"የምኒልክን ቤተመንግስት የግላችን አድርገን፣ የነ ታደሰ ብሩን ሀውልት እናቆምበታለን።" መረራ ጉዲና፥ (ሰላሌ ላይ ከተናገረው) – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

“የምኒልክን ቤተመንግስት የግላችን አድርገን፣ የነ ታደሰ ብሩን ሀውልት እናቆምበታለን።” መረራ ጉዲና፥ (ሰላሌ ላይ ከተናገረው)

1 min read
1

ትርጉም ዶ/ር Abreham Alemu)
—–
ፕ/ር መረራ ጉዲና logical ሰው ነው፣ በወለጋ የሚሽነሪ አክራሪ ጎሰኞች መዝገብ ውስጥ የለም ብዬ፣ ልክ እንደኔው ኩሩ የሰላሌ-ኩዩ እና የሜታ-አድአ በርጋ ዘመዶቼ ደህና ሰው፣ የገረሱ ዱኪ ዘር፣ የአብዲሳ አጋ ዘር፣ አድርጌ እቆጥረው ነበር።

“ተው ኤፍሬም፣ አታውቀውም እሱን፣ ስነግርህ” ብሎኝ ነበር አንድ ወዳጄ። አልሰማሁትም። አሁን ግን መረራ ራሱን ገለጠ። ምናልባት የደጋጎቹ ቅዱሳን ሀገር ሰላሌ የማይቋረጠው ጸሎተ ማርያም አፉን ከፍቶ ፊቱን ጸፍቶ አናግሮታል ብዬ ነው የማምነው።
——
ፕ/ር መረራ በአንተ ላይ የነበረኝን “የተስፋ ፋይል” ዘግቼ በነበቀለ ገርባ ሳጥን ውስጥ እንዲቆለፍበት ወደ መዝገብ ቤት መርቼዋለሁ።
አድዮስ።

1 Comment

 1. xxxxxx መራራ መረረ ።xxxxx

  በሺህ የሚቆጠሩትን ሰዎች፣ወንድ፣ሴት፣ ህሕፃናት፣ሽማግሌዎችንና ባልቴቶችን ወጣቶችን ከዩነቨርስቲ ሳይቀር የገደለባቸውን ቡድን፤ ደማቸውን ደመ-ከልብ አድርገው ያለ ዕርቅ የተጎዳኙት ትልቁ ምክንያት ምንድነው ?አገር ለማግኘት ? ያውም ከካሃዲዎች?
  መጽሐፈ ኢዮብ ፴፫ ፲፬
  “እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ሰው ግን አያስተውለውም።መራራ መረረ ።”
  Politicians are the same all over. They promise to build a bridge even where there is no river. ~Nikita Khrushchev For Juar Mohammed
  In order to become the master, the politician poses as the servant. ~Charles de Gaulle For Lemma Megeressa
  Those who are too smart to engage in politics are punished by being governed by those who are dumber. ~Plato? For Professor Merara Gudina
  DO WE UNDERSTAND EACH OTHER NOW???…
  Instead of giving a politician the keys to the city, it might be better to change the locks. ~Doug Larson
  Politics is the gentle art of getting votes from the poor and campaign funds from the rich, by promising to protect each from the other. ~Oscar Ameringer

  ምነው የወንዜ ሰው፣
  ልብህ ትል ፈጠረ?
  ሌጌዎን ገባህ ወይ
  ሕሊናህ ያረረ።
  እሬት እሬት አለ፤
  እያለሳለስ፤
  ከኮሶውም ባሰ።
  እየጎፈነነ፤
  እኛን አሳዘነ።
  የሬት ፍናፍንት ጠባይ፤
  በዘሩ ሳይታይ፤
  እንደጣዝማ ልብን
  እየሰረሰረ፤
  በፖለቲካ ትግል
  መረራ መረረ።
  እሱስ ዕድሜ ልኩን
  ፖለቲካ ብሎ፤
  ለአገር ነፃነት
  ለሰው ልጆች ታግሎ።
  መብቱ ነው እንዳሻው
  የትም ቢገላበጥ፤
  የሌላውን ሳይወስድ
  ለፈለገው ቢሰጥ።
  ግና ሆነ ብሎ
  ከሕዝቡ አስበልጦ፤
  ለሌላ ፀረ-ሕዝብ
  ቢያደላ በምንም፤
  ክህደት ነው የሬቱ
  ያጋጫል ህዝቡንም።
  ለምሳሌ ጁዋር
  በወንጀል ሲፈለግ፤
  ባለሥልጣን ጉያ
  ሁሌም ነው ‘ሚሸሸግ፤
  ዋሻ አጥቶ ሊመሽግ
  ደጅ ሲጠናቸው፤
  ፋሺሽቶቹ ገቡ
  በድብቅ ፓርቲያቸው።
  ያ ገርባ ገሪባ የናት ጡት ነካሹ፤
  ሄዷል ከዋሻቸው ታሪክ ሊያበላሹ።
  ዕውነት ግን ከሆነ
  የሚወራው ሁሉ፤
  ከእንዲህ ዓይነት ፓርቲ
  በደም እንዳትበሉ።
  መራራ ነው ደሙ
  ሥጋ ሀሞት ቢሆንም
  እሬት እሬት ከሚል
  አይብስም በምንም።
  እናም እንደጣዝማ
  እየሰረሰረ፤
  በፖለቲካ ውስጥ
  መረራ መረረ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.