የብዙሀን ዖሮማራን ስነልቦና ስላለማወቅ - ይድረስ ለቀሼ ፖለቲከኞችና አንጋቾች - ከአባዊርቱ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

የብዙሀን ዖሮማራን ስነልቦና ስላለማወቅ – ይድረስ ለቀሼ ፖለቲከኞችና አንጋቾች – ከአባዊርቱ

1 min read
2
አይበገሬውን፣ ጀግናውን ልጃችንን በላችሁት? አሁን ማ  ይሙት በእንዲህ አይን ያወጣ ግልጽ የአገርና የወገን ክህደት ሥልጣን ልትመለሱ ወይም ጃንጥላ ያዦቹ ወደ እልፍኝ ልትቀርቡ? እናንት ደመነፍሶች እውነትም ዖሮሞን ወይም ኢትዮጵያን አታውቋትም። ለነገሩስ ባእዳን አይደላችሁ? ምድረ የደናቁርት ጄኔራል፣ ማርሻል፣ ዶር አስተማሪ፣ ምናምንቴ ተብዬዎች! ልባችንን በሀዘን ትሰብሩት ይሆናል እንጅ ኢትዮጵያን አትሰብሯትም። ይህን በርግጠኝነት መተንበይ ይቻላል። ይህን በምጽፍበት ወቅት የእልክ ብዛት ጣቶቼ እየተንቀጠቀጡ ነው። ምናልባት የተወሰኑ ለ 30 አመታት አይምሯቸውን አወናብዳችሁ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከጨቅላ አይምሯቸው የሰረቃችሁዋቸው የፌስቡክ ህጻናት ሚሊሻዎችን ልብ ታማልሉ ይሆናል በቀሼ ፖለቲካችሁ። ያውም ለጊዜው። እያደር እየገባቸው ሲሄድ በቁም ይቀብሯችሁዋል። እመኑኝ።  ነፍሶችን መገበሬው አይቀር ነው በዚህ ትንንቅ።
በትላንትናው ምሽት ብርሃኔ ቤካ የምትባል ልጃችንና የመስፍን ፈይሣን የኢሳት ውይይት ሰምቼ ውስጤ ተኮማትሮ ግን በውስጤ ለረጅም ጊዜ የምጠረጥረውና የምጽፋቸውን ነው ያረጋገጡልኝ። እኔ የማውቀው ዖሮሞነት ፣ የወለዱኝና ያዋለዱኝ ማህበረሰብ የነዚህ  አይነት ድንቅ ወጣቶች አመለካከት ነው። በዚህ አጋጣሚ ብርሃኔ ቤካ፣ ልቤን ሰብረሽዋል። የሀጫሉን ጀግንነት ብቻ ሳይሆን ያንቺንና የመስፍን ፈይሣንም ድንቅነት የተማርኩበት ውይይት በመሆኑ። ይስሙት እነዚህ አውሬዎች። እስካሁንም ፣ ሁሌም እንደምለው የብዙሀኑ ዝምታ ነው እንዲህ ኩታራዎች ሲፈነጩ ብሎም በጀግኖቻችን የፈሪ ዱላ  ያሳረፉብን። ይሁን ግድ የለም! ወደ ዶር አቢይ ከታች እመጣለሁ።
የታሪክ ዝቃጮች ህውሀቶችና አገልጋዮቻችሁ!
ይቺን በሆቴላችሁ ግድግዳና በየአሽቃባጮቻችሁ ፣ በውስጥም ውጪም ፣ በናንተው ምጽዋት (ሊያውም በሰረቃችሁን ሀብት) በሚተዳደሩት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ስቀሏት። አማራና ዖሮሞ፣ ሰሜንና ደቡብ፣ ምስራቅና ምእራብ እናንተን ገምግሞ ጨርሶ አፈር ለማልበስ ጥቂት ቀናት ብቻ ነው የቀሩትና ለጊዜው በጠጣችሁት ደም በስካር ፈንጥዙ። ይህን ለጥፉት በየግርግዳችሁ ያ ግርግዳ እስኪናድባችሁ – የመቼ ጉዳይ ብቻ ነው። መቼስ ድንቁርናችሁ ላይጣል ነው። አሁን