"ዘንግህን ማወዛወዝ ትችላለህ፡፡አፍንጫየየን መንካት ግን አትችልም፡፡" መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

“ዘንግህን ማወዛወዝ ትችላለህ፡፡አፍንጫየየን መንካት ግን አትችልም፡፡” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

1 min read

“ዘንግህን ማወዛወዝ ትችላለህ፡፡አፍንጫየየን መንካት ግን አትችልም፡፡”

ዴሞክራሲ ይላል፡፡

እኔም፣እላለሁ!

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

  Do you remember;he went on writing  in your diary, ‘Freedom is the freedom to say that two plus two make four?’ ‘Yes,’ said Winston.

  O’Brien held up his left hand, its back towards Winston, with the thumb hidden and the four fingers extended.

  ‘How many fingers am I holding up, Winston?’ ‘Four.’ ‘And if the party says that it is not four but five ;then how many?’

   1984 በተሰኘው በጆርጅ ኦርዌል መፅሐፍ፣ የቢግ ብራዘርን ርእዮት የሚከተሉ ገዢ መደቦች፣ በብዙሃኑ ላይ ሙሉ ቁጥጥር ለማሥፈን፣ NEWSPEAK (ኒው እሥፒክ) ወይም አዲስ ቋንቋ በተከታታይ ቅፅ ፈለሰፉ። የቀድሞዎቹ የተንዛንዙ ና ኋላ ቀሮች ናቸው በማለት ፈረጁ። ይህንንም ያደረጉት የብዙሃኑን ሥሜት በቀላሉ ለመረዳት ነው። እግረ መንገዳቸውንም ሰዎች ግራ እንዲጋቡ ና በአንድ አእምሮ ሁለት አሥተሳሰብችን እንዲያሥቡ ወይም  DOUBLE THINKER እንዲሆኑ ጫና ለማድረግም ነው፣ አዲሱን ቋንቋ የፈጠሩት። በአዲሱ ቋንቋ እና “በደብል ቲንክ” መርህ ፣ ሁለት ሲደመር ሁለት አራት መሆኑንን እያወቅህ፣ ፖርቲው ካዘዘህ አምሥት መሆኑን አምነህ ትቀበላለህ። ( ዌንሥተን ከቢግ ብራዘር ተቃራኒ የሆነ አሥተሳሰብ ያለው ሲሆን በግድ (በቶርቸር )2+2=5 ነው። እንዲል ተገዷል።)

 ይህ አሥተሳሰብ በዛሬዋ ዓለም መንግሥታት ውሥጥ የለም። በማለት አፋችንን ሞልተን የመናገር ግዴታ እኛ የማይከፈለን ፀሐፍያን የለብንም።(…)

   ይሁን እንጂ፣ የራሳቸውን የፖርቲ የሰው ስብሥብነት ዘንግተው፣ ተሰብስበው ፓርቲ ያደረጓቸውንም ሰዎች የመለአክትን ፍፁምነት አጎናፅፈው፣ ህዝብን እንደተራ እና መሃይም አማኝ በመቁጠር፣ ሥለ ፃድቅነታቸው፣ ዘወትር በሚቆጣጠሩት ሚዲያ አማካኝነት የሚነግሩን አሉ። ሳይወዱ በግድ ወይም ለእንጀራ የትልቁ ወንድም ታዛዦች የሆኑ ጋዜጠኞች እዛና እዚህ ነጭ ፐሮፖጋንዳን ዘወትር ይነዛሉ።አርግጥ ነው መሰል ጋዜጠኞች በአሜሪካ፣ በሩሲያ ፣በቻይና፣ በጀርመን፣ በእንግሊዝ፣በኢጣሊያ፣በፈረንሳይ በብራዚል፤  በደቡብ አፍሪካ፣ በዙምባብዌ፣ በኬኒያ፣በጋና፣የሉም ማለት አይቻልም፡፡(ማንም የሚበላበትን ወጪት ሊሰብር አይችልም፡፡ ትላንትም ለእንጀራ ያደሩ ጋዜጠኞች ነበሩ።ዛሬም መሠል ጋዜጠኞች የትም አሉ።…

