ቪቫ ሽመልስ ! ዳውን ዳውን አዴፓ!  - ቻኪሳው የበለሳው – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ቪቫ ሽመልስ ! ዳውን ዳውን አዴፓ!  – ቻኪሳው የበለሳው

1 min read
8

መቼም ለዚህች አጭር የትዝብት ፅሁፌ የመረጥኩት ርዕስ ብዙዎችን ሊያናድድ አልያም ሊያስገርም እንደሚችል አውቃለሁ::ሆኖም በፈረሰች ኢትዮጵያ ላይ ቆሞ አንድነትን እየዘመረ ላለፉት 30 ዓመታት በቁሙ ለሚፈጀው እና የጄኖሳይድ ሰለባ ለሆነው የአማራው ማህበረሰብ፣ ለፀረ-አማራ ሆኖ ለተደራጀው አዴፓ፣ ለፅንፈኛ የኦሮሞ አክራሪዎች እንዲሁም ከጀርባው ለሚያርዱት የፖለቲካ ሴረኞች ሁሉ የሚያስተላልፈው አንዳች መልዕክት ይኖረዋልና እውነታውን ተረድቶ ፍርድ መስጠቱንም ለእናንተው ትቻለሁ:: ዛሬም ድረስ ዓለም በፅኑ የሚያወግዘው የሩዋንዳው የዘር እልቂት ሲፈፀም አብይ አህመድን ለሰላም ኖቤል ሽልማት እንዲታጭ ፕሮፖዛል ያቀረበው ዶክተር ግሩም ዘለቀ በአንድ ፅሁፉ እንደገለፀው “ቱስሲዎች ዛፎች፣ እባቦች፣ በረሮዎች ተብለው ይጠሩ ነበር። እነዚህ ስሞች የተሰጡት ሁቱዎቹ ቱስሲዎችን ለመግደል በቂ ምክንያት እንዳላቸው ሆኖ እንዲሰማቸው አድርጓል። ‹በረሮዎቹ› ላይ ጥላቻን ለመግለጽ የተፈጠሩ የሚዲያ ጣቢያዎች ነበሩ ፡፡ቱትሲዎችን ከፍተኛ ትምህርት እና በመንግስት የስራ ቦታ መከልከል ተጀመረ።የሬዲዮ ጣቢያዎች በቱትሲዎች ላይ ጥላቻ እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋጽዎ አድርጓል።” ከዚህ ሌላ በኢ-መደበኛ አረጃጃት የተመሰረቱ አክራሪ የሁቱ ነፍሰገዳይ የኢተርሃምዌ ቡድኖችም ለይተው የሚገሏቸውን ሰዎች ስም አዘጋጅተው በፈፀሙት ጥቃት በመቶ ቀናት ውስጥ ከ 100 ሺህ የሚልቁ ቱትሲዎችን እና ለዘብተኛ ሁቱዎችን በገጀራ በዱላና በጦር መሳሪያ በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፈው መግደላቸውን ታሪክዛ ሬም ድረስ ያወሳዋል:: በኢትዮጵያም እየተፈፀመ ያለው ይኸው ነው:: የአክሱማዊው ሥርወ መንግሥት ከአጼ ዮሃንስ ሕልፈተ ሕይወት በኋላ ከትግራይ ወደ ሸዋው ምኒልክ መዛወሩ የእግር እሳት የሆነባቸው አንዳንድ የትግራይ ልሂቃንም ሆኑ ንጉሰ ነገሥት ምኒልክ በአገር ምስረታው ሂደት ኢትዮጵያን በኃይል አንድ አድርጓታል የሚል ቂም እና ቅሬታ ያላቸው የኦሮሞ አክራሪ ቡድኖች የጋራ ጠላታችን ነው በሚሏቸው የአንድነት ኃይል ተብለው በሚጠሩት የኦርቶዶክስ ዕምነት እና የአማራው ማህበረስብ ላይ በጭፍን ጥላቻ ላይ የተመሰረት የተደራጀ ጥቃት እና ዴኖሳይድ ሲፈፅሙ ከ 50 ዓመታት በላይ ተቆጥሯል:: በተለይም ትህነግ ወያኔ ከአማራው ክልል ከወሎ እና ጎንደር በርካታ ወረዳዎችን በኃይል ቀምቶ የራሱን ክልል በ60 በመቶ በማስፋቱ እና የቆየ የሥልጣን ተቀምቻለሁ ቂሙን ለመበቀል በማኒፌስቶው ላይ ጭምር የሩዋንዳ ሁቱዎች ቱትሲዎች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ለመፈፀም እንዲያመቻቸው “በረሮ” የሚል ስያሜ ሰጥተው እንደተንቀሳቀሱ ሁሉ የትግራዩ ሕወሓትም አማራውን “ነፍጠኛ” በሚል ሽፋን የትግራይ ሕዝብ ዋና ጠላት አድርጎ በመፈረጅ በስልጣን በቆየባቸው 27 ዓመታት ከፍተኛ የዘር ዕልቂት ማፈናቀል እና በደል በዚህ ህዝብ ላይ ሲፈፅም ከመቆየቱም በላይ አሁንም የሌሎች ብሄር ተወላጆችን በሃሰተኛ የቂም እና የጥላቻ ትርክት በማደራጀት የውክልና ጦርነት አስከፍቶ የአማራ ህዝብና ክልል በማያባራ ስጋት እንዲኖር ቀን እና ሌት ተግቶ እየሰራ ይገኛል:: ትህነግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በተለይም ከ 1983 ዓ.ም በኋላም ከኦነግ ጋር በመቀናጀት በአርባጉጉ በደኖ ወተር, ጉራፈርዳ እና በአብይ አህመድ የትውልድ መንደር በበሻሻ ጭምር ለፍቶ አዳሪ አማራዎችን “ነፍጠኛ” በሚል ኮድ በቁጥር ከ 3100 የሚልቁ ህጻናትን ቀሳውስትን እና ነፍሰጡር ሴቶችን ሳይቀር ገሚሱን ከነሕይወታቸው ገደል በመክተት ሴቶቹንም ጡታቸውን እየቆረጡ በስቃይ እንዲሞቱ በማድረግ የአማራውን አንገት ለማስደፋት ላይ ይህ ነው የማይባል የዘር ማፅዳት ዘመቻ ሲካሄድበ ቆይቷል:: በቡራዩ፣ ሰበታ በጅማ፣ ሆለታ፣ ሻንቡ፣ ከሚሴ ወሎ፣ አሰላ፣ ሻሸመኔ፣ ዓወዳይ፣ አዳባ፣ ባሌ ሮቤ እና ሌሎች አካባቢዎችም ኦሮሞ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን በተለይም በአማራ፣ በጉራጌዎች በጌዶዎች፣ በጋሞዎችና ኦርቶዶክስ ኦሮሞ በሆኑ ላይ ጉዳት ብቻ ሳይሆን ግድያዎች ከተጀመሩም ሰንብተዋል። ሚልዮኖችን ሰብስቦ “ነፍጠኛውን የሰበረን ቦታ ሰባብረን ፊንፊኔን ተቆጣጥረናል ” የሚል ጄኖሳይድ በተዘዋዋሪ መንገድ በአደባባይ ባወጀ ማግስት አሁን ደግሞ ኦዴፓ አባይ ማዶ ባህርዳር ድረስ ተሻግሮ በአማራ ክልል ኦዴፓ ስለፈፀመው የፖለቲካ ሴራ እንዲሁም አማራን እና አማርኛን ቋንቋ ለማዳከምና ለማጥፋት እየተከናወነ ስላለው ተጨማሪ የጄኖሳይድ ወንጀል ዕቅድ ምስጢር በአንደበቱ የመሰከረበትን የድምፅ መረጃ በመገናኛ ብዙሃን ሰምተን አቋማችንን በጊዜ እንድናስተካክል እረድቶናል:: የኦሮሞው ኦዴፓና በአማራ ስም የሚቆምረው የሌላ ብሄር ስብስብ የሆነው ፀረ-አማራው ድርጅት አዴፓ የአማራው ጠላት ናቸው ስንል አለምክንያት አለመሆኑን ከበቂ በላይ ምሳሌዎችን ዘርዝረን ማሳየት እንችላለን::