ማ ይሙት ሀጫሉ ስለ ምኒልክ ተናገረና፣ በሳምንቱ አስገደላችሁትና አማራና ዖሮሞ ጦርነት ከፍቶ እናንተ ገላጋይ ሆናችሁ በለመዳችሁት ጌኛዎቻችሁ ሸገር ልትገቡ? 27 አመታት ሁሉ አገሪቱን በሁሉም መስክ ቀፍድዳችሁ ገዝታችሁ አገሬውን አንዱንም ክፍል በቅጡ ማወቅ ይሳናችሁ? ዬትኛውን ህዝባችንን ነው ለነገሩስ የምታውቁት? ከአብራኩ ወጣነው የምትሉትን ትግራይን ታውቁታላችሁ? በጭራሽ? ለነገሩ ከዲያብሎስ አብራክ እንጅ የትግራይስ ማህጸን እንደናንተ አይነቱን ጽልመት አያበቅልም። የናንተው እንኳ ከገባን ሰነባበተ ከናንተ ጋር ከ ሁለት እመት ወዲህ ጭራቸውን የሚነሰንሱት በስመ ዖሮሞ ውላጆችም ዖሮሞን አያውቁትም። ከርሳቸውን እንጅ ። መቀሌ ተመላልሰው ስለናንተ ትግል አጋርነት ሲነግሩን ለብዙ አስርተ አመታት በናንተው አጋዚ ጥይት የተበሉትን የዖሮሞ ልጆቻችንን እያሰብን ” ይሁን ግድየለም፣ የሥልጣን ጉዳይ ነው፣ ዛሬ ነገ በርዶላቸው ወደህሊናቸው ይመለሳሉ”  እያልን ትእግስት ኖረን እንጅ ተመልሰው ያበላ እጃቸውን ይነክሳሉን ማንም የጠበቀ አይመስለኝም። አሁን ምን መደረግ እንዳለበት ብዙ ዝብዝብ አያስፈልገውም ። መንግስት ወጥሮ የያዘ በመሆኑ። ሆኖም እንዲህ ልበል።
ይድረስ ለዶር አቢይና የብልጽግና ሹማምንት እንዲሁም ለአቶ ሺመልስ አብዲሣ!
ዶር አቢይ ሆይ!
መለዮ ብያለሁ ኮለኔል!
በቃን መታገሱ። ይብቃን ሰይጣንን ለማቀሰስ ቤተሙከራዎች። በጭራሽ አይቻልም ። ተደርጎም አያውቅም ። በእስላሙም ክርስቲያንም ሃይማኖት የፖለቲካው ቀርቶ ። የብርሃኔ ቤካን ምክር ሀሳብ በደንብ እንዲያጤኑ እየደጋገሙ ይስሙት። እነዚህ የሰይጣን ውላጆች አሁን ዝም ከተባሉ ከነገው ሰኔ ሙከራ የሚተርፍ የለም። የሀጫሉ እልፈት ለመጪው አገራዊ እልቂት ጥንስስ መሆኗ ነው። መስፍን ፈይሣ እንዳለው ይህን ድንቅ ልጅ እንደ “ቦረንቲቻ በግ” የሰውልን ለእቅዳቸው ነው። ከሁለት አመት ወዲህ በየሚዲያው ሲፎከር ነበር በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ። መረጃው በጽሁፍ ፣ ቪዲዮና ኦድዮ አደባባይ ቁጭ ብሏል ። የእርስዎ የባሰ ደም ያስገብረናል ስሌት ማስገበሩ አልቀረልንም – ያውም በሚያም ደረጃ። ይቺ የሃጫሉ ነፍስ አጠፋፍ ስሌት ” አቢይ እንዲህ ግራ ቀኝ በአለም አቀፍ ጉዳይ ተወጥሮ እርምጃ አይወስድም” ከሚል የንቀት ስሌት ነው። እንዲህ ነው የኔ የመፍትሄ ሀሳብ ሌላስ ምንስ ማድረግ እችላለሁ።
 የፈለገው መስዋእትነት ይከፈል ልክ ጁዋርን እንደቀፈደዳችሁ የመቀሌዎቹንም ቀፍድዱልን። እርዳታ ካስፈለገ ለኡትዮጵያ ብለው ሳይሆን ለራሳቸውም ብለው እነ አሜሪካ ሆነች ፈረንሳይ ፣ ቻይና ሆነች ማንም ወደሁዋላ አይሉም። እዛም  መድረስ የለብንም። በአቆሙብን ሰይፍ አናት ላይ እራሳቸው ይቀመጧታል በእኛው የተባበረ ክንድ።
