አቶ ትግስቱ አወሉ ራሳቸውን ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም አገለሉ - ተስፋዬ ኃይለማርያም – ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha): Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

አቶ ትግስቱ አወሉ ራሳቸውን ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም አገለሉ – ተስፋዬ ኃይለማርያም

1 min read

በ750 ሺህ ብር የዕድር ገንዘብ ማጉዳል ሲፈለጉ ነበር

አቶ ትግስቱ አወሉ ከፌዴራሊስት ሃይሎች ፎረም ራሳቸውን ማግለላቸወን አስታወቁ ሲል ፕሬስ መምሪያ በማህበራዊ ገጹ ዘግቧል።

አቶ ትግስቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ የፌዴራሊስት ሃይሎች በሚል የተሰባሰበው ሃይል ህወሓት ዳግም የበላይነቱን ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው።

እንደ አቶ ትግስቱ ገለጻም፤ ይህ ፎረም የኢትዮጵያን ህዝብ ዳግም ለማስለቀስ ያለመ ነው።

ህወሓት የብልጽግና ፓርቲ አሃዳዊ ነው የሚለው የብሄር ብሄረሰቦችን ቀልብ ለመሳብና የስብስቡ አካል ለማድረግ ነው ያሉት አቶ ትግስቱ፤ የፎረሙ አላማና አካሄድ የህወሓትን የበላይነት ለመመለስ ያለመ በመሆኑ ራሳቸውን ከፎረሙ ምክትል ሰብሳቢነት ጭምር ማግለላቸውን አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕብር ሬዲዮ ከሳምንታት በፊት ባቀረበውን ዘገባ በአዲስ አበባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካባቢ የሚገኘው ቅዱስ ሚካኤል ዕድርን በሊቀመንበርነት በመራበት ወቅት 750 ሺህ በማጉደል ተጠርጥሮ ክስ የተመሰረተበት ሲሆን ከቀናት በፊት ፍርድ ቤት ባለመቅረቡ ሲፈለግ ነበር። ተስፋዬ ኃይለማርያም ያወጣውን ዘገባ በዲሴምበር 10/2019 በህብር ማህበራዊ ገጽ አውጥተን የነበረ ሲሆን ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ እንዲያነቡት እንጋብዛለን።

የተለጣፊው አንድነት መሪ ትዕግስቱ አወሉ በ750ሺህ ብር የዕድር ገንዘብ በማጭበርበር ክስ ተመሰረተበት

ሰሞኑን ሕወሓት በጠራው ጉባዔ ላይ ከተገኙት አንዱ የተለጣፊው አንድነት መሪ ነኝ ባዩ ትዕግስቱ አወሉ የዕድር ገንዘብ በማጭበርበር በልደታ ፍርድ ቤት ክስ እንደተመሰረተበት መረጃው ወጥቷል። የተስፋዬ ኃይለማርያምን ትዝብት እክል ዘገባ ያንብቡት ሼር ያድርጉት

ትግስቱ አወሉ፣
መሸጥ የለመደ….

ወዳጄ ተስፋሁን አሰፋ አንድ ጠቃሚ መረጃ አቀበለኝ። መረጃውን ከተቀበልኩ በኋላ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን በማነጋገር እነሆ ለሕዝብ አቀረብኩት። ዕድሜ ለ Citizen Journalism .

ትግስቱ አወሉን የምናውቀው ለኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ የነበረውን ታላቁን አንድነት ፓርቲ በማፍረስ በወርቅ ሰሃን አድርጎ ለወያኔ የሸጠ ሰው መሆኑን ነው።

ትግስቱ አወሉ ከኤርትራ ተፈናቅሎ ሲመጣ ችግሩን በማየት በህዝቡ አስተባባሪነት ቤት እንዲሰጠው ተደረገ። በሚኖርበት አካባቢ የዕድር አባል ሆኖ ሲኖር በለመደው አፍራሽነቱ የዕድሩን አመራሮች በማውረድ ራሱ የዕድሩ ሊቀመንበር ሆነ።

ትግስቱ አወሉ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካባቢ የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ዕድር ሰብሳቢ ዳኛ ሆኖ ሲስራ የዕድርተኛውን ብር 750,000.00 (ሰባት መቶ አምሳ ሺህ ብር) ለግል ጥቅሙ በማዋሉ ልደታ በሚገኘው ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበታል።

ትግስቱ አወሉ የቅዱስ ሚካኤልን ዕድር ካዝና በመገልበጡ ለስድስት አባላት ሞት እርዳታ የሚከፈል ገንዘብ በመጥፋቱ ከተወሰኑ አባላት ኪስ ወጥቶ ሊሸፈን ችሏል። ትግስቱ ለስድስት ዓመት ያህል የዕድሩን ገንዘብ ባንክ ካለማስገባት በተጨማሪ ” አክስዮን እመሠርታለሁ” በሚል ሰላሳ ሰዎችን በማጭበርበርና በጠቅላላው በአራት ወንጀሎች ተከሶ የክስ መጥሪያውን እንዲወስድ ሲጠራ “መቀሌ ስብሰባ ላይ ነኝ” የሚል መልስ ሰጥቷል። በቀጣይ ታህሳስ 11 እንዲቀርብ የተወሰነ ስለሆነ፣ በቦታው ተገኝተን የክስ ሂደቱን ተከታትለን እናቀርባለን።

እኛ እንደምናውቀው የታቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ላይ ክስ የሚመሰረትባቸው ለዴሞክራሲና ለእኩልነት በሚያደርጉት ተጋድሎ እንጂ እንደ ትግስቱ የደሃ ህዝብ መረዳጃ ዕድርን ገንዘብ ሲመዘብሩ አይደለም።

አንድነት ፓርቲን ለወያኔ የሸጠ ግለሰብ፣ የሰፈሩን ድሆች ገንዘብ የመዘበረ ቁጭ በሉ ሰውዬ በየትኛው ሞራሉ ኢትዮጵያን ሊመራ ያስባል? የኑሮ ውድነት ያደቀቀውን ነገ የሞት አደጋ ቢደርስብኝ ቤተሰቤን ከመሸማቀቅ ይታደገኛል ብሎ ያሰባሰበውን የደሃ ህዝብ ገንዘብ መዝረፍ በየትኛው መመዘኛ ሊመዘን እንደሚገባው አይገባኝም። የመቀሌዎቹ ጌቶቹ ከዚህ ክስ ሊያስጥሉት አይችሉም። ክሱን ከመሠረቱት መካከል ያነጋገርኳቸው ሰው “ከዚህ በፊት በዕድሩ ስብሰባ ላይ የተበሳጨው ዕድርተኛ ካልገደልነው ብለው በመነሳታቸው፣ እኛ ደርሰን አድነነዋል” ብለውኛል።

ትግስቱ ሆይ! እዚህ መምጣት የምትችል አይመስለኝም። ስለዚህ እዚያው መቀሌ ፕላኔት ሆቴል እነ ጌታቸው አሰፋን ጥገኝነት ብትጠይቅ ይሻልሀል።
ተስፋዬ ኃይለማርያም
ማስታወሻ
በእስር ገንዘብ ማጭበርበር ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው የተለጣፊው አንድነት መሪ አቶ ትዕግስቱ አወሉ ክሱን ለማስተባበል ወይም የተቃውሞ አስተያየት ካላቸው የእሳቸውንም ሀሳብ እናስተናግዳለን።