ትክክል ያልሆነ መገስገሻውና መድረሻውም ትክክል አይሆንም – በወንጀል የተገነባ ስብዕና፣ በተንኮል የተዋቀረ ቁመና በምክንያታዊነት ጥምቀት ስለማያምን ምክንያታዊነትን አምርሮ ይጠላል፤ ምክንያታውያንንም ስለማይወድ አያስቀርባቸውም ብቻ ሣይሆን እየተከታተለ ያጠፋቸዋል፡፡ እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡

አታሞ በሰው እጅ ታምራለች፡፡ ሲይዟት ግን ታደናግራለች፡፡የሥልጣን ብቸኛ ምንጭ ሕዝብ እስካልሆነ ድረስ፣ በጅዶና በጠረባ በአቋራጭ የሚገኝ ሥልጣን ምን ጊዜም ወደ አምባገነንነት መውሰዱ አይቀርም – አለዚያ አይጸናማ፡፡ ሥልጣን ያሳሳል፤ ወንበር ያጓጓል፡፡ ተማርክ አልተማርክ ዋጋ የለውም፡፡ ዋናው በወደድከው መቁረብህ ነው፡፡ ሥልጣን ከወደደክ ሀገርና ሕዝብ ገደል ቢገቡ ደንታህ አይደለም፡፡ የቀን ቅዠትህና የሌት ቅብዥርህ ሁሉ የሚያቀጣጨው ሥልጣንህን ባለማስነጠቁ ላይ እንጂ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው፡፡ ስለዚህ በከንቱዎቹ አንፍረድባቸው፡፡ አንዴ አለመለከፍ ነው እንጂ በሥልጣን ሱስ ያበደና የሰከረ ሰው እንኳንስ የምርጫና የሚኒስትሮች መተዳደሪያ ደምቦችን፣ የሀገር የኅልውና አውታሮችን በደቂቃዎች ውስጥ እስከማፈራረስ ሊደርስ ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ሥልጣን ደግሞ በባሕርይው የተረገመ ነው፡፡ ያንቀዠቅዣል፤ ኅሊናን ያሳውራል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭብጨባ ደግሞ በተለዬ ያሳብዳል፤ ነፈዝ ያደርጋል፡፡ እላይ ስትወጣ ሀብት ንብረቱና ገንዘቡ ብቻ ሣይሆን ዜጎችንም አንተ ራስህ የፈጠርካቸው ሊመስልህ ይችላል፡፡ ስለሆነም ሥልጣኑንም ሆነ ሁሉንም የሀገር ንብረት እናትህ ከጉሊት ገዝታ እንዳመጣችልህ የድንች ጥብስ ለወደደድከው ታድለዋህ፤ ለጠላኸው ትነሳዋለህ፡፡ ሁሉም ያንተ ነው፤ ሁሉም ላንተ ያሸረግድልሃል፡፡ ያኔ አንተም ይሞቅሃል፡፡ ራቁትህን ብትሄድ ሁሉም ራቁቱን ይሄድልሃል – ለክብርህ፡፡ ሳያስነጥስህ መሀረቡን የሚዘረጋልህ ብዙ ነው፡፡ኧረ ሚስቱንም የሚጋብዝህና እንድትሾመው ደጅ የሚጠናህም አታጣም፡፡ እኛ እኮ መልካችን እንደነብር ዥንጉርጉር ነው፡፡ ስትወድቅ ግን አንተን አያድርግ፡፡ ያሽቃበጠልህ ሁሉ ቀድሞ ያዋርድሃል፡፡ ጅሎቹ ባለሥልጣናት ያልተረዱት ይህንን መሠረታዊ ሃቅ ነው፡፡