   የበሉበትን ወጪት ካለመስበር አንፃር ፣ ታሪክን ለመዝለል፣ የሚያሥገድድ ሥራ በዋነኝነት መንግሥታት ቢሠሩም፣ በየትም ሀገር እውነት እንድትቀበር ተደጋጋሚ ፕሮፖጋንዳ የሚነዙት የመንግሥትን እንጀራ የሚበሉ ጋዜጠኞች ናቸው።በትረ ሥልጣኑን የጨበጠውን የማገልገል እና የልብ ትርታውንም የማዳመጥ ኃላፊነትም አለባቸው።

ለምሳሌ፣ የንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን የልብ ትርታ በማወቃቸው ነበር የእቴጌ ዘውዲቱ ምኒልክን፣ ንግሥና ከአፄ ኃይለሥላሴ ንግሥና በኋላ ያላወሩት። ታሪካቸውም ገዝፎ ያልተነገረውና ለትውልዱ ያልተላለፈው በዚህ ምክንያትም ነበር። በኢትዮጵያ ታሪክ ሴት ንግሥት መሪ ነበረን “ንግሥተ ነገሥታት “(እቴጌ )።ይህ ሁላችንም ልንኮራበት የሚገባን ታሪክ ነው።(1916 –1930 እኤአ) ተፈሪ መኮንን፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት የተባሉት ከእቴጌ ዘውዲቱ በኋላ ነበር።

Zewditu (also spelled  Zeoditu  or  Zawditu  or Zauditu or Zäwditu; Ge’ez: ዘውዲቱ; born Askala Maryam; 29 April 1876 – 2 April 1930) was Empress of Ethiopia from 1916 to 1930. The first female head of an internationally recognized country in Africa in the 19th and 20th centuries, and the first empress regnant of the Ethiopian Empire, her reign was noted for the reforms of her Regent and designated heir Ras Tafari Makonnen (who succeeded her as Emperor Haile Selassie I), about which she was at best ambivalent and often stridently opposed, due to her staunch conservatism and strong religious devotion. As of 2020 she is the most recent empress  regnant in history.

( Zewditu Nigiste Negestatt Empress of Ethiopia Reign 27 September 1916 – 2 April 1930  )

 ጋዜጠኞችን በጭፍን ለማውገዝ አልዳዳም፡፡በዓለም እጅግ ተዳቂ ጋዜጠኞች ነበሩ፡፡ዛሬም አሉ፡፡ በጋዜጠኝነት ሙያ፣ የተሠማሩ፣ ምሥጉን፣ እውነተኛ፣ ግለሰቦች ይህቺ ዓለም ዛሬ ከደረሰችበት የሥልጣኔ ደረጃ እንዴት እንደደረሰች እና በዓለም ላይ የሚታየው የኑሮ ደረጃ ለምን የሰማይና የምድርን ያህል እንደተራራቀ፣ በተለያየ ጊዜ ፣ገንቢና አስተማሪ ፅሁፋቸውን አቅርበዋል። አያሌ ዶከመንተሪ ፊልሞችንም ሠርተው ዓለምን አንቅተዋል፣አስተምረዋል፣አስጠንቅቀዋል፡፡ዛሬም ይህንን በጎ ሥራቸውን ለአለም ህዝብ እያቀረቡ ነው።