 

ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የተመሰረተው ህወሃት ቅቡልነት አግኝቶ የትጥቅ ትግሉን ለመግፋት ያመቸው ዘንድ እንዳሻው የሚጋልበውን ብአዴን ጠፍጥፎ ሲሰራው ስያሜው አንድ ብሄርን ማለትም አማራን ብቻ የሚወክል ሳይሆን የብረ ብሄር ቅርፅ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ ኢሕዲን በሚል ስያሜ ነበር:: አመራሮቹም ሆነ አባላቱ እንደ በረከት ስምዖን ያሉ ኤርትራውያን እንደነ ታምራት ላይኔ ተፈራ ዋልዋ አዲሱ ለገሰ እና የአሁኑ የመከላከያ ምክትል ኤታማጆር ሹም ብርሃኑ ጁላና አባ ዱላን የመሳሰሉ የኦሮሞና የደቡብ ብሄር ተወላጆችን በስሩ ያቀፈ መሆኑም አይዘነጋም:: የአማራው ሕዝብ የሚደርርስበትን ጄኖሳይድ ግድያና አፈና በመቃወም በታዋቂው የህክምና ባለሙያው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አማካኝነት የአማራው ጥቃት ተከላካይ ድርጅት መኢሕድ መመስረቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ግን ስጋት የገባው ትህነግ/ሕወሓት ፕሮፌሰሩን እና የአመራር አባላቱን ከማስወገድ ጀምሮ አማራውን ጠርንፎ የሚቆጣጠርለትና በእሱ ትዕዛዝና መመሪያ ሰጪነት እንዳሻው አማራውን አንገት የሚያስደፋለትን አሻንጉሊት ድርጅት ፈጥኖ መመስረት እንዳለበት ወስኖ በወቅቱ የኢሕድን ሊቀመንበር የነበረውን ታምራት ላይኔ እጅ ጠምዝዞ ወደ አማራ ዘውግ ድርጅትነት ስሙን እንዲቀይር አድርጎታል:: ከዛ በኋላ ነው እንግዲህ የዛሬው አዴፓ ወይም ብአዴን ቀሪ አማራ ጠል የሆኑ አብዛኛው አማርኛ ተናጋሪ የሌላ ብሄር ተወላጆችን በኤርትራዊው በረከት ስምዖን ሊቀመንበርነት እንደነ ካሳ ተክለብርሃን ፣ ህላዊ ዮሴፍ ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አገኘሁ ተሻገር፣ ንጉሱ ጥላሁን ያሉ የትግራይ፣ ኤርትራ፣ ኦሮሞና ደቡብ ተወላጅ የቀን ጅቦች በአምራ ስም ከጎኑ አሰልፎ የአማራን ጥንታዊ ርስተ መሬት ለትግራይና ለሱዳን ሲያስረክብ በሥርዓቱ ላይ ሰላማዊ ተቃውሞ ማሰማት የጀመሩትንም የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ሲያስበላ ሲያስገድል አካል ሲያጎድልና ዘር ሲያመክን 30 ዓመታት የዘለቀው:: ይህን ደግሞ በምሳሌ ማየት ይቻላል::

