የድጋፍ ሠልፍ? ለማን? ዜጎችን እያሳረደ ላለው ቡድን? አዝናለሁ! - ሰርፀ ደስታ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

የድጋፍ ሠልፍ? ለማን? ዜጎችን እያሳረደ ላለው ቡድን? አዝናለሁ! – ሰርፀ ደስታ

1 min read
4

ኢትዮጵያውያን ሆይ እባካችሁ ከነዳው አትነዱ፡፡ ለሕዝብና አገር ቆም ብላችሁ አስቡ! በዚህ ቅዳሜና እሁድ ዜጎችን እያሳረደና ተባባሪ ሆኖ ለሚቆምረው መንግሰት ነኝ የሚለው አካል የድጋፍ ሰልፍ በሚል መልዕክቶችን አይቼ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን ሆይ ምን ሆነናል?ለመሆኑ እያደረግን ያለንውን እያስተዋልን ነው? እነማን ናቸው የዚህ ድጋፍ ሠልፍ ተብዬ አስተባባሪዎች? ምን አዚም ነው የሆነብን? ለገዳይና አስገዳይ የድጋፍ ሰለፍ እየተወጣላቸው ለንጹሐን ማን ይቁምላቸው? ማን ይናገርላቸው? የንጹሐንን ደም አናርክስ፡፡ አዝናለሁ! ልትደግፉት ሠላማዊ ሠልፍ የምትወጡለት ቡድን ማን ነው?

  1. ኢትዮጵያውያን በስንት መከራ ያመጡትን ለውጥ ከወያኔ ወደ ኦሮሞ ዘረኝነት የለወጠ፡- እኛ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እያልን ከዳር እዳር ስንደግፍ አብይ አህመድና ቡድኑ በፍጥነት የኢትዮጵያን የመንግስት መዋቅራት ሁሉ በጸረ-ኢትዮጵያ ኦሮሞ ሲተካ ነበር፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊና በኢትዮጵያዊነቱ በሚኮራ ኦሮሞ ቢተካ አንዳች ቅሬታ የለኝም፡፡ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞዎችማ ዛሬ ወራዳ በሆኑ በኦነግና ወያኔ የአስተሳሰብ ባርነት በወደቁ ሥማቸው እንኳን እንዳይነሳ ሆነዋል፡፡ የአብይ ቡድን ያደረገው እኛን በኢትዮጵያዊነት እያባበለ በፍጥነት ቦታዎችን በጸረ-ኢትዮጵያ በሆኑ ኦሮሞዎች ማስያዝ ነበር፡፡ ለእኔ ከአብይ ይልቅ ለማን አምነው ነበር፡፡ አሁንም ድረስ የለማ ነገር ለእኔ እንቆቅልሽ ነው፡፡ ለብዙዎች አብይ ነው ኢትዮጵያዊው፡፡ በእኔ እይታና አስተሳሰብ ግን ኢትዮጵያዊ የነበረው ለማ ነበር፡፡ አብይና ለማ ያልተግባቡበትን ሚስጢር እስካሁንም ግልጽ አደለም፡፡
  2. ገንዘብ ለጸረ-ኢትዮጵያና ለወሮበሎች ማስተላለፍ፡- ለብዙ ችግሮች ዋና መሣሪያ እየሆነ ያለው ገንዘብ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአሸባሪዎች ገንዘብ ለማስተላለፍ በሚመች ሁኔታ አስተዳዳሪዎች እንደተመደቡለት እንታዘባለን፡፡ ባንኩን በበላይነት ከሚመሩት ባብዛኛው ኦሮሞ መሆናቸው ብቻም ሳይሆን ጸረ-ኢትዮጵያ አቋም ያላቸውና አንዳንዶቹም ከአረቡ ዓለም ጋር ልዩ ቁርኝት ያላቸው ናቸው፡፡ ዋናዎቹ አስተዳዳሪዎች የመጡት ከአዋሽና ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ከሚባለው ነው፡፡ ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል የመጣውና ዘሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና የሆነው ግለሰብ በኦሮሚያ ንግድ ባንክ ዋና ሥራው የእስላማዊ ኦሮሞ ቡድንን ማጠናከር እንደነበር ከሆኔታዎች እንረዳለን፡፡ አቤ ሳኖ ሙሐመድ ይባላል፡፡ ከዚሕኛው በፊት አንድ ሌላ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነ ኦሮሞ ነበር ከ25 በላይ ቅርንጫፎች ሲዘረፉና ለአሸባሪዎች ገንዘብ ሲተላለፍ ያየንው በዚሁ ግለሰብ የባንኩ አስተዳደር ዘመን ነበር፡፡ እንግዲህ ይሄ ሁሉ የሆነው በዚህ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡  የገንዘብ ጉዳይ ከተነሳ ዛሬ ላይ የመንግሰት ባንኮች ልማት ባንክን ጨምሮ አደጋ ላይ ናቸው፡፡ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በብድር መልክ ተሰጥቶ በማይመለስበት ሁኔታ እንዳሉ እንሰማለን፡፡
  3. ኦሮሚያ በሚባለው ክልል እጅግ ብዙ ልዩ ኃይል ማሰልጠን፡- ኦሮሚያ በሚባለው ክልል እንደምንሰማው እጅግ ቁጥሩ የበዛ ልዩ ኃይል በሚል እየሰለጠነ እንደሆነ ሲመረቅ ነበር፡፡ አሁን ቀጥሏል፡፡ ይሄ ልዩ ኃይል እየሰለጠነ ያለው ማንን ለመጠበቅ ነው? ሕዝብን? የምንሰማው ሁሉ አደጋ የደረሰው ፖሊስ ቆሞ እያየና አንዳንድ ቦታዎችም እየተባበር ጭምር እንደሆነ እየሰማን ድጋፍ በሚል ይሄን ኃይል በሕዝብ ላይ ላዘመተ ቡድን ድጋፍ ይታያችሁ፡፡ በነገራችን ላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የሚባው እየሰለጠነ ያለው ኢትዮጵያን በኃይል ለመያዝ እንጂ ሠላም ለማስከበር አደለም፡፡ እድሜ ልኩን በዘረኝነትና ጥላቻ አድጎ በስልጠናውም ወቅት ይሄው እየተሰበከለት የሚወጣ ኃይል እንደሚሆን አለማሰብ አደገኛ ስህተት ነው፡፡
  4. ዜጋ ያልሆኑ ግለሰቦችን መሾም፡- አሁን ያለው ቡድን ሕግና ሥርዓት ሳይሆን መስፈርቱ ኦሮሞነት ብቻ እንደሆነ በሚያሳዝን ሁኔታ ታዝበናል፡፡ ዜጋ ያልሆኑ ግለሰቦችን በኦሮሞነት ብቻ ትልልቅ በሚባሉ የመንግሰት መዋቅሮችና የአምባሳደር ሹመቶች ጨምር እየመደበ እንደሆን እየተነገረ ነው፡፡ የዜጎች ደህንነት የሚጠበቀው ሕግና ሥርዓት ሲከበር እንጂ በኃይል እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ለኦሮሞ ወንጀለኞች ያለማፈር ከለላ እያደረገና ሕግና ሥርዓት እየጣሰ ያለው አሁንም ይሄው ቡድን ነው፡፡ የአገሪቱ ሕግና ሥርዓት በማይፈቅደው የውጭ ዜግነት የላው ግለሰብ በአገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲ አባልነት እንዲታቀፍ ብቻ ሳይሆን በአገር ላይ አሁን የምናየውን ሽብር ጨምሮ በተለያየ ወቅት ለሆኑ የሽብር ጥቃቶች ከለላ እየሆነውና በጀት ጭምር መድቦለት ሲያንቀሳቅሰው የነበረው አሁንም ይሄው በስልጣን ላይ ያለው ቡድን እንደሆነ በደንብ ይስተዋልበት፡፡

