ሃገር በቀል ኢኮኖሚ ወይስ ሃገር ነቀል ኢኮኖሚ!!! - ሚሊዮን ዘአማኑኤል – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ሃገር በቀል ኢኮኖሚ ወይስ ሃገር ነቀል ኢኮኖሚ!!! – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

1 min read

የሃገር በቀል ኢኮኖሚ የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ ጡረተኛው ግርማ ብሩ የዘውረዋል፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ ባጫ ጊና የኦዴፓ ሹመኛ የጁዋር መሃመድን ‹‹ኦሮሞ ፈርስት›› የሴራ ፖለቲካ፣ እንደ ሮኬት አመጠቁ፣ ሆኖም ኢኮኖሚያችን፣ከከርሰ ምድር አዘቅት ተባብረው አጠለቁት፡፡ ባጫ ጊና 24 ባንኮች፣ በኦነግ ሸኔ ጃል መሮ ሲዘረፍ በመተባበር መግለጫ ሰጥተው አያውቁም!!! የተቀነባበረ ሴራ መሆኑ አብይ አህመድና ለማ መገርሳም ያውቁታል፡፡ በቄሮ ሠላም ያጣው የኦሮሞ ህዝብ የእልቂት ድግስ ደግሰውለታል፣ ኢንቨስተሮች ክልሉን ጥለው ወተዋል፣ የእርሻ ስራና ገበያ የለም፣ ትራንስፖርት የለም፣ መንገድ በቄሮ ይዘጋል፣ የኦሮሞ ህዝብ በመከላከያ ሠራዊት ኮማንድ ፖስት ተጠርንፎ ይገኛል፡፡ የኦነግ መሪዎችን የኦሮሞ ህዝብ የነቃ ጊዜ  ይበላቸዋል፡፡   

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከፍተኛው ድርሻ በአገልግሎት ዘርፍ መሪነት ሲከወን በተለይም በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የአንበሳውን ድርሻ ሲያስገኝ ቀጥሎም ከውጭ ንግድ ገቢ ከሚላኩ ምርቶች ቡና፣ ሰሊጥ፣ ጫት፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ አበባ፣ የቁም እንስሳት፣ ወርቅ ምርት ሽያጭ የሚገኙ  የውጭ ምንዛሪ ገቢዎች ናቸው፡፡ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ገቢ ዝቅተኛ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የባንክ፣ ኢንሼራንስ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ባቡር፣ ዓየር መንገድ፣ ወዘተ መንግስታዊ ዘርፍ ቁጥጥር ስር ናቸው፡፡

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ መሠረት በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆልና በሃገሪቱ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት  በታህሳስ ወር 2012ዓ/ም የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ19.5 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን በጥር ወር 25 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገልፆል፡፡

2020 እኤአ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እድገት ማለትም አመታዊ አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት (ጂዲፒ) 6.3 በመቶ እንደሚሆን ተንብዬል፡፡ በ2021 እኤአ 6.4 በመቶ፣ በ2022 እኤአ 7.1 በመቶ እንደሚሆን ተንብየዋል፡፡ በአንፃሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጂዲፒ ትንበያ መሠረት በ2019 እኤአ  9 በመቶ  ወደ 10.8 በመቶ ከፍ እንደሚል ተንብየዋል፡፡ የሃገሪቱ የምጣኔ ኃብት ዝግምተኛነት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋትና የህግ የበላይነት ጥሰት፣ የግልና መንግስታዊ ዘርፍ ግንባታዎች መቀዝቀዝና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ሳያጠናቅቁ ሌላ መጀመር የመሳሰሉት እንከኖች አንኮሮቹ ናቸው፡፡ የሃገራችን  ጉዞ ሃገር በቀል ኢኮኖሚ ለመገንባት ወይስ ሃገር ነቀል ኢኮኖሚ ውድቀት!!!