   በፅሑፋቸው ና በዘጋቢ ፊልማቸው፣ ዓለማችን ዛሬ ከደረሰችበት ሥልጣኔ ላይ እንዴት ደረሰች? የማንም ግል ንብረት ያልነበረችው ዓለም ዛሬ፣ በጥቂት አህጉራት እና በብዙ ሀገሮች እንዴት ለመከፋፈል በቃች ?የሰዎች መግባባያ ቋንቋ እንዴት በሺ የሚቆጠር ሆነ?…ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችን አንሥተው፣ አወያይ ሃሳችን በሰው ልብ ውሥጥ የጫሩትን ሣይንቲስቶችን ሥራ ከሽነው አቅርበዋል ። የሰው ልጅ አፈጣጠር አንድ መሆኑን አንባቢ ና ተመልካች እንዲገነዘብ አድርገዋል።ዓለም ዛሬ ከደረሰችበት የሥልጣኔ ከፍታ ላይ እንዴት ደረሰች? ብለው በመጠየቅ መልሱን ከተመራመሪዎቹ እና ከአሳቢዎቹ እንድሰማም አድርገዋል።

እኔም፣እላለሁ!

 ዓለም ዛሬ በሚደንቅ የሥልጣኔ ከፍታ ላይ ተቀምጣ ያገኘናት እንዲሁ፣ በዋዛና በፈዛዛ አይደለም። ጥቂት የማይባሉ ተመራማሪዎች ፣ሀገር አሳሾች ፣ነፍጠኞች፣ የጉልበት ሠራተኞች ወዘተ። ለዚች ዓለም ዘመናዊነት ውድ ህይወታቸውን ከፍለው ነው። እንዲህ ላለ እፁብ ድንቅ ሥልጣኔ ያደረሷት።

  ዓለም በኢሲያ፣ በአውሮጳ ፣በአሜሪካ እና በአረቡ ሀገር ዓለም በሥልጣኔ እንዲህ የዘመነችው፣ ያለእረፍት በሚሠሩ እና የፈጠራ ችሎታቸውን በብዙ ውጣ ውረድ እውን እንዲሆን ባደረጉ፣ ጥቂት ታታሪ የፈጠራ ሰዎች ነው። …በተጨማሪም፣ ዓለም ሥትፈጠር የሁለት ተቃራኒ ፆታዎች ባለቤት ሆና ሳለ፣ ዛሬ ሰው በመዋለድ ተባዝቶ ምድርን ሥለሞለት እንዴት ሰው በነገድ፣ በቋንቋ፣ በኃይማኖት ሊለያይ ቻለ? ብለው በመጠየቅ ጥቂት አሳቢዎችም  መልሥ ሰጥተዋል።ታሪክ እና እውነት እንደሚመሠክሩት፣ ዓለም ሥትፈጠር የሁሉም ሰው ነበረች። ሰው የምንለውም ወንድ እና ሴት ሆኖ የተፈጠረ ነው። ዘሩ እየተባዛ ሲሄድ ግን የምግብ ፍላጎቱን ለማሟላት በሚያደርገው እንቅሥቃሴ ከሰፈረበት ቦታ እየረቃ ሲሄድ ለኑሮ የተሻለ አካባቢ በመመልከቱ፣ ጥቂቱ መሠል ቤተሠቡን ይዞ ወደቃኘው ሥፍራ በመሄድ ኑሮውን በዛው መሠረተ። እንዲህ፣ እንዲህ እያለ፣ ሰው ልጅ፣ በዓለም ዙሪያ ሁሉ ሊገኝ ቻለ። እየተዋለደ ሲበዛም ለመኖር አሥቸጋሪ የሆነ የምግብ እጥረት አጋጠመው። በዛ ላይ የሚኖርበት አካባቢ ኑሮውን አከበደበት። እልፍ በማለት እልፍ ይገኛል። …”ብሎ አመነ። የእንጨት ጀልባ ሰርቶም ሌላ ሥፍራ ማሰስ ጀመረ።

