ሪያል ማድሪድ 34ኛ የላ ሊጋ ዋንጫውን አሸነፈ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ሪያል ማድሪድ 34ኛ የላ ሊጋ ዋንጫውን አሸነፈ

1 min read
ትናንት ምሽት በተደረጉ የ37ኛ ሳምንት የላ ሊጋ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ ቪላሪያልን አስተናግዶ 2 ለ 1 በማሸነፍ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው 34ኛ የላሊጋ ዋንጫውን አሸንፏል፡፡
በምሸቱ በተከናወነው ጨዋታ ለሪያል ማድሪድ ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች ካሪም ቤንዜማ ነው ያስቆጠረው፡፡
ከተከታዩ ባርሴሎና በሰባት ነጥብ ልዩነት የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ያረጋገጠው ማድሪድ ከሶስት አመታት በኋላ የላ ሊጋ ዋንጫ ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡
ባለፉት ሶስት አመታት የላሊጋው የበላይ የነበረው ባርሴሎና በምሽቱ ጨዋታ በሜዳው በኦሳሱና ሁለት ለአንድ ተሸንፏል፡፡
ከድሉ በኋላ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን በሰጠው አስተያየት ከሶስት ዓመታት በኋላ ከማድሪድ ጋር ላ ሊጋን ማሸነፉ ከሻምፒዮንስ ሊግ ድል በላይ እንዳስደሰተው ገልጿል፡፡
” ይህ ድል ከምንም በላይ ነው ያለው አሰልጣኝ ዚዳን ዋንጫውን ለማሸነፍ ከፍተኛ ጥረቶች መደረጋቸውን ተናግሯል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የክለቡ ተጫዋቾችም ከዚዳን ጋር በመስራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን እና ወደፊትም ለተሸለ ስኬት እንደሚመራቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ምንጭ:- ቢቢሲ ሰፖርት

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.