 1. ደመቀ መኮንን :-አገው ወረዳ ተወለድኩ የሚለውና በወሎ ማሊያ የሚጫወተው የወቅቱ የአዴፓ ሊቀመንበር ደመቀ መኮንን ከዛሬ 15 ዓመታት በፊት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት በነበረው አያሌው ጎበዜ የስልጣን ዘመን ሕወሃት በሱዳን አዋሳኝ ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ እንደ ከፋኝ እና የአርበኞች ግንባር ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይላትን ከአካባቢው ለማጥፋት በወጠነው ዕቅድ መሰረት 12 ሺህ ሄክታር የኢትዮጵያን ለም መሬት ቆርሶ ለሱዳን ያስረከበበትን የአገር ክህደት ወንጀል እንዲሳካ ትልቅ ሚና ከተጫወቱት መካከል ስሙ የሚጠቀስ ነው:: በወቅቱ አሻጥሩ ያልተስማማው አያሌው ጎበዜ ስልጣኑን ለቆ በገዱ አንዳርጋቸው እንዲተካ ተደርጓል:: የመሬት ርክክቡን እንዲያስፈፅም በህወሃት ወያኔ የተሰየመው በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበረው አባይ ፀሃዬ የመተማ አስተዳዳሪ የነበረውን ሙሉአለም ገሌ በሄሊኮፕተር ጭኖ አወዛጋቢው የድንበር መሬት ድረስ በመውሰድ ከሱዳን ወኪሎች ጋር እንዲፈራረም ቢያስገድደውም አሻፈረኝ የኢትዮጵያ መሬት ነው በማለቱ ጥርስ ተነክሶበት በእነ ገዱ እና ደመቀ አቀናባሪነት 36 ልዩ ልዩ የወንጀል ክስ ተመስርቶበት በእስር ፍዳውን እንዲያይ ተደርጓል:: በርካታ አርሶአደሮች ለሱዳን መሬቱ ተላልፎ መሰጠቱን በመቃወማቸውና በሙሉዓለም ጎን በመሰለፋቸው እየተለቀሙ ማዕከላዊ ድረስ ተልከው በቶርች እና ግርፋት አሳራቸውን እንዲበሉ ተደርገዋል::ለሀገሩ የሚቆረቆር መንግስት እና እውነተኛ ፍትህ በአገሪቱ ቢኖር በአገር ክህደት ወንጀል ሞት አልያም የዕድሜ ልክ እስራት ሊበየንበት የሚገባው ደመቀ ሕወሃትን ትግርኛ ተናጋሪ መሆኑንና የዛ ብሄር ደም እንዳለበት በማሳመኑ ከተራ አባልነት እንደ ሮኬት በአንዴ ተተኩሶ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ዛሬም ድረስ የተቆናጠጠውን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርነትን ማዕረግ ሊቀዳጅ በቅቷል:: ይህ ወንጀሉ ይታወቃልና ለሱዳን የመሬት ርክክቡ ከመጠናቀቁ አስቀድሞ “ከደሙ ንፁህ ነኝ የለሁበትም” ለማሰኘት ሕወሃት በወቅቱ ወደ ለንደን ለትምህርት ልኮት ነበር:: ዛሬ ላይ ወያኔ ደጋግማ “በደመቀ ተከዳሁ” የማለቷ የእዬዬ ም ምስጢርም ከዚህ በመነጨ ነበር:: በለውጡ ማግስት የኢትዮጵያን መሬት ከህወሃት ጋር ተባብራችሁ ለሱዳን ሰጥታችኋል ይባላል ምን መልስ አሎት ሲል የአማራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ያቀረበለት ደመቀ አይኑን በጨው አጥቦ “እኔም የኢትዮጵያ መሬት መሆኑን ያወኩት በቅርቡ የአካባቢው ገበሬዎች ለሌላ ጉዳይ ቢሮዬ መጥተው እግረ መንገድ ሲነግሩኝ ነው:: ክው ብዬ ደንግጫለሁ:: በዛ ሰአት ደግሞ ለትምህርት ውጭ ስለነበርኩ የተሰራውን ስህተት አላወኩም:: አሁን ከያዝናቸው የአማራው ማታገያ አጀንዳዎች ይህን መሬት በንግግር እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ከሱዳን ማስመለስ ነው” ሲል የፉገራ መልሱን ሰጥቷል:: የቃለ-መጠይቅ ቪድዮውን ከዩቲዩብ ላይ ማየት ይቻላል::ለሀገሩ የሚቆረቆር መንግስት እና እውነተኛ ፍትህ በአገሪቱ ቢኖር በአገር ክህደት ወንጀል ሞት አልያም የዕድሜ ልክ እስራት ሊበየንበት የሚገባው ደመቀ ሕወሃትን ትግርኛ ተናጋሪ መሆኑንና የዛ ብሄር ደም እንዳለበት በማሳመኑ ከተራ አባልነት እንደ ሮኬት በአንዴ ተተኩሶ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ዛሬም ድረስ የተቆናጠጠውን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርነትን ማዕረግ ሊቀዳጅ በቅቷል:: ይህ ወንጀሉ ይታወቃልና ለሱዳን የመሬት ርክክቡ ከመጠናቀቁ አስቀድሞ “ከደሙ ንፁህ ነኝ የለሁበትም” ለማሰኘት ሕወሃት በወቅቱ ወደ ለንደን ለትምህርት ልኮት ነበር:: ዛሬ ላይ ወያኔ ደጋግማ “በደመቀ ተከዳሁ” የማለቷ የእዬዬ ም ምስጢርም ከዚህ በመነጨ ነበር:: በለውጡ ማግስት የኢትዮጵያን መሬት ከህወሃት ጋር ተባብራችሁ ለሱዳን ሰጥታችኋል ይባላል ምን መልስ አሎት ሲል የአማራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ያቀረበለት ደመቀ አይኑን በጨው አጥቦ “እኔም የኢትዮጵያ መሬት መሆኑን ያወኩት በቅርቡ የአካባቢው ገበሬዎች ለሌላ ጉዳይ ቢሮዬ መጥተው እግረ መንገድ ሲነግሩኝ ነው:: ክው ብዬ ደንግጫለሁ:: በዛ ሰአት ደግሞ ለትምህርት ውጭ ስለነበርኩ የተሰራውን ስህተት አላወኩም:: አሁን ከያዝናቸው የአማራው ማታገያ አጀንዳዎች ይህን መሬት በንግግር እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ከሱዳን ማስመለስ ነው” ሲል የፉገራ መልሱን ሰጥቷል:: የቃለ-መጠይቅ ቪድዮውን ከዩቲዩብ ላይ ማየት ይቻላል::