በዚህ አጋጣሚ ባለፈው አመት ያወለቃትን የኢትዮጵያ ቡልኮ ዛሬ ጃኖ እስከዝናሩ ታጥቆ ቆፍጠን ብሎ ስለኢትዮጵያ ብሎ  አመራር እየሰጠ በማየቴና መስማቴ ለወጣቱ ሽመልስ አብዲሣ መለዮዬን አንስቻለሁ። እንዱህ ነው አሳይተህና ነስተኸን የነበረውን ፍጹም ኢትዮጵያጵያዊነት በአመቱ መለስክልን። ምናልባት የዚህ ድንቅ ሀጫሉ ደም ደመከልብ ሆኖ እንደማይቀር ማስረጃም ይህው ነው።
ውድ ኢትዮጵያውያን!
የአማራዎቹም ልጆች እነ አምባቸው ሲሰየፉ እንዲሁ ነው የነደድኩት። እስከመቼ ልጆቻችንን በውስኪና አልባሌ ጉዳይ በሰከሩ ሰዎች አስረክበን ዝም የምንለው? የሚጮሁት በርሜሎች ጥቂት ሆነውና ደምቀው እንደምን ብዙሀኑ ድምጻችሁንና ድጋፋችሁን ለዚህ ድንቅ የአገር መሪ እንኳ ባይታያችሁ እንደምን ለብዙ አስርተ አመታት ልጆቻቸውን በግፍ ላጡ እናቶች ግድ አይላችሁም? እስከ መቼ? ነው ? ሳየው ዝም ከሚለው ወገን ለነዚህ ከይሲዎችም ቢሆን ያጎበደዱትን የታሪክ አተላዎች ለማድነቅ ሁሉ ዳዳኝ። ለምን? ለከርሳቸውና ገንዘብም ቢሆን አላማ ሰንቀዋልና። በዝምታ በዚች የመከራና ኮረና ዘመን እንኳ አሁንም እንደ ዘመነ ጽልመት  በዝምታ ብቻ የተወረራችሁ ብዙ ትኖራላችሁ። እስከ መቼ? ይህ ኑሮ ነው?
ይህን እየጻፍኩ እስክንድርም ታሰረ የሚል ዜና አየሁ። አከታትሎም አቶ ስማቸው የተባለ 360 ከተባለው አውታር እንደተሰናበተ አነበብኩ። እንግዲህ  ያ ኤርምያስ ለገሰ የሚባለው ሲጀምረው ሁሉ አልጣመኝም ነበር። ዛሬ እንዲህ ጉድ ሊወጣ። እንግዲህ የኤርምያስ የአዲሳባ “ቫይስሮይ” መሆኑም አይደል እስክንድር? ምናለ ጥንት በጋዜጠኛ ጀግንነቱ እንደተወሳ በቀረ ኖሮ። እውነትና  ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ ምንም ሳልቸኩል ለምን እንደተያዘ እስኪጣራ ልጠብቅ። አንድ ለአይምሮዬ ግራ የሚገባኝ እነዚህ የወያኔን ኮዳ፣ ግርፋት፣ እርዛት እናም ሌሎች የሚቀፉኝን ግፍ የተፈጸመባቸው የሀብታሙ፣ ርእዮት፣ በቀለ፣ አሁን ደሞ እስክንድር አይነት ጉዶች በምን ስሌት ነው ተመልሰው እነዚሁ ጽልመቶች ስር የሚርመሰመሱት? ምን አይነት ህሊና ነው? የኢትዮጵያ አምላክ ፍርዱን ይሰጣል።
በመጨረሻም በግፍ ላለቁብን ወገኖቻችን ነፍስ ይማር። በቃችሁም ይበለን። የጀግናው ልጃችንንም የወደቀ አገዳደል የመጨረሻው ያድርግልን ። ለብዙ የሚዋሱትን፣ የማንንም ከርሳም ቆፍጠን ብሎ ፊትለፊት ለተፋለመ ጀግና ይህ አይገባውም ነበር። የዖሮሞ አባባል አለ። ” ሲላስ ናማ ያርቱቲ ናማ ጋላፋታ”  ጥንትም ጀግና በአልባሌ ሰው እጅ ነው የሚወድቀው እንደማለት።
አመሰግናለሁ
ነፍስ ይማርልን!

