ለሻሸመኔው እልቂት ተጠያቂው ሸኔ ሳይሆን ብልጽግና ውስጥ ያሉ ጽንፈኞች ናቸው- ግርማ ካሳ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ለሻሸመኔው እልቂት ተጠያቂው ሸኔ ሳይሆን ብልጽግና ውስጥ ያሉ ጽንፈኞች ናቸው- ግርማ ካሳ

1 min read
4
ከአንድ አመት ተኩል በፊት ፣ “ሻሽመኔ በአክራሪ ኦህዴዶች እስከተዳደረች ድረስ የሚለወጥ ነገር አይኖርም” በሚል ርእስ ስር፣ በሻሸመኔ ጽንፈኞች አንድ ሽማግሌ የሙስሊም አባትን መሬት ላይ ጥለው ፣ ሲወግሩና ሲደበድቡ የሚያሳይት ቪዲዮን አያይዤ ለጥፌ ነበር፡፡
የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ተማም ሁሴንና የከተማው አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ናደው አምቦ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር ውለዋል

ይኸው በድጋሚ ሻሸመኔ ሌላ በጣም የከፋ ሰቆቃ አስተናግዳለች፡፡ ሻሸምኔ እንዳለ በጽንፈኞች ወድማለች፡፡ አሌፖ ሲሪያ ሆናለች፡፡

መንግስት ኦነግ ሸኔ ያደራጃቸው ናቸው ይሄን ያደረጉት ይላል፡፡ ለሁሉም ነገር ሸኔ ጥፋተኛ እየተደረገ ነው፡፡ ቀላሉ እርሱ ስለሆነ፡፡ ሆኖም ይሄ የመንግስት ጣት ቀሰራ አልተዋጠልኝም፡፡
ሸኔ በአገራችን ችግር ፈጣሪ እንደሆነ የሚካድ አይደለም፡፡ በወለጋ የተማሪዎች መታገት፣ ወለጋና ጉጂ የጦርነት ቀጠና እንዲሆኑ በማድረግ በአካባቢው ህዝብ ላይ ትልቅ ችግርን እየፈጠረ ያለ፣ መሸነፍና መደምሰስ ያለበት ቡድን ነው፡፡
ሸኔ ማለት የዳዎድ ኢብሳ ኦነግ የዉትድርና ዊንግ የነበረ ማለት ነው፡፡ ብዙዎች ላያወቅቱ ይችሉ ይሆናል፤ ሸኔዎች ሆነ እነ ዳዎድ ኢብሳ ከነጃዋር መሐመድ ጋር ችግር ያለባችው ሰዎች ናቸው፡፡ በተለይም ሸኔዎች እንኳን ለነጃዋር ክብር ሊኖራቸው፣ በማንኛውም ጊዜ እርምጃ ሊወስዱባቸው እንደሚችሉ የታወቀ ነው፡፡
የጃዋር ኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ (OMN) ወለጋ ስላለው እንቅስቃሴና ስለ ሸኔ ብዙ አይዘግብም ነበር፡፡ አቶ ዳዎድ ኢብሳ በOMN የቀረቡበት ጊዜ ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ OMNን በመቃወም፣ በዋናነት ወለጋዎች ያሉበት የኦሮሞ ኔትዎሮክ ኒዩስ (ONN) የሚል ሜዲያም ተቋቁሟል፡፡ የዳዎድ ኢብሳ ኦነግ፣ ከኦብነግና ሌሎች ድርጅቶች ጋር “ትብብር” የሚባል ጥምረት ሲመሰርት፣ OMN ን ሳይሆን ONN ነበር የዘገበው፡፡ OMN ለነ አቶ ዳዎድ ኢብሳ ኦነግ ሽፋን መስጠት ብዙም አይፈልግም፡፡ እንግዲህ ይሄ በራሱ አንድ የሚያሳየን ነገር አለ፡፡
ሸኔ የሚንቀሳቀሰው በዋናነት በወለጋና በጉጂ ነው፡፡ በአርሲ፣ ሃረርጌ፣ ባሌ፣ ከሚሴ በመሳሰሉት ሸኔ የለም፡፡ ያ እንደሆነ በታወቀበት ሁኔታ በነዚህ ቦታዎች ግፍ የፈጸመው ሸኔ ነው ማለት እውነትን ከሕዝብ መደበቅ ነው፡፡ ወለጋና ጉጂ ስላሚሆነው ሸኔን መክሰስ ያስኬዳል፡፡ አርሲና ባሌ፣ ሃረርጌና ከሚሴ ስለሚሆነው ግን ሸኔን መክሰስ አዋጭ አይደለም፡፡ (በነገራችን ላይ ላይ ከዚህ በፊት በአጣዬ ለተፍጠረው እልቂት ፣ ኦነግ እንደሆነ ተገልጾ ነበር፡፡ አዎን ኦነግ ነበር፡፡ ብዙ ኦነጎች ናቸው ያሉት፡፡ በዳዎድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ሳይሆን አርሲና ባሌ ካሉ እስላማዊ ኦነጎች ጋር ግንኙነት ያለው ኦነግ ነው)