አገኘሁ እንግዳ፣ ደመቀ እና ገዱ አንዳርጋቸው እንደለመዱት አላየሁም አልሰማሁም ለማለት፤

የአማራን ጥንታዊ ርስት ለማስመለስ፤ የራያ እና ወልቃይት ጉዳይ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ እና አማራን ከጥቃት ለመከላከል የልዩ ሃይል ሰራዊት እንዲሰለጥን ፈር ቀዳጅ ሆነው አዲስ የትግል መስመር የጀመሩት እነ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ዶክተር አምባቸው አቶ ምግባሩ ከበደና ሌሎችም የአማራው የቁርጥ ቀን ልጆች በኦዴፓ የፖለቲካ ሴራ እንዲገደሉ የተቀነባበረው ድራማ ከመፈፀሙ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ለህክምናና ለስብሰባ በሚል ወደ አሜሪካና ጀርመን እንዲላኩ መደረጉንም የምንረሳው አይደለም:: ደመቀ ዛሬ በሚያወዛግበው የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይ በ 1997ቱ ምርጫ በቅንጅት ድል የተመታው ሕወሓት ተደናግጦ አማራን እና ኦሮሞን ለመከፋፈል በቀየሰው አዲስ ዘዴ ከዛ በፊት የኦሮምያ ክልል ምክርቤትንና ዋና መቀመጫ ከአዲስ አበባ አባሮ አዳማ ናዝሬት እንዲያደር ከወሰነ በኋላ ዳግም ተመልሶ አዲስ አበባ ላይ ጨፌ ኦሮምያ ስራውን እንዲቀጥል በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንዲያገኝ ያለ ሕዝብ ውይይት የህገመንግስት ማሻሻያ ሲያደርግ ዋናው ደጋፊ ሆኖ በፊርማው ያፀደቀና ድምፅ የሰጠ እንደሆነ ይህም ቃለ ጉባኤ በምክር ቤት እንደሚገኝ አምና ሮፖርተር ጋዜጣ በአንድ እትሙ አብራርቶ ገልጿል::

 1. አገኘሁ እንግዳ:- “መለስ ዜናዊ በመንግሥታዊ ስልጣን ላይ የነበረው ዕይታ ሳይንሳዊ እና ተራማጅ ነው ” እያለ በየመድረኩ ከሕወሃት በላይ መለስን የሚያንቆለጳጵሰው ይህ ውሽልሽል ግለሰብ የሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪ እንደነበር አይዘነጋም:: የመጠጥ ሱሰኛ ነው እየተባለ የሚታማው ግለሰቡ እንደለመደው በአልኮል መጠጥ ናውዞ በባርዳር ከተማ መኪና ሲያሽከረክር አንድ ወጣት ገጭቶ ቢገልም በስልጣኑ ምክንያት በነጻነት እንዲንቀሳቀስ የተፈቀደለት ወንጀለኛ መሪ ነው:: በጣም የሚገርመው ለሀገር እና ሕዝብ ደህንነት የማይጨነቅ አደርባይነቱ ብቻ ሳይሆን ሕወሓት ስልጣን ተቀምታ ወደ መቀሌ ከመሸኘቷ በፊት በነበሩት 4 ዓመታት አይከል እና ጭልጋን ጨምሮ 2 ወረዳዎችን ከአማራ ክልል ነጻ ቀጣና ውጪ አድርጎ የቅማንት ማህበርሰብ ለብዙ ሺህ ዘመናት በደም ከተጋመደው አማራው ጋር ደም እንዲቃባ ከባድ እና ቀላል የጦር መሳሪያ እንዲሁም ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጥ እሱ አይቶ እንዳላየ ማለፉ ከቅማንት ብሄርም ሆነ ከቡድኑ ጋር አንዳች የስጋ ዝምድና አለው የሚል መረጃዎች ሊወጡበት ችሏል:: አማራ ዙሪያውን በጠላቶች ተከቧል ሰላሙን ማስጠበቅ አለብን ብሎ ያንን ክልል ፈጣን በሆነ ሁኔታ ከክልሉ ፕሬዝዳንት ዶክተር አምባቸው ጋር ተናቦ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍንበት የቅማንት ነፃ አውጪ ነኝ የሚለው ቡድንም በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈጽመው ግድያና አፈና እንዲገታ ያደረገው ጄኔራል አሳምነው ላይ ፈጣን እርምጃ እንዲወሰድበት በምክርቤት ሳይቀር ሲወተት የነበረ ሰው መሳይ በሸንጎ ነው አገኘው :: ይህንንም ንግግሩ ከታች በለጠፍኩት ቪድዮ ላይ ማድመጥ ይቻላል:: የሚያሳዝነው አገኘሁ አሳምነው ፅጌ የአማራን ጥቃት ተከላካይ ልዩ ሃይል ማሰልጠኑ ክፉኛ ይከነክነው ስለበር አሳምነውን ከኦዴፓ ጋር ባቀናጁት የፖለቲካ ሴራ ከመግደላቸው ሁለት እና ሶስት ቀናት ቀደም ብሎ በዚህ ድንፋታ አዘል ንግግሩ “እኛ ለስሙ የክልሉ ካቢኔ ነን:: ሌላ መንግስት ግን አለ:: እኛን ተክቶ ክልሉን ሊመራ የሚፈልግ:: ይሄን ነው መታገል ያለብን ይህ ክልል ሊረጋጋ ከሆነ:: ይሄንን ልንታገል ክልቻልን ይሄ ክልል ከዚህ በላይ በጣም ብዙ ጉዳቶች ሊደርሱበት ይችላል” ሲል ነበር የግድያውን ትዕዛዝ በእጅ አዙር የነገረን:: እጅግ የሚያቆስለው ይህ ከንቱ ሰው ወዲያው ጄኔራል አሳምነውን እንደገደሉት የሱን ቦታ ተክቶ የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ በመሆን አሁንም ስልጣን ተደርቦለት የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ ሆኖ በሱ ቦታ ተሹሟል::