World Bank cuts Ethiopian growth forecast  “The annual inflation rate in Ethiopia was 19.5% in December 2019 and 25 % February 2020. ..The World Bank cut its forecast for Ethiopia’s economic growth in the 2020 fiscal year to 6.3 %, well below the government’s projection. Growth could increase slightly to 6.4 % in fiscal 2021 and 7.1% in 2022, according to the World Bank. …The National Bank of Ethiopia has forecast that Gross Domestic Product growth would accelerate to 10.8 for the fiscal year ending in July, up from a 9 % pace in fiscal 2019 as the government implements a blueprint expected to boost investment.’’1

የ2012 ዓ/ም የመጀመሪያው ሩብ አመት ዕቅድና አፈፃፀም፣

  • የግብርና ሚኒስቴር በ2012 ዓ/ም የመጀመሪያው ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም መሠረት በመላ ሀገሪቱ በእርሻ ልማት 13.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለመሸፈን ተችሎል፡፡ በመህር ምርት 382 ሚሊዩን ኩንታል የምርት ዘመን ይገኛል ተብሎ ይገመታል፡፡
  • በበጀት አመቱ ወደ ውጭ ከተላከው ቡና 284 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቆል፡፡
  • የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ2012 ዓ/ም የመጀመሪያው ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም መሠረት 17.2 ቢሊዮን ብር ከግብርና ታክስ ሰብስቦል፡፡ በ2011 ዓ/ም 16.7 ቢሊዮን ብር ከግብርና ታክስ ተሰብስቦ ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ2012 ዓም 48 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ አውጥቶል፡፡ በዚህም መሠረት 37 ቢሊዮን ከታክስ ዘርፍ እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ገቢን ሳያካትት 95 በመቶ ከግብር ከፋዩ ህዝብ ተሰብስቦል፡፡ መንግሥት የንግድ ፖሊሲ በማዘጋጀት፣ ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት መዘርጋትና የ10 አመት መሪ እቅድ በማዘጋጀት ኢኮኖሚውን ለማዘመን አቅዶል፡፡
  • ኢትዮጵያ በ2012 ዓ/ም ከውጭ ንግድ ገቢ 3.7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቆል፡፡ ከኢኮኖሚው ዘርፍች ውስጥ የ3.7 ቢሊዮን ዶላር ድርሻ ክፍል ውስጥ የግብርናው ዘርፍ የገቢውን 80 በመቶ (2 ቢሊየን 960 ሚሊዮን ዶላር)፣ከማምረቻ ዘርፍ 779 ሚሊዮን ዶላር፣ ከማዕድን ዘርፍ 261 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ከተለያዩ ዘርፎች ቀሪው ይሰበሰባል ተብሎ ታቅዶል፡፡ በዚህም መሠረት የ2012 ዓ/ም የመጀመሪያው ሩብ አመት ከውጭ ንግድ 723 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተገኝቶል፡፡ በሃገሪቱ የሚገኝ የወርቅ ማዕድን የኢዛና ወርቅ ማዕድን በህወሓት ተወስዶል እንዲሁም የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን በኦሮሞ ነፃ አውጭ (ኦነግ) የጦር አበጋዞች ተወስዶል፡፡ በዚህም ምክንያት በአመት ከ500 እስከ 600 መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኘው ዛሬ 30 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ገቢ በማሽቆልቆል ላይ ይገኛል፡፡ የክልሎች ኢኮኖሚ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ኢኮኖሚ በማሽመድመድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ክልሎች የራሳቸውን የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ የፖሊስ ኃይል፣ ሚሊሽያ፣ የደህንነት ሃይል፣ በአጠቃላይ የክልል የፖለቲካና የኢኮኖሚ ወታደራዊ ሃይል በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ክልሎች የእራሳቸው ባንዲራ፣ ብሄራዊ መዝሙር፣ የክልል መሬት ድንበር፣ ወዘተ ላለፉት 28 አመታት የሌለ የሃገረ-መንግሥት ታሪክ ትርክት ህወሓት/ ኢህአዴግና ጭፍሮቻቸው የፖለቲካ ሴራ ዛሬም በዶክተር አብይ አህመድ የብልፅግና መንግሥት ውርስነት ቀጥሎል፡፡
  • የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን 299 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን አራት መንገዶች ፕሮጀክት በ6.1 ቢሊዮን ብር ወጪ ለቻይና የመንገድ ሥራ ተቆራጮች ተሰጥቶል፡፡ አንደኛው የሃሙሲት- እሰቴ 76.6 ኪሎሜትር በ1,395,640,048 ብር፣ ሁለተኛ ጩለሴ- ሶያማ 90 ኪሎ ሜትር በ1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ፣ ሦስተኛ የአዲሴ-ግራዋ መንገድ 55 ኪሎሜትር በ1,436,800,000 ብር አራተኛ ጎዴ-ቀላፎ መንገድ 88.5 ኪሎሜትር በ1,530,000,000 ብር ወጪ ሁሉም ለብረት መዝጊያው የቻይና መንገድ ተቆራጮች ተሰጥቶል፡፡2