አፄው ግማሽ አምላክ እስከመሆን ደረሱና ተመለኩ፡፡ መንጌ ያቺ ልቡ አበጠችና እንደእፉኝት ተነፋፋ፡፡ መለስ አብጦ አብጦ ንግግሩን ሳይቀር መቆጣጠር አቃተው፡፡ ሁሉም ግን መጨረሻቸው አንድ ሆነ – ውርደት፡፡ ይቺ አቢቹም ከአሁኑ የምትሠራውን አጥታለች፡፡ ኢትዮጵያን በኦሮሞ እየወረረች “በኔ የሥልጣን ዘመን ኦሮሞ የተለዬ ጥቅም አግኝቶ ከሆነ በ24 ሰዓት ሥልጣኔን እለቃለሁ” ስትልም በሣቅ ገደለችን- ቀላል አሾፈች እንዴ!- (አንድ ያስገረመኝን ነገር ልተንፍስ፡- ትናንት አንድ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ የምሥክር ወረቀት አየሁ፤ ሁለት ኃላፊዎች የፈረሙበት ነው፡፡ ሁለቱም ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ አጋጣሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ሆን ተብሎ ሁሉንም የኃላፊነት ቦታ ልክ እንደወያኔው ዘመን ሁሉ በተረኛ ዘውግ የመሙላትና ተረኛ ዘወግን የመጥቀም ሌሎችን ደግሞ የማንጓለል ግልጽ ዘመቻ ነው)፡፡ አቢቹ የጫጫና የደብረ ብርሃን አካባቢ አማራን ትታ “ከሱልልታና ከሰንዳፋ ኦሮሞዎች ጦር ሰብቀው በፈረስ እየተመሙ… እንዴት አድርጌ መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎቹን ልሰር..?” ብላም አስቃናለች – (መቼ ሰሙና ማን ነገራቸውና)፤ በፊትም ኢንጂነር ስመኘው ራሱን አጠፋ ብላ አስቃናለች፤ በቀደምለትም የምትሠራውን ከሠራች በኋላ በሁሉን ዐወቅ የአተራረክ ሥልቷ ደራሴ-ተውኔት  ወተዋናይ አቢይ የባሕር ዳሩን ጭፍጨፋ “የአማራ ክልል መንግሥት ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ ከሸፈ” በማለት በአግራሞታዊ ሣቅ ፈጀችን፤  ምን አለፋችሁ ሥራዋ ሁሉ ማሣቅና ማሳቀቅ ብቻ ሆኖ አረፈው – ምን ይሉኝንም እንክት አድርጋ በልታዋለች – አለመታደል ነው! (አቢይ ግን ከቤተ መንግሥት ይልቅ ለብሔራዊ ትያትር ይቀርባል፤ ደምበኛ ቲያትረኛ አይደል እንዴ! (“መፈንቅለ መንግሥቱ” ግን ከመጀመሩ መክሸፉ፣ ከመክሸፉም አዲስ አበባ ላይ ለሚገኙ ሁሉን ዐወቅ ሰዎች መፈንቅለ መንግሥት መሆኑና አለመሳካቱ በቅጽበት መታወቁ  እናንተዬ!)፡፡ ሥልጣን እንዲህ ያባልጋል፤ ያውራልም፤ ይሉኝታና ሀፍረትንም ከሰውነት አውጥቶ ባዶ ቀፎ ያደርጋል፡፡) ይህን መሰሉ የአቢቹ የሀሰት ክምር አንድም ከትዕቢትና ከትምክህት የሚመነጭ ነው፤ አንድም ዜጎችን በአላዋቂነት ከመፈረጅ የሚበቅል ገለባነት ነው፤ አንድም ራስን ካለማወቅና ለራስ የተለዬ ቦታ ከመስጠት ታላቅ ድንቁርና የሚፈልቅ ነው፤ አንድም ሀሰትን እንደባሕርይ ልብስ ከመውሰድ የሚመጣ ነው – መለስን pathological liar ነበር እንደምንለው ፡፡ እውነቱን እኮ ራሱ አቢይም ያውቀዋል፡፡ አይደለም የአሁኑን እውነት ቀጥሎ የሚመጣውን እውነት ሳይቀር ውስጠ ውሳጤው ያውቀዋል – (his subconscious, I mean)፡፡ ሥልጣን እንዲህ ነው፡፡ ድብን አድርጎ ያሳውራል፡፡ እላይ ያለው እንዲህ እንደጣቃ የሚተረተር ከሆነ ከርሱ ቀጥሎ ያሉትማ እንዴት ይሆኑ? አዎ፣ ቤት ጣራው ካፈሰሰ ማገሩና ወጋግራውም መፍረክረኩ አይቀርም፡፡ ወዮልን!

የማያድግ ልጅ ካካው ብዙ ነው፡፡ ሌላም ልጨምርልህ፡፡ የማያድግ ልጅ በአባቱ ብልት ይጫወታል፡፡ ልሰልስልህ ከፈለግህ፡፡ “አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት የባሏን መጽሐፍ አጠበች”፡፡ ይህ ሁሉ ምሣሌያዊ አባባል በአንድ ወይ በሌላ መልክ ለአቢቹ ይገጥማል፡፡ ጥሩ ነው፡፡  አቢይ ብዙ ጊዜ ያለው አይመስለኝም፤ ነገረ ሥራውም ይህን ከመረዳት የመነጨ ይመስላል፡፡ ጥድፊያ ያበዛል፡፡ አንዳንዴ እንዳባባ ታምራትም መሆን ይቃጣዋል – በአንድ ጊዜ ብዙ ቦታ የመከሰት ዓይነት ተዓምራዊ ድርጊቶች ያስደስቱታል-  በዚያውም ተከታዮችን ማስደመምና ማስጨበጨብ፡፡ ለነገሩ ይፍጠን፡፡ ፍጠን በሉት፡፡ የሚጠቅመውን በቶሎ ይጥቀም፡፡ የሚያስወግደውንም በቶሎ ያስወግድ፡፡ ‹ባለቀ ጊዜ አትዘናጋ› በሉት፡፡ የሁሉንም ሂሣብ ግን በቅርብ ያወራርዳል፡፡ ወያኔም ….