ገዢው ፓርቲ ነገሮችን ከማድበስበስ ይልቅ የችግሩ ዋና ምንጭ ላይ ማተኮር ያለበት ይመስለኛል፡፡
እንደነ አርሲ ባሉ ቦታዎች የሚንቀሳቀሰው ሸኔ ሳይሆን ሌላ፣ እነጃዋር የሚመሩት የተደራጀ የጽንፈኛ ቡድን አለ፡፡ ይሄ ቡድን ከዳዎድ ኢብሳ ኦነግ የተለዩ በአብዛኛው የነጃራ ተከታይ እስላማዊ ኦነጎች ፣ በኦፌኮ ውስጥ ያሉ አክራሪዎች እንዲሁም በትልቁ ሊሰመርበት የሚገባ በኦህዴድ አሁን ደግሞ የኦሮሞ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አባላትንና የተወሰኑ አመራሮችን ያቀፈ ቡድን ነው፡፡ አዎን እዚህ ቡድን ውስጥ የብልጽግና ፓርቲ አለበት፡፡ ያ እንዳይታወቅም ነው፣ ችግሩን externalize በማድረግ ከችግሩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውን ሸኔ ተጠያቂ በማድረግ በሻሸመኔና በዝዋይ፣ በከሚሴና በሃረርጌ ለሆነው ነገር ጣት እየቀሰሩ ያሉት፡፡
የኦነግ ሸኔ ጉዳይ እልባት እያገኘ ነው፡፡ መከላከያ እየወሰደ ባለው እርምጃ በወለጋና በጉጂ አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ ነው፡፡ እነ ጃል መሮም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወይ እጅ ይሰጣሉ አሊያም ይደመሰሳሉ፡፡ ሆኖም ግን ትልቁና አሳሳቢ የሆነው እነ ጃል መሮ ከፈጸሙት የባሰ ግፍና ሰቆቃ እየፈጸመ ያለው፣ አብዛኞቹ አባሎቻቸው የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የተሰገሰጉ፣ የጽንፈኛው ቡድን ነው፡፡
ስለብልጽግና ይሄን ስናገር አንዳንድ የዶር አብይ ደጋፊዎች ሊከፉ ይችላሉ፡፡ ግን የምንጽፈዉና የምንናገረው ዶር አብይ አህመድ የርሱን ድርጅት እንዲያጸዳ ነው፡፡ በብልጽግና ውስጥ አመራሮች ጋር ሳይቀር ሰርጎገቦች፣ ላይ ላዩን ኢትዮጵያ እያሉ ውስጡን ውስጡ የዘረኝነት አጀንዳ የሚያራመዱ፣ በአቶ ለማ መገርሳ የተሾሙ ብዙ አሉ፡፡
እስቲ አስቡት ሻሸመኔ ስትወድም፣ የፖሊስና የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይሎች ለምንድን ነው ከተማዋናን ሕዝቡን መታደግ ያልቻሉት ? መመሪያ አልተሰጠንም ይላሉ፤ ባይሰጣቸውስ ዝም ማለት ነበረባቸው ወይ ? ደግሞ መመሪያ ለምን ከአመራሮች አልተሰጣቸውም ? የኦሮሞ ክልል ፖሊሶችንና ልዩ ኃይላትን የሚመሩት፣ የሚያሰማሩት፣ መመሪያ የሚሰጡት እነ ማን ናቸው ? የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች አይደሉም ? በተፈጠረው የዘር ማጽዳት ወንጀሎችና ሰቆቃዎች ሰዎችን የብልጽግና ፓርቲ ላይ ጣታቸውን ቢቀስሩ ትክክል አይደሉም ?
ከአንድ አመት በፊት እንዳልኩት አሁን ደግሜ እላለሁ፡፡ በተመለከተ ችግሩ ያለው ኦህዴድ ጋር ነው፡፡ ወይም የኦሮሞ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጋር ነው፡፡ ችግሩ ያለው የኦሮሞ ክልል መስተዳደር ጋር ነው፡፡ ችግሩ ያለው በኦሮሞ ክልልያሉ የዞንና የወረዳ መስተዳድሮች ጋር ነው፡፡ ችግሩ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ጋር ነው፡፡ ችግሩ ያለው እነዚህ መስተዳደሮች የሚመሩበት የዘር ፖለቲካው ጋር ነው፡፡