 

 1. ገዱ አንዳርጋቸው:- ሴረኛ አሳዳሚና አኩራፊ ነው ይሉታል:: ግለስቡ በወሎ ማሊያ የሚጫወት ቢሆንም ለውጡ እስኪመጣ እንደሱ የትህነግ አሽከር ሆኖ አማራውን የበደለ ሰው እንደሌለም ይነገራል:: “አማራው በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው”፣ “”የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል፣ ይህ ሕዝብ የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት” ሲል አማራን እወክላለሁ ብሎ ለሕወሃት ጋሻ ጃግሬ በመሆን አማራውን በአደባባይ ሲሰድብና ሲያዋርድ የኖረ ,የአማራውን ቅስም ለመስበር የተመለመለ ቅጥረኛ ባንዳ ፀረ-አማራ የአዴፓ አመራር አለምነው መኮንን የሚባል የመለስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት በስሩ ኮልኩሎ በአማራው ላይ ከሰራቸው ክህደቶች ጥቂቱን እንጥቀስ:: ገዱ ለሱዳን በተሰጠው መሬት በሀገር ክህደት ከሚጠየቁት በዋና ረድፍ የሚቀመጥ ነው:: በንፁሃን አማራዎች ሰቆቃ ግድያና ጥቃትም ፍርግ አደባባይ መቅረቡ አይቀሬ ነው:: የወሎን ህዝብ እወክላለሁ ብሎ በርካታ የወሎን መሬት ለትህነግ ያስረከበው ገዱ በተለይ በዋጃ ጉዳይ ተደጋግሞ ስሙ ይነሳል:: በአወዛጋቢዋ የዋጃ ወረዳ ላይ ሕወሃትም አዴፓም ውሳኔ ለመስጠት በተናጥል ስብሰባ ተቀመጡ:: ትህነግ ለአማራ ይገባዋል ብላ ወሰነች:: ገዱ ግን በራሱ ትዕዛዝ አለቆቹን ለማስደሰት ከህገመንግስቱ ውጪ ዋጃን ለሕወሃት አስረክቧታል:: ይህ ቆዳው የዋህ መሳይ መሰሪ ግለሰብ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ክልሉን ለማገልገል ሲመጣ እንደ አገኘሁ ተሻገር ሁሉ ጥርሱን ከነከሰባቸው የአዴፓ አመራሮች አንዱ ነበር:: በአጭር ጊዜ ውስጥ በመላው አማራ ማህበረሰብ ልብ ውስጥ መድጋቱን ሲያስተውል ከማይጋፋው ባላጋራ ጋር ትግል መግጠሙን ተገንዝቦ “እነ አሳምነው ከሱ ትዕዛዝ ውጪ እንደሚንቀሳቀሱ ክስ በማቅረብ አላሰራ አሉኝ የሚል ምክንያት ሰጥቶ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንትነት ስልጣኑን በፈቃዱ አስረከበ” አብይ በለውጡ ሰሞን ለስልጣን እንዲበቃ ላደረገለት ውለታም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን ሹመት ሰጥቶታል:: ግለሰቡ እነ ዶክተር አምባቸው ከመገደላቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ በስብሰባ ሰበብ ጀርመን እንዲሄድ ተደርጓል::

 