የ2012 ዓ/ም የሁለተኛው ሩብ አመት ዕቅድና አፈፃፀም፣

  • ኢትዮጵያ በ2012 ዓ/ም ከውጭ ንግድ ገቢ 3.7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቆል፡፡ የ2012 ዓ/ም የሁለተኞች ሩብ አመት ከውጭ ንግድ 607 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተገኝቶል፡፡
  • የ2012 ዓ/ም የአንደኛና የሁለተኞች ሩብ አመት እቅድ 1.66 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ፣  የውጭ ንግድ አፈፃፀም 1.33 ቢሊዮን  የአሜሪካ ዶላር ሆኖል፡፡
  • የብልፅግና ፓርቲ የሃገሪቱን የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ግብርና፣ ኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች የተለያዩ ሚንስትሮችና መስሪያ ቤቶች የሩብ አመት የእቅድና አፈፃፀም መረጃ ከህዝብ መደበቅ ጀምረዋል፡፡

 

በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር 40 ብር ከሃምሳ ይመነዘራል!!!

የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ምክረ-ሃሳብ፣ መሠረት ለኢትዮጵያ መንግሥት 2.9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታና ብድር ለመሰጠት ተስማማ፡፡ በአንጻሩም የኢትዮጵያ መንግሥት ኢኮኖሚውን ከመንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ግል ዘርፍ ፕራይቬታይዝ ማድረግና የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ ኢኮኖሚ እንዲወሰን ስምምነት አድርጋለች፡፡ በዚህም ምክንያት የአንድ ዶላር ዋጋ ተመን በጥቁር ገበያ 40 ብር ከሃምሳ በመመንዘር ላይ ይገኛል፡፡ መቶ ዶላር በ4,050 ብር ይመነዘራል፡፡ በዚህም የተነሳ በሃገሪቱ የዋጋ ግሽበት መባባሱንና በተለይ የምግብ ፍጆታ ወጪ 22 በመቶ መድረሱን መረጃ አስታውቆል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት በሦስት ይከፈላል፡፡

{1} አንደኛው ቆሚ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት (Fixed exchange Rate System) በገበያ ፍላጎት የማይመራ ተለዋዋጭ ያልሆነ ቆሚ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት  ነው፡፡ በጥቁር ገበያ የአንድ ዶላር ዋጋ እንዳሰኘው ቢለዋወጥም በመንግሥታዊ ባንክ ተመኑ ቆሚ ሆኖ ሲያገለግል ነው፡፡ በኢትዮጵያ በቀ.ኃ.ሥ እና በደርግ ዘመን ቆሚ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ነበር፡፡

{2} ሁለተኛው የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት (Managed floating  Rate System) የብሄራዊ ባንክ አስተዳደር በጥቁር ገበያ የአንድ ዶላር ዋጋ 40 ብር ቢሆንና በመንግሥት ባንክ ተመኑ 30 ብር ቢሆን የሁለቱን አማካኝ በመውሰድ 35 ብር እንዲሆን የሚወስኑበት ሥርዓት ነው፡፡