4 Comments

  1. Ato Girma, you have very valid points here. In my appeal to ORoMara governor generals, I as well was pleading with them to rid off their kilils from remnants of anti-ethiopian figures. I noticed, especially after the murder of Hacaalu, the leaders seem to have realized their blunders and trying to correct them. Give them the benefit of the doubt so that they may unleash their power against these evils. It is, however, critical to support our fragile transitional team in that endeavour. I suggest you come up with measures that these leaders should consider to overcome the current impasse between TPLF and the Abiy government. I wish all Ethiopians drop their party allegiance and come up with alternative solutions so that there won’t be any more bloodshed in hour homeland. Great analysis !

  2. “በተፈጠረው የዘር ማጽዳት ወንጀሎችና ሰቆቃዎች ሰዎችን የብልጽግና ፓርቲ ላይ ጣታቸውን ቢቀስሩ ትክክል አይደሉም ?” ግርማ ካሳ
    አንዱን ምረጥ እንጂ ግርማ ካሳ! “ከፓርቲያቸው ኦሮሞን ቢያጸዱ?” ትላለህ። በሌላ ወገን ደግሞ ዘር ማጽዳት ወንጀል ነው ትላለህ። ዘር ማጽዳት ለኦሮሞ ሲሆን ትክክል ነው?? ናዚነትን በግልጽ መስበክ ብቻ ሳይሆን መፈጸም እና ማስፈጸም ጀመራችሁ! !

    • እንደእናንተ ያሉ ገዳዮችን ፀረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ቢያፀዱ መልካም ነው::መሆንም አለበት::ንፁሀንን መጨፍጨፍ ኦሮሞነት አይደለም:: የንፁሀን ደም ይከተላችሗል:: ጃዋር እጁ ደም አለበት:: የንፁሀን ደም ዘራፊና ሌባና ባንዳውን ወያኔም ይከተላል:: በሻሸመኔ የተካሄደው ቦኮሀራም ድርጊት ይከሽፋል:: ኢትዮጵያ ፈርሳ የእናንተ ምናባዊ ኦሮሚያ አትፈጠርም :: እንደቃዣችሁ የህይወት ፍፃሜያችሁ ይሆናል::

      • ባንተ ቤት ሃሳብህን የተቃወመ ሁሉ ጸረ ኢትዮጵያ ነው ! ጨቅላ! ሌላ ሥራ የለህም??

Leave a Reply to Abawirtu Cancel reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.