 1. ንጉሱ ጥላሁን :- ተወልዶ ያደገው አርሲ ውስጥ ሲሆን ጥሩ ኦሮምኛ ተናጋሪ መሆኑም ይነገርለታል:: ይህ ግለሰብ አማራው ላይ ሕወሃትም ሆነ ኦዴፓ ለፈፀሙት ጥቃቶች እና ግድያዎች እንዲሁ ጥንታዊ ርስቱን እንዲያጣ ለተደረገባቸው ወንጀሎች ሁሉ በተባባሪነት ከሚጠየቁት መካከል ዋናውና ቀንደኛው ነው:: የሕወሃት አስተዳደር ዘመኑን ክስተት ትተን ከለውጡ በኋላ በአማራው ላይ ለሚደርሱ መፈናቀሎች አረመኔያዊ ግድያዎች ጄኖሳይድና የአማራ ሴት ተማሪዎች እገታ ድራማ ላይ ሳይቀር የእነ አብይ አህመድ አስተዳደር እኩይ ገመና በአደባባይ እንዳይጋለጥ ተግቶ የሚሰራ ሞተ ለሆጉ አይነት ግለሰብ ነው:: በኦሮምያ ኦዴፓ የፀጥታ ኃይላት ቸልተኝነት እና በራሱ ኦዴፓ የተቀነባበረ ተንኮል የሚፈፀሙ ጥቃቶችንም “ሕወሃት, ለውጥ አደናቃፊና ያኮረፉ ኃይላት ናቸው” በሚሉ ተደጋጋሚ እና አሰልቹ ዲስኩሮች የኦዴፓን የጄኖሳይድ ጥቃት በማድበስበስ ላይ ይገኛል:: በአማራው ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎችን በቡራዩ በለገጣፎ በቦሌ ቡልቡላ በሰበታ እንዲሁም በኦሮምያ ልዩ ልዩ ወረዳዎች በህገወጥ ግንባታ ሰበብ አማሮች ለዘመናት ከኖሩበት ቤታቸው እየፈረሰ ሲፈናቀሉ ገዳዩን ከህገወጥነት ጋር በማያያዝ እንዲሁም ይጣራል በሚል ሰበብ ተዳፍኖ እንዲቀር ብዙ መሰሪ ተግባራትን ፈፅሟል:: በተደጋጋሚ አሰቃቂ ግድያ በኦሮምያ እና ትግራይ ክልሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚደርስባቸው የአማራ ክልል ተማሪዎች ወደነዚህ ክልል አንሄድም በማለታቸው “አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል ከክልል ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረናል” በሚል መግለጫ ከተጠለሉበት ባህርዳር በወታደርና ፖሊስ አስገድዶ በመላክ ዳግም የሞት ጭዳ እንዲሆኑ ያስደረገ ግለሰብ ነው:: አርሲ ተወልዶ አርሲ ያደገው ንጉሱ እወክለዋለሁ የሚለው አማራ ሳይሆን የኦሮሞ ተወካይ እስኪመስል በአርሲ የስም ዝርዝራቸው ተለይቶ የታረዱ አማሮችን ጉዳይ በተመለከተ መግለጫ ለመስጠት ድፍረት አጥሮት ተደብቆ ሰንብቷል:: በቤተሰቦቻቸው ፊት የታረዱ ነፍሰጡሮች ሕፃናት እና አርረጋውያንም ገዳይ እንደነ ንጉሱ ላለው እጁ በንፁሃን ደም ለተጨማለቀ ፀረ-አማራ ግለሰብ ምንም አይደለም:: አሳፋሪው ነገር ይህ ግለሰብና አገኘሁ እንግዳ ዓለም ያወገዘን ዘር እና ሃይማኖት ተኮር ጄኖሳይድ “የዘር ዕልቂት ነው” ቢያንስ እንወክለዋለን ብለው ከርሳቸውን የሚሞላላቸውን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ በአደባባይ ድርጊቱን አውግዘው ህገወጥ ተግባሩ እንዳይደገም ከመጣር ይልቅ “ኦዴፓ በአማራ እና አማርኛ ቋንቋ ላይ የጄኖሳይድ ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን” አቶ ሽመልስ በአደባባይ የተናገረውን ከባድ ወንጀል “የሽመልስ ንግግር የግለሰብ እንጂ የብፅግና አይደለም” ሲሉ መደመጣቸው ወደፊት በሚኖረው ዓለማቀፍ የሕግ ችሎት ሸምቀቆዋቸውን እንዳጠበቁ ሊያውቁት ይገባል:: እነዚህ ግለሰቦች ሽመልስ ያንን ከባድ ሚስጥር ያፈነዳው ለብቻው ሳይሆን የፌደራሉ የብልፅግና ጽህፈትቤት ሃላፊ የአሁኑ የኦሮምያ ብልፅግና ጽህፈቤት ሃላፊ ፈቃዱ ተሰማ እና የኦዴፓ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ብቂላ ሁሬሳ በጋራ በመሩት መድረክ የኦዴፓን እንቅስቃሴ የስራ ክንውንና ቀጣይ ዕቅድ ለአባገዳ ተወካዮች ለኦሮሞ ምሁራንና ለታዋቂ የኦሮሞ የግድ ማህበረሰብ አባላት በተዘጋጀ የጋራ ስምነት መድረክ መሆኑን ሳያውቁ ቀርተው ሳይሆን እነ ጄኔራል አሳምነው ጽጌን ዶክተር አምባቸው ምግባሩ ከበደና እዘዝ ዋሴ ሌሎችም የአማራ ወሳኝ ታጋዮች የተገደሉበትን ሴራ በእነ አብይ አህመድ አደራጅነት እና በእነሱ መግለጫ አቀናባሪነት በጋራ የተፈፀመ በመሆኑ ጉዳዩን ማስተባበላቸው ነው:: ሆኖም የፍየል ጭራ የቱንም ያህል ብትውተረተር ገመናዋን እንደማይሸፍነው እነ እነ ንጉሱ በውል ሊያውቁት ይገባል::

 

5.ሻለቃ ተመስገን ጥሩነህ:– አዊ ወይም አገው ወረዳ መወለዱ ነው የሚነገረው:: እነ ዶክተር አምባቸው በሴራ ከተገደሉ በኋላ የአማራ ክልልን እንዲያገለግል የተሾመ መሆኑን ሽመልስ አብዲሳ በግልፅ በአደባባይ ነግሮናል:: አብይ አህመድና ተመስገን በኢንፎርሜሽንና ደህንነት መስሪያ ቤት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ውስጥ ለረጅም ጊዜናት አብረው መስራታቸውና የቅርብ ወዳጆች መሆናቸው የሚታወቅ ነው:: የዚሁ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የነበረው ተመስገን አብይ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ከተቆናጠጠ በኋላ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ በመሆን እንዲያገለግል ሾሞታል:: ከአማራ ክልል አመራሮች ግድያ በኋላ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ተደርጎ በአብይ ትዕዛዝ ከተሾመመ ወዲህም በሰላም ማስከበር ስም በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የአማራው ጥቃይ ተከላካይ አርበኞች እንዲገደሉና ትጥቅ እንዲፈቱ አድርግል:: እራሳቸው እነ አብይ በፈጇቸው የአማራ ባለስልጣናት የወንጀል ገዳይ በርካታ የአማራ ታጋዮች ታስረው እንዲንገላቱ ከእነ ደመቀ እና ንጉሱ ጋር የቻለውን ያህል ተንቀሳቅሷል:: በኮረና ምክንያት የተጣለውን የጉዞ እገዳ አስታኮም የፋኖ ወጣቶችን እና የአርበኞችን እንቅስቃሴ ለማዳከም መከላከያ ሰራዊቱን አማራ ክልል ጎንደር ውስጥ አስገብቶ የቻለውን ያህል ጉዳት አድርሷል:: አሁን ላይ ግን በቃ ሊባል ይገባዋል::