አዝናለሁ በኢትዮጵያዊነት የመጡ በስሎን በእርግጥም ከልብ ደግፈናል፡፡ የኢትዮጵያን የመንግስት መዋቅርም ከወያኔ ወደ ኢትዮጵያውያን ያስገቡታል ብለን ነበር፡፡ እዚህ ጋር አሁን አንዳች ክፍተት እንዲፈጠር አልፈልግም፡፡ በዘር ኦሮሞ መሆንና አለመሆን አደለም፡፡ ቅድሚያ ማንም ይሁን ማን በኢትዮጵያ የመንግስ መዋቅር ውስጥ የኢትዮጵያዊነት አመለካከት ወሳኝነት አለው፡፡ አምባሳደርነት ቦታ ተመድቦ ለጠላት የሚሠራ የፀረ-ኢትዮጵያ አመለካከት ያለው ግለሰብ በኢትዮጵያ የመነግስት ወሳኝ መዋቅር ላይ መቀመጥ የለበትም ባይ ነኝ፡፡ በተራ ሠራተኝነት ሊሰራ ይችላል፡፡ የአሁንም መንግስት ነኝ የሚለው አካል ለኢትዮጵያ አደጋ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ ግለሰቦችን በትልልቅ የመንግስት መዋቅር ላይ ሆን ብሎ ያስቀመጠ ቡድን ነው፡፡ አዝናለሁ፡፡