{3} ሦስተኛው፣ ነፃ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት (Free floating Rate System) በገበያ ፍላጎት የሚመራ ተለዋዋጭ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት  ነው፡፡ በጥቁር ገበያና በመንግሥታዊ  ባንክ ተመን የአንድ ዶላር ዋጋ በብር ተመኑ አንድ ሲሆን ነው፡፡

“The Ethiopia government has recently announced a three-years reform blueprint called “Homegrown Economic Reform” for the purpose of growth, job creation and poverty reduction. The government has also announced that it has secured roughly US$9 billion external finance  for the reform package.” 3

የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግሥት 9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታና ብድር ለመሰጠት ተስማማ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የሶስት አመት ‹‹የአገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ›› በማውጣት ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠርና፣ድህነት ለመቀነስ አቅዶል፡፡ ዶክተር አብይ ተጀምረው ያልተጨረሱ ፕሮጀክቶችን ብቻ እንጨርሳለን አዲስ አንጀምርም ያሉትን ቃል በልተውታል፡፡ ብድርና የዕዳ ጫና ሃገር በቀል ኢኮኖሚ አይገነባም!!! በተገላቢጦሽ ብድር ሃገር ነቀል ኢኮኖሚ የሃገር ውድቀትንና የህዝብ ድህነትን ያመጣል እንላለን፡፡

በኢትዮጵያ በገበያ ፍላጎት የሚመራ ተለዋዋጭ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት  ተግባራዊ እንዲሆን  የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተጽዕኖ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ መርሃ ግብር የሚሰጠውን 2.9 ቢሊዮን ዶላር ብድር አጽድቆል፡፡ በዚህም መሠረት ከብድሩ 308.4 ሚሊዮን ዶላር በአፋጣኝ ለኢትዮጵያ እንደሚሠጥ  አይ ኤፍ ኤም አስታውቆል፡፡

የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሦስት አመታት ውስጥ

{1} የውጭ ምንዛሪ ተመን፣ በ2017 እኤአ መንግሥት የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን 15 በመቶ እንዲቀንስ በማድረጉ ኢኮኖሚው አዘቅት ውስጥ እንዲገባ ወያኔ/ ኢህአዴግ ሲያደርግ አዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ደግሞ ነፃ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት ማለትም በገበያ ፍላጎት የሚመራ ተለዋዋጭ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት  በአገሪቱ ሲዘረጋ የጥቁር ገበያና በመንግሥታዊ  ባንክ ተመን የአንድ ዶላር ዋጋ በብር ተመኑ አንድ ይሆናል ማለት ነው፡፡  ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባው የኢንዱስትሪ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማሽነሪዎች፣ ነዳጅ ወዘተ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ከውጭ ንግድ የግብርና ምርቶች በመላክ ተጠቃሚ መሆን አይቻላትም፡፡ በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር 40 ብር ከሃምሳ ይመነዘራል!!! የአንድ አገር የውጭ ምንዛሪ ተመን ጥንካሬ ከሚወሰንባቸው ነገሮች ውስጥ (1.1) የውጭ ምንዛሪ አቅርቦታና ፍላጎት (1.2) በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የገበያ ኃይሎች ሁኔታ (1.3) የዋጋ ግሽበት ሁኔታ እንዲሁም (1.4) የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሁኔታ የሃገሪቱን ገንዘብ ጥንካሬ ይገልፃል፡፡ በዚህ መሠረት በአፍሪካ አህጉር ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃ ያላቸው ጠንካራ ሃገራቶች የሊቢያ ዲናር፣ የቱኒዝያ ዲናር፣ የጋና ሲዲስ፣ የሞሮኮ ዲናር፣ የቦትስዋና ፑላ፣ የዛምቢያ ካዋቻ፣ የስዋዚ ሊላንጂኒ እና የደቡብ አፍሪካ ራንድስ ይገኙበታል፡፡4