የመርከብ መሥራት ፈጠራውን በተፈጥሮ አሥገዳጅነት ቀስ በቀሰ በማሻሻል፣ በእጨት የሚቀዘፍ ትልቅ መርከብ ወደ መሥራት አሳደገ። ካለበትም አካባቢ ከባህሩ ባሻገር ያለውንም ውብ ጠፈጥሮ  ለማየት ጓጓ። ሥለ ምድር ክብነት ለማረጋገጥም ተመኘ። ምድር ክብ ከሆነች በአንድ አቅጣጫ ተጉዞ በሌላው አቅጣጫ ወደ ተነሣበት እንደሚመለሥ በመረዳቱ ዓለምን ለመዞር ተነሳ። በመጨረሻም ዓለምን ዞሮ ክብነቷ ንአረጋገጠ።

የዓለምን ክብነት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ ሰው ገና ብዙ ያልኖረበት ሆኖም በተፈጥሮ ሀብቱ ማራኪ የሆነ መሬት እንዳለ አረጋገጠ። እናም ለሰው የሚመች ሥፍራ አሳሾች፣ በአውሥትራሊያ፣ በአሜሪካ ፣በኢሲያ፣ በአውሮጳ፣ በአፍሪካ ፣በሁለቱ ዋልታዎች ተጉዘው ለሰው ኑሮ የሚመቸውን የምድር ሥፍራ ና የማይመቸውን ሥፍራ ለዩ። እናም በተመቻቸው ሥፍራ የራሳቸውን ሰው አምጥተው አሠፈሩ።የባርያ ንግዱን አትዘንጉ፡፡

በነገራችን ላይ፣ ከዚ በፊት ግን ዓለም በሰባቱ አህጉራት ከመከፈሎ በፊት ታላላቅ ወንዞች ብቻ ያላት እንደነበረች ይታመናል። ሰዎች እዛና እዚህ እየኖሩ ዓለም በተፈጥሮ አሥገዳጅነት ወይም ከሰማይ በወደቀ አሥትሮኖይድ አማካኝነት ሰባት ቦታ ለመከፋፈል በቅታለች። ተብሎ ይገመታል።ይህ ክሥተት ደግሞ በወቅቱ የነበሩትን አንድ ቤተሰቦች ሊለያያቸው ችሏል። እናም በየአህጉሩ ተነጣጥለው እንዲኖሩ የተገደዱት በሚኖሩበት አየር ፀባይ አሥገዳጅነት የቆዳ መጥቆርና መንጣት አጋጥሟቸዋል። ይህ ብቻ አይደለም፣ ምናልባትም ጥቁር ቆዳ ያላቸው፣ ነጭ ቆዳ ካላቸው ጋር እንዲዳቀሉ፣ አሥገድዶዷቸውም ሊሆን ይችላል።

ድንገተኛ ፍንዳታው ና የፈጠረው ዘግናኝ ጥፋት ፣ባሥከተለባቸው ሽብር ፣በወቅቱ ከፍተኛ ጭንቀት ውሥጥ ገብተው እንደነበረ መገመት ይቻላል። ከዛ ጭንቀት ቀስ በቀሥ ሲያገግሙ እና ወደቀልባቸው ሲመለሱ ራሳቸውን ያገኙት በሌላ ሥፍራ እና ሰዎች መሐል ነበር። ወይም ደግሞ ፣ከቶም የማይተዋወቁ ህፃናት በማያውቁት ሥፍራ ያ  ክሥተት አገናኝቷቸው ይሆናል።

ይህ ክሥተት የሚፈጥረውን ምሥቅልቅል ሥሜትና ግራ መጋባት የዛን ጊዜ ሰው እንጂ፣ የዛሬው ሰው፣ ሊረዳው አይችልም። ያም ሆነ ይህ ህይወት ትቀጥላለች።ከመከራ ፣ከሥቃይ፣ ከሰቆቃም በኋላ ህይወት መቀጠሏ አይቀርም። ሰው ልጅ ለመኖር ሲል ከአውሬ ጋርም ቢሆን ተላምዶ መኖሩ ግድ እንደሆነ የተገነዘበው ያኔ ነው። ያሳለፈው መከራ፣ እንግልትና ሥቃይ በቃላት ለማሥረዳት የሚከብድ ነበርና።

