የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት፣ በአፍሪካም የተወላጆች የመጀመሪያ ሲኒማ፣ "ሰይጣን ቤት" - ነገሰ ተፋረደኝ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት፣ በአፍሪካም የተወላጆች የመጀመሪያ ሲኒማ፣ “ሰይጣን ቤት” – ነገሰ ተፋረደኝ

1 min read
1

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት፣
በአፍሪካም የተወላጆች የመጀመሪያ ሲኒማ፣
“ሰይጣን ቤት”

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት፣

በጥሩ ሁኔታ ታድሶ ከሚሰራው የመስቀል አደባባይ-ማዘጋጃ ቤት ፕሮጀክት ጋር ተካቶ አሁን ካለበት አሳዛኝ ሁኔታ ይላቀቃል።
ይኸን ከክቡር ከንቲባው ጠይቄ ተረድቻለሁ
ታሪካዊ ቤቱን እንዲህ በሚያሳዝን እና በሚያስጠይቅ ሁኔታ ላለፉት 25 አመታት በላይ ያለጥገና አሁን ደግሞ በአደገኛ ሁኔታ የዕቃ ማከማቻ ያደረገው ድርጅት ከዚያ እንዲወጣ መደረጉ ግድ ነው።
፨፨፨ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እንደጻፉት

“ሰይጣን ቤት” ተብሎ የሚጠራው ህንፃ ትናንት ምሽት እንደፈረሰ የሚነገረው እና የሚፃፈው ትክክል አይደለም – የከንቲባው ፅ/ቤት ፕረስ ሰክረታሪ ፌቨን ተሾመ “የሲኒማ ቤቱ ህንፃ ፈፅሞ አይፈርስም፣ እንደውም ውስጡ ያሉት ሱቆች እንዲወጡ ተደርጎ እና እድሳት ተደርጎለት ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውል ይደረጋል” ያለችው ፌቨን ጨምራ “ግቢው ውስጥ ግን ድሮውንም መፍረስ የጀመሩ ቤቶች አሉ፣ እነሱ እንዲነሱ እየተደረጉ ነው” ብላለች።

የማሕበራዊ ድረገጽ አስተያየት ሰጪዎች በታሪካዊ ቅርስነት የተመዘገበው የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት(ሰይጣን ቤት) በለሊት መፍረሱ ሌላኛው ጥያቄ ያስነሳ ጉዳይ ነው። አዲስ አበባ መስተዳደር ጨለማን ተገን አድርጎ ታሪካዊ ቅርሶችን አፍርሷል ሲሉ ይተቻሉ። አዲስ አበባ ታሪክ የሌላት ከተማ ለማድረግ የሚደረገው ሩጫ ሊቆም ይገባል ሲሉ የቅርስ ጥፋት እንዲቆም የሚከራከሩ አካላት ይናገራሉ።ሲኒማ ቤቱ 1900 ዓ.ም አካባቢ በአፄ ሚንሊክ ዘመነ መንግስት የተሰራ እንደሆነ ይነገራል።

ዋፋ ሲኒማ ተብሎ የሚጠራው ቦታ ሊፈርስ ነው በሚል የወጣው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ቦታው በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ታሪካዊ እንደመሆኑ መጠን ታሪካዊ ይዞታውን በጠበቀ መልኩ የመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት የሚገነባው የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት አካል ሆኖ በአዲስ መልክ ይገነባል ተብሏል።

አሁን ላይ ያለበት ይዞታም ቦታውን በማይመጥን መልኩ በእቃ ማስቀመጫነት እያገለገለ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ ይህን ቦታ ታሪካዊ ይዞታውን እንደጠበቀ በዘመናዊ መልኩ ተመልሶ ለአገልግሎት እንዲውል እንደሚሰራ ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ነገሰ ተፋረደኝ

1 Comment

  1. Addis Ababa need to follow the example of city of Pompeii Italy on all of the historical heritage buildings sites in Addis Ababa, meaning the word “modernization” should be a no no.

    Modernization defeats the purpose of keeping historical sites . The city of Pompeii in Italy is not modernized anywhere. In CoronaVirus’s time turning this historical site into a homeless coronavirus containment shelter or turning it into another movie theater service should not be considered at all since it risks loosing it’s genuineity originality. Addis Ababa got many other sites to shelter the homeless.

    Addis Ababa need her own Mayor not the unelected illegal Aba Gadda Mayor Takele Uma ,this Aba Gadda if given a chance Next he might bring the fancy tv screens and the fancy modern musical instruments with escalators elevators into Lalibella-Wollo church and into Axum Tsion-Tigrai church after they are done “modernizing” Addis Ababa.

Leave a Reply to Abdulkidus Cancel reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.