{2} የውጭ ምንዛሪ እጥረትን በዘላቂነት እንድትፈታ ለማድረግ  9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታና ብድር በመስጠት ተቀማጭ የውጭ ምንዛሪያችን በብድር ገንዘብ እንዲደገፍ አድርገዋል፡፡ የሃገሪቱ የውጭ ንግድ ገቢ ተስፋ እንደሌለው ጠቆሚ መረጃ አይኤም ኤፍና የዓለም ባንክ ተገልፆላቸዋል፡፡ ሃገሪቱ በብድንና በእዳ ጫና ወጥመድ ውስጥ ወድቃለች፡፡የሀገሪቱ እዳ ከ50 እስከ 65 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ የውጭ ንግድ ገቢ ከሞሸሸ እዳችንን እንዴት እንከፍላለን፣ እንኮን እዳ የብድራችንን ወለድ መክፈል ይሳነናል፡፡

{3} በገበያ ፍላጎት ሥርዓት የሚመራ ተለዋዋጭ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት መዘርጋት ይጠበቅብናል፡፡

{4} የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የዕዳ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የአስተዳደርና ቁጥጥር ሥርዓቱን ማጥበቅ እንዲሁም

{5} የአገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን ማጠናከር በሌላ በኩል በገቢዎች ሚኒስቴር የሃገሪቱ የግብርና ታክስ ገቢ የመሰብሰብ አመታዊ እቅድ 235 እስከ 347 ቢሊዮን ብር ሲገመት ከጂዲፒው ከ12 እስከ 15 በመቶ ድርሻ እንዳለው ይገመታል፡፡ “The next budget proposal stands at 346.9 billion Br, out of which the government targets to collect 235.7 billion Br, almost 90pc of this from tax revenue by the federal government.” 5 በሃገሪቱ ከሚገኙ ከተሞች አዲስ አበባ (48 ቢሊዮን ብር ግብር ይሰበሰባል)፣ አዋሳ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ መቀሌ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ሀረር፣ ጅማ፣ ወዘተ የሚሰበሰበው የከተሞች ግብርና ታክስ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝ ይታመናል፡፡ ሃገሪቱ ከአፍሪካ አህጉር ዝቅተኛ የግብርና ታክስ ገቢ እንዳላት ይታመናል፡፡ በሌላ በኩል የክልል መንግሥቶች ከግብርና ታክስ የሚገኙት ገቢ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህም የተነሳ የፌዴራል መንግስት ለዘጠኙ ክልሎች በመደበኛ በጀትና ለክልሎች ድጎማ በማድረግ ከፍተኛውን በጀት እንደሚሰፍርላቸው ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት መብት መሠረት የክልል መንግሥቶች ቁጥር ሃያ፣ ሠላሣ፣ አርባ፣ ሃምሳ እየደረሰ በመጣ ጊዜ የሚከፋፈሉት በጀት ዝቅተኛ ይሆናል ብሎም ኃብታም ከተሞች ለደሃ ክልላዊ መንግሥቶች የሚቀራመቱት ኃብት፣ድህነትን ተከፋፍለው (Distribution of poverty) ‹‹ጨዋታ ፈረሰ፣ ዳቦ ተቆረሰ››ይባባላሉ፡፡

{6} የመንግሥት ወጪን መቀነስ አስተዳደራዊ ወጪዎችን መቆጠብ፣የመሳሰሉት ለውጦች የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ በሃገራችን የመንግሥት ወጭ ይጨምራል እንጂ ሲቀንስ አይታይም፣ የመንግሥት በጀት ለመደበኛና ለክልሎች ድጋፍ የሚመደበው ወጪ ከፍተኛ ሲሆን ለዘጠኝ ክልሎች፣ አስረኛው ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሃድያ፣ ከፋ፣ ወዘተ እየተጨመሩ በመጡ ቁጥር የመንግሥት አስተዳደራዊ ወጪ እየጨመረ መሄዱ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው፡፡ በሃገሪቱ የመከላከያ ኮማንድ ፖስት ተጨማሪ በጀት እያለ የመንግሥት ወጪ ሊቀንስ አይችልም ስለዚህ ሃገሪቱ በብሄር፣ በዘርና የተከፋፈለ አስተዳደራዊ ሥርዓትን ከህገመንግሥቱን በመቀየር በድንበርና የታጠሩ ክልሎችን በማጥፋት ሃቀኛ ፌዴራለዊ ሥርዓት በመመስረት ሃገሪቱ የሁሉም ዜጎች በማድረግ ከቦታ ቦታ ሰዎች ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ በማድረግ የኢኮኖሚ ብልፅግና ማግኘት ብቻ ነው ያለው አማራጭ እንላለን፡፡