  ዛሬ ያላመዳቸው እና ቤተሰቡ ያደረጋቸው እንሥሣት እንኳን ትላንት አውሬ ነበሩ።ይህን ሥናሥተውል ሰው የመጣበት መንገድ ምን ያህል በመከራ የተሞ ላ እንደነበር እንገነዘባለን።የዛን ግዜው ሰው፣ መሠረታዊ ፍላጎቶች የሚባሉትን በማያውቅበት ዘመን፣ሰው፣ ከአውሬ እኩል አውሬ ሆኖ በሚኖርበት ዘመን ይህ ዘግናኝ የመሬት መሠነጣጠቅ እና አያሌ የተፈጥሮ ውድመት ተከሥቷል። የቋንቋ ብዝሃነትም አፈጣጠር ፣ከማይተዋወቁ ነገዶች መደባላለቅ ጋር የተገናኘ ነው።

እኔም፣እላለሁ!

   ቋንቋ ሊፈጠር የቻለው ሰው ልጅ በመዋለድ በመብዛቱ እና ፣አንዱ ከሌላው ጋር ለመግባባት እና ድርጊቶችን ለመፈፀም ከደመነፍሳዊ መግባባት ውጪ በአንደበቱ ቃለቶችን ያወጣ ሥለነበር እነዛ የተለያዩ ቃላቶች፣ ከወቅታዊው ድርጊት ጋራ በማገናዘብ ሥያሜ እየሰጠ የሚግባባበትን ቃላት በመፍጠሩ ነው።

ከላይ ከጠቀሥኩት ሃሳብ ጋር ፣ይህንን የቋንቋ ጅማሮ እና ክፍፍል ጋር፣ አቆራኝታችሁ እውነቱን ተገንዘቡ። ከሰማይ በወረደች ቁራጭ የእሳት አሎሎ ምድር ሥትመታ (ወደፊትም በእሳት አሎሎ እንደምትመታ፣ የሥነከዋክብት ተመራማሪዎች ያምናሉ።የዛሬዎቼ ተራ ሟቾች   ብታምኑም ባታምኑም ወደ ምድር ምውሐር የቀረቡ፣ በብዙ መቶ ቶን ክብደት ያላቸው፣ አያሌ የእሳት አሎሎዎች አሉ። ለምድር የሚያሰጉም በጣት የሚቆጠሩ አሉባቸው። በምድር ዙሪያ በሚሊዮን ኪ/ሚ ርቀት ላይ እየተምዘገዘጉ ነው። መቼ ወደ መሬት ሊቃረቡ እንደሚችሉ የታወቁ ጥቂቶች አሉ።መሬትን ድንገት ሳት ብሏቸው ከመቷት ደግሞ ሰውን ጨምሮ በምድር ያለ ፍጡር ሊያጠፋ ይችላል።)

   However, this asteroid poses no threat to Earth.While the chances of a major asteroid hitting Earth are small – NASA believes there is a one in 300,000 chance every year that a space rock which could cause regional damage will hit – the devastating prospect is not impossible.

እኔም፣እላለሁ

የትላንት “ወላጆቻችን ” ይህ ድንገተኛ አደጋ ተከሥቶ፣ በተፈጥሮ አሥገዳጅነት እዚህ ዓለም ከመምጣታቸው በፊት የሚግባቡበት የራሴ የሚሉት ቋንቋ ነበራቸው። ይኽ ቋንቋ ግን ፣ከተቀላቀሉት ጎሳ፣ ነገድ ወይም ዘር ጋር ሥለ ማያግባባቸው፣ ሌላ ሦሥተኛ የሚያሥማማ የተዳቀለ ቋንቋ መፍጠር ግድ ሆኖባቸዋል። እናም በየአህጉሩ የተለያየ ቋንቋ ፈጠሩ። ያም ቋንቋ ዛሬ በየሀገሩ ሥያሜ አገኘ። (እንግሊዝኛ፣ ማንዳሪን፣ ላቲን ፣ፈረንሳይኛ ፣አረብኛ፣ ጣሊያንኛ ፣መሥኮብኛ፣ ሢኋሊኛ፣ ግእዝ እንዲሁም የግእዝ ልጆች አማርኛ ና ትግሪኛ …እየተባለ።)