2 Comments

 1. የጻፍከውን የምታምንበት ከሆነ ከዶሮ የተሻለ ጭንቅላት የለህም እና አይፈረድብህም! ለሆድ ከሆነ ግን ትንሽ አለዝበው፣ ነገም ቀን ነውና!
  የሃጫሉን ሆነ የሌሎች ጀግኖችን ስም አታንሳ! እንደሃጫሉ ያሉ ዉድ የኦሮሞ ልጆች የተሰዉት እና እየተሰዉ ያሉት፣ ባለጉልበትን ሲያሞግሱ ወይም የባለስልጣንን ቂጥ ሲጠርጉ አይደለም፣ ጉልበተኛን እና ሆድ አደሮችን ሲዋጉ እንጂ! ጀግና በከንቱ እንደማያቅራራ ሁሉ፣ በርካሾች እንደበት ስሙ መነሳቱንም ይጸየፋል!! “baalbaaseen baasa hin beektu, gadheen asaasa hin beektu”. Abba Caala ነኝ።

 2. አባ ጫላ ቋንቋህን ብታለዘብዉ ጥሩ ነበር የምድር ቄሮንና የሳይበርን ቄሮ ማስተናገድ ይከብዳል።
  አጫሉን በተመለከተ ከምንም በላይ የተጎዳዉ ጥበብና ኪነት ነዉ ልጁ ጊዜ ቢሰጠዉ ተአምር ይሰራ ነበር። ትግሬ ስላሰረዉ በብስጭት ጁዋራያዊዎች/ኦነጎች የልጅነት አእምሮዉን ባይሰልቡት በሰከነ መንገድ ህይወቱን ይመራ ነበር። ለዛዉም ከሗላዉ የሎሬት የጸጋዬን የመስለ ስም ያስከተለ ዜጋ ጭልጥ ብሎ በደናቁርት ይሳባል ማለት ከንቱ ነዉ። ልጁ ብሩህ አእምሮ አለዉ LTV በተባለዉ ቴሌቭዥን ቤቲ የምትባለዉ ደካማ ጋዜጠኛ ባይ በመሪ ጥያቄ ወደ ማይረባ እንካ ስላንትያ ልትከተዉ ስትል በምን አይነት መንገድ አልፏት እንደሄደ ካወቅሁ በሗላ ልጁ የጭዳ በግ እንደሚሆን ገምቼ ነበር።

  ባጠቃላይ እንደማልኮሜክስ ያመልጠናል በሚል እሳቤና እሱ ከወጣ ምን ያህል ኪሳራ እንደሚያርስባቸዉ የገመቱ የራሱ ወገኖች ከትግሬዎች ጋር በቅንብር የዚህን የዋህ የጥበብ ሰዉ ህይወት መቅጠፋቸዉ በጣም ያሳዝናል።

  እስክንድር፤ስንታየሁ ቸኮል፤ኢንጂነር ይልቃል፤ አስራት ሚደያን በተመለከተ ማሟያና አንድም አክራሪዎችን ለማስደሰት ሁለትም ጠንካራ ተፎካካሪዎችን ሞራል መጣል፤ ማዳከም ወይም ደግሞ በመንግስት በኩል ፍርሀት ግብቶት ካልሆነ በስተቀር እነዚህ ሰዎች መንግስትንም የሚያሰጉ ካለመሆናቸዉም በላይ መንግስት በከፈተዉ ቻናል የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ መንግስት ለክብፉ ሲል እንደዉም ጥበቃ ሊያደርግላቸዉ በተገባ ነበር።የነዚህ ሰዎች መታሰር ሁኔታዉን ትያትራዊ ስለሚያደርገዉ የመንግስትን እርምጃ ክብደቱን ይቀንሰዋል።
  ለማንኛዉም አጫሉ ሳናዉቀዉ ያመለጠ የጥበብ ሰዉ ነዉ ነብስ ይማር ለቤተሰቡም መጽናናትን ይስጥ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.