በኢትዮጵያ በገበያ ፍላጎት የሚመራ ተለዋዋጭ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት  ተግባራዊ ሲሆን ሊከሰት የሚችለው አደጋዎች ውስጥ

{1} የኢትዮጵያ ብር ዋጋ ተመን መቀነስ፣ የብር የመግዛት አቅም መዳከምና መሽመድመድ ያስከትላል፡፡ የዋጋ መናር ወይም ግሽበት ያስከትላል፡፡ 17 በመቶ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበትና 23 በመቶ የምግብ ዋጋ ግሽበት ተከስቶል

{2} የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ሃገራችን ገብተው እንዲሰሩ ማድረግ አልተቻለም፡፡

{3} በ2012 ዓ/ም አስቸኮይ የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 10.6 ሚሊዮን ሲሆን ከዚህ ውስጥ 3.3 ሚሊዮን  በኦሮሚያ፣2.4 ሚሊዮን በሶማሌ፣1 ሚሊዮን በአማራ 2.1 ሚሊየን የሃገር ውስጥ ተፈናቆይች የአስቸኮይ ጊዜና የስብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዓለም ባንክ ጥናት መሠረት በ 30 ሚሊዮን ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ፈጠራ አለመኖር

{4} ዶክተር አብይ አህመድ መጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ከ2500 ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

{5} ህወሓት የትግራይን ክልል ይዞ ተገንጥሎል፡፡ ኦነግ ሸኔ ወለጋ ጠቅላይ ግዛትን ይዞ ተገንጥሎል፡፡ ነገ የህዳሴው ግድብ በኦነግ ይታገታል!!! የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን በኦዴፓ ተወርሶል!!! በድሬዳዋና ሃረር ከተሞች ቄሮ ሜንጫ ይዞ ህዝብን አላሰራ ብሎል፡፡ በሁሉም ክልሎች ሰላምና መረጋጋት ጠፍቶል፣ የህግ የበላይነት አልተከበረመረ፡፡ በዚህም ምክንያት ኢንቨስትመንት ቀዝቅዞል፣ የሃገር ጎብኝዎች ቁጥር ተመናምኖል፡፡ በህዝብ እንቢተኛነትና አመፅ የተቃጠሉ ፋብሪካዎች፣ የአበባ እርሻዎች፣ መጋዘኖች መኪኖች፣ ትራክተሮች ወዘተ ለባለሃብቶቹ ግማሽ ቢሊዮን ብር መንግሥት እንደሚክስ ገልፆል፡፡ በ2012 ዓ/ም በመላ ሃገሪቱ በአጠቃላይ 60 በመቶ የሃገሪቱ ህዝብ በመከላከያ ኮማንድ ፖስት ስር ይተዳደራል፣ በዚህም የተነሳ የመከላከያ ሠራዊቱ  በጀት ከፍተኛ ወጪ አስከትሎል፡፡ የመንግሥት ወጭ ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ እንዲሄድ ገሃድ ሃቅ ሆኖል፡፡

በግፍ ለታገቱ  ለአማራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መታሰቢያ ትሁን!!! አጋቾች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ምንጭ

{1}  www. Tadias.com/01/09/2020/World Bank- cuts- Ethiopian- growth- forecast/

2} ህዳር 25/2012 ኤፍቢሲ

{3} Tsegaye Tegenu (Ph) 20/9/12

{4} The 8 strongest currencies in Africa in 2019

{5} https://addisfortune.net/columns/authority-gets-tough-as-revenues-disappoint/

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.