 ልብ በሉ፣ ይህ ሊከሰት የሚችል እውነት ነው :: ዓለም ዛሬ ወይም ነገ ትጠፋለች።በዚህ ሰፊ ህዋዊ ዓለም ዛሬ፣ ወይም ነገ ምን እንደሚከሰት አናውቅም። በበኩሌ ትላንት አያሌ ከቋጥኝ የሚገዝፉ የእሳት አሎሎዎች በፈጣሪ ኪነጥበብ በሰማይ ላይ፣ ምድርን እየታከኩ ለአያሌ ዓመታት ምድርን ሳይነኩ ማለፋቸውን አምናለሁ። ዛሬ ደግሞ ምድር ላይ የማይወድቁበት ምክንያት እንደሌለ ና ይታወቃል፡፡ቢያነስ ለተመራማሪዎቹ ።(ከላይ በእንግሊዘኛ የተጠቀሰው ይህ እውነት ነው።) ይሁን እንጂ ሞትን ይዘው የሚመጡትን የእሳት አሎሎዎች ሞተን አንጠብቃቸውም። እየኖርን ነው፣የምንጠብቃቸው።ቶሎ ቶሎ ብለን ሥራችንን ለመጨረሥ እየታገልን እንጠብቃቸዋለን።ሞት ሲመጣ ይመጣል፡፡ሥለማናስቀረው በፍርሃት ሺ ጊዜ ሞተን አንጠብቀውም፡፡

  ከእኛ የሚጠበቀው ሥራ ምንድነው? ከእኛ      የሚጠበቀው ሥራ በተሠጠን መክሊት ተጠቅመን ፍሬ ማፍራት ነው። ይህንንም እያደረግን ከሆነ ለእሳት አሎሎው እብዛም አንጨነቅም። እሱ ሲመጣ ይመጣል። አሁን ሥለሱ የምንጨነቅበት ወቅት አይደለም። ጨለማ  በበርሃን እየሠራን ሳለ በሰዓቱ እንደሚመጣ እንዲሁ የእሳት አሎሎውም በሰዓቱ ይመጣል።ወዳጄ ፣ሞትህን በጭንቀትህ አታሰቀረውም ፣ታዲያ ምን ያሥጨንቅሃል?

  ምንያ ሥጨንቀናል? ኢትዮጵያዊው ሰው፣ሳይጨናነቅ ሰውነቱን አውቆ እንዲኖር በፅሑፊ ሁሉ ጥሬያለሁ።ነገ በእሳት አሎሎ ለምትጠፋ ዓለም ፣ዛሬ በሥግብግብነት ተነሥቶ ኃይማኖትን እና ፖለታካን ምሽግ አድርጎ ወንድምና እህቱን መቆሚያና መቀመጫ ማሣጣት የለበትም። እንዲህ አይነቱን አጥፊ ሃሳብ በህዝብ ውሥጥ የሚዘሩትን ፖለቲከኞችም ሆነ አክራሪ ኃይማኖተኞችን መንግሥት መታገሥ የለበትም፣በማለት ወትውቻለሁ። በፅሑፊ ሁሉ፣ ሰው ሰው እንጂ ቋንቋ አይደለም ብያለሁ። ሰው ሰው መሆኑን፣ ቋንቋ መግባብያ እንደሆነ እንዲገነዘብ ደጋግሜ ፅፊለሁ።አማራ፣ ትግሬ፣ኦሮሞ ፣ሱማሌ፣ ወላይታ፣ሲዳማ፣ቤንሻጉል፣አፋር፣ሐረሬ፣ጋቤላ፣ወዘተ ::የሚባል ሰው የለም።…