 

ውድ ወገኖች! ኣብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ ምንም እንኳ በቀደመው የሕወሃት አስተዳደር እጁ በወንጀል እና በንፁሃን ደም የተጨማለቀ ቢሆንም ከኦሮሞው በላይ ጉሮ ወሸብዬ እልል ብሎ ቀድሞ በፍቅር የተቀበለው እውቅና የሰጠው የዘረኝነት ስሜት ያልፈጠረበት ሀገር ወዳዱ የአማራው ማህበረሰብ ነበር:: ይሁና ወርቅ ላበደረ ጠጠር እንዲሉ ባለፉት 2 ዓመታት በአማራው ጫንቃ ላይ ሰፍረው ለረጅም ጊዜያት ደሙን ሲመጡት ከኖሩት አዴፓ ከሚባሉት የለየላቸው ፀረ-አማራ ቡድን አባላት ጋር በማበር ይህ ደግ ማህበረሰብ በጄኖሳይድ እንዲፈጅ ቋንቋውም ጨርሶ እንዲጥፋና ሀገር አልባ እንዲሆን ወያኔ ከፈፀመው በላይ የግፍ ግፍ በኦሮምያ ክልል በቤኒሻንጉል እና አሁን ደግሞ በጋምቤላ ከፍተኛ ዘመቻ ውስጥ እንደሚገኙ ቢረፍድም ሽመልስ እንቅጩን ነግሮናል:: ዋና ተቀናቃኞችና የስልጣን ተገዳዳሪዎቹ እነ ዶክተር አምባቸው እንዲህ በፖለቲካ አሻጥር ከተገደሉ በኋላም የአብይ የቅርብ ወዳጅ ሻለቃ ተመስገን ጥሩነህ በአማራው ካባ ተሸፍነው አማራውን ኦዴፓ በሚፈልገው መንገድ እንዲዘውር መሾሙንም ሽመልስ አብዲሳ ሹክ ብሎናል:: የአማራ ክልል መፈንቅለ-መንግሥት ሲል አብይ አህመድ በደረሰው እና የሱ ሴክሬተርያት የአርሲው ተወላጅ ሲሳይ ንጉሱ በመገናኛ ብዙሃን በለፈፈው ተውኔት ሽመልስ አብዲሳ “አባይን ተሻግረን ባህርዳር ብዙ ሰርተናል። የቻልነውን አሳምነን ያልቻልነውን ግራ አጋብተን። አሁን የሚያስቸግረው ሌሎች ለምን ግራ ተጋቡ ብላችሁ ትጨነቃላችሁ። ምን አገባችሁ?” ሲል የአማራ ባለስልጣናትን ሴራ አፍረጥርጦ በአደባባይ አዝረክርኮታል:: እነ ንጉሱ እና አገኘሁ የሚውተረተሩት በጥቃቱ በተአምር ተረፍን ሲሉ ማቅ መስለውና ማቅ ለብሰው እንባና ንፍጣቸውን እያዘሩ አማራውን ለማሳመን በመገናኛ ብዙሃን እመኑን ድርጊቱ ሲፈፀም አይተናል በማለት በወንድሞቻቸው ደም ቁማር የተጫወቱትን እነ አብይ አሳምነው የወንጀሉ ተባባሪ ያደረጓቸውን አራቱ ግለሰቦች ማለትም ላቀ አያሌው ፣ ዮሃንስ ቧያለው ፣ አብርሃም አለህልኝና መላኩ አለበል ቅሌት የራሳቸውን ያደፈ የግፍ ታሪክና የኦዴፓን የዓመታት የክህደት ተግባር እንዲሁም የለየለት ፀረ-አማራ ስሜት ለመሸፋፈን ነው:: ታዲያ ይህን ስታዩ “ቪቫ ሽመልስ ! ዳውን ዳውን አዴፓ!” ማለት አያንሰውም ትላላችሁ:: ለሁሉም ብቸኛ መፍትሄው አማራ ነኝ የምትል ንቃ! በሬ ካራጁ ጋር ይውላል እንደሚባለው ተረት በጎጥና ብሄር ተከፋፍላ እንዲሁም በፖለቲካ ሴራ ተሸርባ በፈራረሰች ኢትዮጵያ ላይ ቆመን “አንድነት! አንድነት!” እያልን ስንዘምር ውሎ አድሮ ሀገር አልባ ሆነን እንዳንቀር ለቤተ አማራ ምስረታ ዘብ ብንቆም መካም ይመስለኛል:: ኢትዮጵያ ካለችበት ማጥ ወጥታ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ሃላፊነቱ እና ግዴታው የሁሉም ብሄር እንጂ የአማራ ብቻ አይመስለኝም:: ዛሬ እያንዳንዱ ብሄር የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል ስላሰጋው ነው የክልል እንሁን ጥያቄው እስኪፈፀም የፈራ ይመለስ በሚል መርህ ደሙን የሚያፈሰው:: አማራው ግን በአንድነት ስም ሰሚ አልባ የቁራ ጩኸቱን ሲጮህ ሽመልስ እንደነገረን በሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ ቀደምት የጎጃም ግዛት በነበረው እና ዛሬ ኦነግ ሼኔ አማራውን በሚያሳድድበት ቤኒሻንጉል ክልል ሳይቀር ከ 37 በመቶ በላይ ኦሮምኛ ተናጋሪ ማድረጋቸውን ልብ ይሏል :: ወደፊት ወያኔ አማራውን ለመጉዳት እንዲሁም በመስኖ እና አሳ እርባታ ትግራይ ተጠቃሚ እንድትሆን በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር ከስክሶ የአባይን የውሃ ፍሰት በማስቀየር እዛው ቤነሻንጉል ጉባ ወረዳ ውስጥ የገነባውን የህዳሴው ግድብ የኬኛ ፖለቲካ አራማጆች ” አባይ ኬኛ!” የሚሉበት ቀን አይመጣም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነውና ዝንጀሮ መቀመጫዬን እንዳለችው መሰረታዊ የአማራው ጠላት በሆኑት አዴፓ ሕወሓት ኦዴፓ እና ኦነግ ላይ ትኩረታችንን ሳናዞር የራሳችን ሕዝብ ደህንነት እና የግዛት መሬታችን ሕልውና ላይ ሳንውል ሳናድር ብንረባረብ መልካም ነው እላለሁ::