አሁን እየደረሰብን ያለው አደጋ ከሁለት ዓመት በፊት ሊያውም በዛ ቀውጢ ወቅት ሕዝብን ከሕዝብ ማቀራረብ ብቻም ሳይሆን የቱንም ያህል ለ27 ዓመታት ሙሉ የጥላቻና ዘረኝነት ዘር ቢዘራበትም እጅግ ከምናሰበው በላይ ሕዝብ ወደ አንድነቱና ወደሠላማዊ አመለካከቱ ተመልሶ ነበር፡፡  ያ እንዲሆን ዛሬም ቢሆን ትልቁን ድርሻ ለለማ መገርሳ መስጠትን አላፍርበትም፡፡ ዛሬ ምን አቋምና አመለካከት እንዳለው ባውቅም፡፡ የውሸትም ነበር ብዬ ለማመን አሁንም ቢሆን የሚከብደኝ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትና ፍቅር በእርግጥም በሕዝቡ ዘንድ እየጎላ መውጣት ችሎ ነበር፡፡ በኋላ የሠላም ሚኒስቴር ሲባል በወቅቱ የዚህ የሚኒስቴር መቋቋምን  ከማይደግፉት ብሆንም ከሆነ አይቀር ደግሞ በልዩ ዝግጅቶች፣ በተለያዩ መገናኛዎችን ሁሉ በማስተባበር እንደተባለውም ኢትዮጵያዊነትን ማለምለምና ለዘመናት ሕዝብ ከተመረዘበት የዘረኝነትና ጥላቻ አስተሳሰብ መፈወስ በተቻለ ነበር፡፡ በፍጥነት ሲሆን ያየነው ሁሉ ግን ተቃራኒዊ ነው፡፡ ትልልቅ ወንጀሎች ሲፈጸሙ ወንጀሎችን ማድበስበስና ጭራሽ ተጠቂዎችን መክሰስ ወንጀለኞችን ማበረታታት እየታዘብንው ያለ እውነት ነው፡፡ አሁን እንኳን አቃቤ ሕግ ተብዬዋ የእነ ጀዋርን ወንጀል ለማድበስበስ ብሎም አጋጣሚውን በመጠቀም ለመበቀል ስትል እስክንድር ነጋ ከጀዋር ጋር ተናቦ ይሰራ ነበር ስትል አላፈረችም፡፡ እርግጥ ነው እስክድር ነጋ የአዲስ አበባን ወጣት ለገድለው የሚመጣን ቡድን እንዲከላከል ቀስቅሶ ይሆናል፡፡ ይሄ ደግሞ ከትክክለም በላይ በተለይ የወንጀለኞች ከለላ የሆነው መንግስት ነኝ የሚል አካል በዋናነት አገሪቱን በተቆጣጠረበት ሁኔታ ግድ ነው፡፡  ቅንነት፣ የሕዝብና አገር አሳቢነትን በማስመሰል አይሆንም፡፡ መጀመሪያ ከሴራና ተንኮል የነጻን ስንሆን ሌላውን እግዚአብሔርም ይረዳናል፡፡ ሥለዚህ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የመጀመሪያ ጥያቄ ሊሆን የሚገባው የመንግሰት መዋቅር በማን እጅ ነው የሚለው ሲሆን አሁን የደረሰብን አደጋ ሁሉ መንግስት የተባለው ቡድን ሕግና ሥርዓትን ከማስጠበቅና የዜጎችን ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ ለወንጀለኞች ከለላ እየሆነ የተደረገ በመሆኑ በዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብም ይሄው ታውቆ ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ የከፋ አደጋ እንዳይደርስ ከወዲሁ ቢታሰብበት እላለሁ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

4 Comments

  1. You’re not any better. And the people can do what the hell they like. At least they’re doing it on their own terms.

  2. ሠርፀ
    በትክከል አስቀምጠኸዋል። ይህን መንግሥት ደግፎ መሰለፍ እንደ ሰው መክሸፋችንን አመላካች ነው ።የዚህ ሁሉ እልቂት መሠረተ አብይና እሱ የሚመራው መንግሥት ነው። አብይ በዝምታው ሽብር የኦሮሞ አክራሪዎች መብት አንደሆነ አረጋግጧል ።ጃዋርና በመንግሥት ውስጥ የተከማቹ ፅንፈኞች የሚያወሩት እና የሚያደርጉት ሁሉ የሽብር ሥራ ነበር። የኦሮሞ ፖለቲከኞች ሥራቸው ሁሉ በምርጫ አሸንፎ አገር መምራት ሳይሆን በፍጥጫ አዲስ አበባን ነጥቆ ነፃ ኦሮሚያን ማዋቀር ነው። ከመሥራት ይልቅ ነጥቆ መውሰድ ዋና አላማቸው ነው ። አብይ አህመድም ቢሆን ከዚህ የፀዳ ራዕይ የለውም ። ራሳችንን አናሙኝ።ለማ መገርሳም የሥልጣን ጉዳይ ካልሆነ ለኢትዮጵያ የወገነ ሰው አይደለም።

  3. Balderas is not permitted to hold demonstrations in Ethiopia but that does not the Balderas supporters cannot be the voice of Balderas by holding demonstrations in countries outside Ethiopia.

  4. Balderas is not permitted to hold demonstrations in Ethiopia but that does not mean the Balderas supporters cannot be the voice of Balderas by holding demonstrations in countries outside Ethiopia.

Leave a Reply to Mekuria Cancel reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.