  ከዚህ እውነት ተነስቼ አንድ ሰው፣ የሆነ ቋንቋ በመናገሩ ሰው መሆኑን ክዶ “እኔ ቋንቋ ነኝ፡፡” በማለት በዛ ቋንቋ ሥም ሥያሜ ማግኘት የለበትም በማለትም ደጋግሜ ፅፌያለሁ።ሰው ነው እንጂ ቋንቋ ባለመሆኑ፣ እንግሊዘኛ ሥለ ተናገረ ሰው መሆኑ ቀርቶ እንግሊዝ ሊሆን አይችልም። አሜሪካዊው የሚናገረው እንግሊዘኛ ነው።ያ  አሜሪካዊ እንግሊዝኛ በመናገሩ “እንግሊዝ “ሊባል ነውን?ኬኒያዊውስ? ጋናዊውሥ? የደቡብ አፍሪካ ተወላጁስ?…እንጊሊዝኛ በመናገሩ ብቻ “እንጊሊዚ” ሊባል ነውን?

  በሰለጠነው ዓለም ሆነ በመሰልጠን ላይ ባለው ሀገር የሰው መጠሪያ ሰው ነው። ቻይና እና መሥኮብም ሂድ፣ ሰው ሰው ነው። ቻይናዊ ና ሩሲያዊ ዜግነት ያለው ሰው።

በእኛ ሀገር ግን፣ ጎሳና ነገድ የጥቂቶች ሥልጣን ማግኛ እና መበዝበዣ መሣሪያ በመሆኑ ምክንያት ባለፉት 29 ዓመታት ሰው በሰውነቱ እንዳይጠራ ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ እና ከታረክ መማር የማይፈልጉ፣በሆዳቸው የሚያሰቡ ፓርቲ ነን ብለው ስንት ሰው እንኳን እንደወከላቸው የማይታወቁ ፣እንደ ዘመነ መሳፍነት ከዛና ከዚህ ባገኙት መሳርያና በእንጀራ ጠርንፈው  በያዙት ነፍጥ አንጋቢ በመመካት ሰውነታቸውን ዘንግተው ፣”ሰው ማለት ቋንቋ ነው ከቋንቋ ጋር ብቻ ተጋቡ፣ለቋንቋ ብቻ አድሉ፡፡ቋንቋችሁን የሚናገር ብቻ አቅርቡ፡፡ከቋንቋችሁ ጋርም ዝረፉ፡፡”በማለት ዛሬም ይሰብካሉ፡፡

ከዚህ የቋንቋ ፖለቲካ ለመውጣት እየታገሉ ያሉት ጥቀት ፓርቲዎች ብቻ ናቸው።  የብልፅግና ፓረቲም ዋናው ለውጥ ፈላጊ ነወ፡፡ የብልፅግናን የ21ኛው ከፍለ ዘመን የማይፈልገው ደችሞ ቢገ ብራዘር ነው፡፡ትልቁ ወንድም፣ወይም ወንድ ጋሼ፡፡