 

ቻኪሳው የበለሳው

8 Comments

 1. ዋው ቻኪሳው የብለሳው አይነት ቆራጥ አማራ ስላለ አማራ ምንም አይሆንም:: ማፈሪያ :: ይህን በየጠላቤት የለቃቀምከውን ሀሜት እዚህ የመፃፍ እድል አገኘህ የወያኔ አለቅላቂ:: ንጉሱ ጥላሁን አርሲ ስለተወለደና አፋን ኦሮሞን ስለተናገረ በአንተ ሚጢጢ ጭንቅላት ሙሉ አማራ አይደለም?
  የአማራ እንቅፋት የሆነው የአማርኛ ቋንቋ ሆኗዋል:: የአማራን አንድነት የማይፈልጉ ጠላቶች በዚህ ቋንቋ ይገለገሉበታል

  • እውነቱ የምትባል ሰው ወይ የግንዛቤ ችግር አለብህ አማራውን ለመታደግ እንዲህ ያለ ጠንከር ያለ ጽሁፍ ሲወጣ እንድትሳደብ ዳረጎት የተሰጠህ ወይም ደግሞ ያስተሳሰብ ችግርና ተከፋይ ልትሆንም ትችላለህ።
   በተለይም በአማራው ሰቆቃ ነብስህ ሀሴት ከሚያደርጉት መሀል አንዱ ነህ። የስድብህ ግምባር ቀደም ተጠቂዎች የአማራን ጉዳይ የሚያነሱት ናቸው የድፍረትህ ድፍረትና ያላዋቂነትህ ጥግ መንካት የሚታየው ደግሞ እነ አቻምየለህንና የከባድ ሚዛን ተጋጣሚዎችን መስደብህ ነው። የሚገርመው ሁሉንም የምትሰድባቸው ጽሁፋቸው ገብቶህ ሳይሆን ስማቸውን አይተህ ነው። ይመችህ በርትተህ ተሳደብ ካልተሳደብክ ፈንድተህ ልትሞት ትችላለህ እንዴት ያለ ክፉ አመል ነው።

 2. እውነቱ፡

  ከነስምህ በሃሰት የተሞላህ አድርባይ ነህ፡፡ ንጉሱ የሚባለው ዝፍዝፍ ባንዳ የአሩሲ አማራ ከሆነ ለምን የሞቱትን አማራዎች ነብስ ይማር አላለም? ዝምብከህ እንደ ዝምብ ወተት ጥልቅ ከማለትህ በፊት ፖለትካው ይግባህ፡፡ ፀሃፊው ስለንጉሱ ባንዳው ሳይሆን የሚያወራው ተቆርቋሪ መሪ ስላጣው የአማራ ህዝብ ነው፡፡

 3. So enlightening! This is the whole fact about ADP and ODP. But there is one factual error, dear writer. That is the number of people (Tutsis) who died by the Hutus’ genocide was 800000, not 100000. The rest, so fine! And please send this piece to different youtubes including zehabesha.com youtube.
  And readers like Semere, please don’t waste your time in answering something to people like so called Ewunetu who are digital OPDs or Woyanes. Such people survive by reacting to such big realities that bring about change in the thinking of the mass.

 4. አሽቃባጭ አማርኛ ተናጋሪ ወያኔዎች::እኔ ማንም ሀይል ምንም ሊከፍለኝ የማይችል ለህሊናዬ ያደርኩ የአማራ ልጅ ነኝ ሆኖም ኢትዮጵያዊነት ከአማራ ኦሮሞ ከሁሉም በላይ እምነቴ ነው:: የወያኔን እባብነትና አስመሳይነት አውቀዋለሁ:: በአማራ ስም በአማራ ዋቢነት በኦሮሞና አማራ መካከል መርዝ እየረጩ ህውሀትን እንደገና ለማንገስ የሚደረገውን እሩጫ ጠንቅቄ አውቃለሁ:: ሰመረ የተባልክ ደካማ ሰው እኔ ወደአንተ ወርጄ አፍ ለመካፈት ደረጃዬ አይፈቅድም:: አማራውን እየገዘገዛችሁ መሪ አሳጥታችሁ ለወያኔ መጫወቻ የምታደርጉትን ዘመቻ ህፃን ማሞኘት አይቻልም:: ዛሬ አዴፓና አብን እየተናበቡ ይሰራሉ ቀሽሞች!

  • ከከከ እውነቱ መሪ ገዱ ነው ደመቀ ወይስ ንጉሱ ወይስ ዳግማዊት? መሪውንማ አሳምነውን አስበላኸው። ምን አደረቀኝ ካንተ ጋር አንተ ትከፍሎህ ነው እኔ ጄኖሳይድ ቀንስኩ ብዬ ነው በተለያየ መስመር ሁነን ነው ለሀገር ተቆርቋሪዋችን አትሰደብ ማለት አትስራ ማለት ነው። ጨርግዳቸው ይመችህ

 5. You wrote Some Tigrayan scholars and Emperor Menelik, who were on fire after the Axumite dynasty’s transfer from Tigray to Shoa Menelik, set fire to it. This sentence is wrong. Historian Haile Larebo wrote that the Axumites were not Tigreians. You may say the Tigres were unhappy because of the transfer of power from Atse Yohannes to Atse Minilik.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.