የሀገር መከላከያ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ የሌሎች ክልል ፖሊሶችን የደንብ አልባሳትን እና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በመጋዘን ውስጥ አከማችተው የተገኙ በቁጥጥር ስር ዋሉ – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

የሀገር መከላከያ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ የሌሎች ክልል ፖሊሶችን የደንብ አልባሳትን እና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በመጋዘን ውስጥ አከማችተው የተገኙ በቁጥጥር ስር ዋሉ

1 min read

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሀገር መከላከያ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ የሌሎች ክልል ፖሊሶችን የደንብ ልብስ አልባሳትን እና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በመጋዘን ውስጥ አከማችተው የተገኙ አምስት ተጠርጣሪዎች ከእነኤግዚቢቱ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡ ቦንብ፣ ሽጉጥና ጥይት አብሮ ተይዟል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው እፎይታ የገበያ ማዕከል አካባቢ የሚገኝን መጋዘን የተከራዩ አንዲት ግለሰብ በህገ-ወጥ መንገድ በርካታ የሀገር መከላከያ፣ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ የሌሎች ክልል ፖሊሶችን የደንብ ልብስ አልባሳትን፣ አርማዎችን ፣ ቀበቶዎችን ፣ መለዮችን ፣ጫማዎችን ፣ካቴናዎች፣ ወታደራዊ የውሃ መያዥ ኮዳዎችን በተከራዩት መጋዘን እንዲሁም በሦስት ሱቆች ውስጥ አከማችተው መያዛቸውን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ከበደ አስፋ አስታውቀዋል፡፡

ከእነዚህ ወታደራዊና ፖሊሰዊ ቁሶቁሶች በተጫማሪ አንድ ቦንብ፣ አንድ ሽጉጥ እና 267 የሽጉጥ ጥይቶች ከማጋዘኑ ውስጥ እንደተገኙ ከኮማንደሩ ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡ በወንጀሉ የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው መቀጠሉን እና መጋዘኑን የተከራዩት ግለሰብ ለጫማ ማስቀመጫነት መጋዘኑን እንደተከራዩት በምርመራ መረጋገጡን ኮማንደር ከበደ ተናግረው መንግስት እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የሀገር ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ትኩርት ማድረጋቸውን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም የወረዳው ንግድ እና ኢንዱስትሪ ያሸገውን መጋዘን በመክፈት ወንጀሉ መፈፀሙን ኮማንደሩ አስታውቀው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት በማስገባት በተጠናከረ መልኩ በጋራ እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

(ኢፕድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.