የአፄ ቴዎድሮስ የቀደመ አሥተሳሰብ በዘመኑ ኋላቀር አሥተሳሰብ እና ጥቅመኞች እንደተደናቀፈ ሁሉ፣ ይህም የለውጥ ጅማሮ ለሥልጣን እና ለሆድ እንጂ ለህዝብ ብልፅግና ደንታ በሌላቸው እንዳይደናቀፍ እሰጋለሁ።የብልፅግና ፓርቲ መሪው ክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ(ዶ/ር) በብዙ ንግግራቸው፣”በኢትዮጵያ፣ብልፅግናን ለማምጣት፣ዴሞክራሲን ማስፍን እና ሰባአዊ መብትን ማረጋገጥ እነደሚያስፈልግ…”ደጋግመው አስገንዝበዋል፡፡ይሁን እንጂ ዴሞክራሲ ማለት ” ዘንገህን አወዛውዝ ሆኖም የወንድምህን ወይም የእህትን አፍንጫ በምንም ምክንያትና ሰበብ መምታት አትችልም፡፡” ማለት እነደሆነ  ዛሬም በውል ያልተገነዘቡ ህግ አውጪዎች፣ ህግ ተርጎሚዎችና  አስፈፃሚዎች አሉ፡፡ዛሬም ለሥልጣናቸው ብዙሃኑን መሰዋት ለማስከፈል  ከሰውነት ይልቅ፣የባህል አንድ ክፍል የሆነውን ቋንቋን አግዝፈው በማሳየት እና የመለውን ዜጋ ሰውነት በለመቀበል “ቡከን ጦር አውርድ!” በማለት ሴጣንን የሚለማመኑ አሉ፡፡አረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ባንዲራ ፣ትላንት ሰንደቅ እነዳልነበረ ሁሉ ዛሬ በጠላትነት ተፈርጆ በአንዳንድ ክልል ፖሊሶች የቡከን ጦር አውርድ መገለጫ መሆን አልነበረበትም፡፡ከላይ እንዳልኩት ዜጎች እንዳአቅሚት የያዙትን ልምጪም ሆነ ዘንግ የማወዛወዝ መብት አላቸው፡፡ሆኖም ግን የማንንም አፍንጫ መንካት አይፈቀድላቸውም፡፡ያ ቀዩን መስመር መጣስ ነውና፣ በህግ ያስጠይቃቸዋል፡፡ በደምሳሳው የለውጡ መልካም ግስጋሴ፣ዛሬ ለእነጀራው ሲል በሚጠብቃቸው ዜጋ በመመካት (ሰው ነውና ነገ እውነትን በመገንዘብ እነደሚከዳቸው ዘንግተው፡፡) ነገ በተፈጥሯዊ ሞት ራቁታቸውን መሄዳቸውን ዘንግተው፣ከሞቱ በኋላ ተውልዱ እንደሚያዝንባቸውም በቅጡ ባለመገንዘብ፣ቅን በሆነው በለውጥ መሪ ላይ  የአደጋ ሥጋት ተደቅነውበታል፡፡መንግስታዊው  ሥርዓት በተሟላ መልኩ፣ፌደራላዊ ና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የሚያደርገውንም ጥረት በእንቅፋት አየሞሉት ነው፡፡ ቋንቋዊነት ና ሴረኝነትን ያደመቀ ፣ በከፋፍለህ ግዛ የሚመራ መንግሥት ሲመሩ ለ27 ዓመት በመዝለቃቸው በብዙሃኑ ቅቡልነት እንዳልነበረው ግን አሳምረው ያውቃሉ።ሆኖም ግን ዛሬም ከታላቁ የምፅአት ቀን በፊት፣ ከትልቁ ወንድም ፖለቲካ ይህቺ ሀገር እንድትላቀቅ አይፈልጉም፡፡ እናም በጊዜ እነዚን ከእኩይ ድርጊታቸው ለመማር ያልፈለጉ፣ሆኖም ግን ፍቅር በሆነው በትግራይ ህዝብ ጉያ ተወሽቀው ህዝብን ከህዝብ ጋር ደም ለማቃባት ዛሬም የሚጥሩትን የትግራይ ህዝብ በቃችሁ አይናችሁን ጨፍኑና እናሞኛችሁ አትበለን በማለት ፣በተለመደው ጀግንነቱ የጥፋት እጃቸውን እንዲሰበስቡ ያድርግ፡፡(….)

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.