ስለወያኔማ ይህችን ብዬ ልሰናበት እንጂ፡፡ በአንድ ተራራ ላይ ከሚኖሩ ቤቶች በአንደኛው እሳት ይነሳል፡፡ ጎረቤቶች እሳቱን ለማጥፋት በአፈርም፣ በቅጠልም፣ በውኃም … ባላቸው ነገር ሁሉ መረባረብ ይዘዋል፡፡ ከተራራው ግርጌ አንድ ኩሬ አለ፡፡ በዚያ ኩሬ ከሚኖሩ ዕንቁራሪቶች መካከል አንዷ ቀበጥ ዕንቁራሪት እሳት የሚያጠፉትን ሰዎች ሽቅብ እየተመለከተች በማፌዝ መልክ ታሽካካ ይዛለች፡፡ አንዷ አሮጊት ዕንቁራሪት ግን “ምን ሆነሻል አንች ልጅ? ዝም አትይም? ግፍ አታኑሪ”ብላ ትገስጻታለች፡፡ ልጂት ግን “እንዴ እኔ ውኃ ውስጥ እያለሁ ምን እሆናለሁ?” በማለት በተቸገሩት ሰዎች እያላገጠችባቸው ማንቋረሯን ትቀጥላለች፡፡ መንደርተኞቹ በአካባቢያቸው የሚገኝን ነገር ሁሉ ጨርሰው በባልዲ ውኃ ለመጨለፍ ወደዚያ ኩሬ ወረዱ፡፡ ሌሎቹ ወደኩሬው ውስጠኛ ክፍል ወርደው በመሸጎጥ ራሳቸውን ከአደጋ ለማውጣት ሲሞክሩ ያቺ ለፍላፊ ግን በመጀመሪያው ባልዲ ተጠልፋ የእሳት ማጥፊያ ሆነች፡፡ አያድርስ ነው፡፡ ኦህዲድ/ኦነግ አማራን ለመጨረስ ያብቃቸው እንጂ እርሱን ከጨረሱ በኋላ የጎሣ ፖለቲካቸውን ጦር ዒላማ ወዴት እንደሚያዞሩት ለማወቅ በግድ አሮጊት ዕንቁራሪት መሆንን አይጠይቅም፡፡ ከሁለት ጠላቶች ጋር መፋለም አዋጭ ባለመሆኑ እንጂ ትግሬ ከአማራ ያነሰ ጠላት መሆኑን ከመረዳት አይደለም የኦነግ ሕወሓትን “መታገስ”፡፡

በኢትዮጵያ የሚገርም ሞኝነት እየተስተዋለ ነው፡፡ ሁሉም ቢስማማና ቢተባበር በግሩም ሁኔታ ደልቶት መኖር እየቻለ እንደ እናት ገዳይ እየተያዩ አንዱ ከአንዱ በየተራና በሤራ ፖለቲካ መናቆር የሚያስደንቅ ድንቁርና ነው፡፡ ለነሱ ይሄኔ ዘመናዊነትና ብልኅነት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ግን ጭልጥ ያለ ገልቱነት ነው፡፡ ዛሬ ቦምብ የምታጠምድለት ወገን ነገ ላንተ ወርቅ አንጥፎና የዘምባባ ዝንጣፊ ይዞ አይጠብቅህም፡፡ የሚያዋጣው በንጹሕ ልብ ቅራኔን አስወግዶ ተከባብሮና ተስማምቶ መኖር ነው፡፡ ይህን የምለው ለቅን አሳቢዎች እንጂ ለአጋንንቱ አይደለም፡፡ ምክንያቱም መጥፎ ልማድ ካላስቀበረ ስለማይለቅ ሕወሓትንና ኦህዲድን ለመምከር መቃጣት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ነው፡፡ ተልእኳቸው ልዩ ስለሆነ ሆዳቸው ተገልብጦ ካልተሰፋና በቂም በቀልና ጥላቻ የደነደነው ልባቸው በፍቅር ሞረድ ለስልሶ ካልተስተካከ