34 የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን የባንክ አካውንት ማሳገዱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

34 የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን የባንክ አካውንት ማሳገዱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ

1 min read
4
ሱር ኮንስትራክሽን ፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር ፣ሜጋ ማተሚያ፣ ኢፈርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሁም ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢስነስ እገዳ ከተጣለባቸው ተቋማትመካከል ናቸው፡፡
ኢቢሲ

4 Comments

 1. ጅብ ካለፈ ዉሻ ጮኸ አሉ? ስልጣን ላይ ሲወጣ በመጀመሪያዉ ቀን ተነግሮት ነበር አብይ አባዱላን አድናለሁ ወንጀለኛ ትግሬን አድናለሁ ሲል አገር ገደለ። አሁን ምን ሊያገኝ ነዉ ገንዘቡ ሁሉ ወደ ዶላር ፓዎንድ ዩሮ ተለዉጦ ባህር ማዶ ሂዷል። አሁን ተወረሱ የተባሉት ድርጅቶችም የባንክ እዳቸዉን ከሸፈኑ ትልቅ እድል ነዉ።የሚገርመዉ ይሄን ይዘዉ ብራቮ እያሉ የሚያራግቡትን ነዉ።አዜብ እዉነትም ጉሊት ልትቀመጥ ነዉ ማለት ነዉ?

 2. እንደ አቶ ሰመረ ወደ ኋላ ተመልሼ ጠ/ሚሩን በአሁኑ ሰአት ልወቅስ አልችልም። በሰላም ነገሮችን ለማጠናቀቅ በመደመር ሂሳብ ሞክሯል። ችግሩ ሃበሻው እንደ ተልባ በአንድ በኩል ሲቆጥሩት በሌላ በኩል እየተሸራተተ ለዚህ ደርሰናል። ወያኔ በዘመኑ ሁሉ የሰው ልጆች ህልውና ተሰምቶት አያውቅም። ለዚያም ነው እንዴት ከ 20 ዓመት በላይ አብሮት ቀበሮ ጉድጓድ የኖረን ሰራዊት ይመታል ሲሉ ግርም የሚለኝ። አጠገብህ ሆኖ ጦር ሲያሰለጥን፤ እዋጋለሁ ብሎ ሲፎልል ከትግራይ ተራራና ረባዳ ስፍራዎች ጋር ራሱን ለማላተም እንዳልሆነ የ 5 አመት ልጅ ይገባዋል። ሆን ተብሎ ያለ የሌለ የሃገሪቱ የጦር እቃ ትግራይ እንዲከማች የተደረገውም ለዚሁ ተንኮል እንዲረዳቸው ነው። ውጊያውንና አፈናውን ከመክፈቱ ከሰአታት በፊት ከጠ/ሚሩ ጋር ያወራው ዶ/ር ደብረጽዪን አዲሱን ብር ላክ ሲል ሁለት ነገሮችን ለማረጋገጥ ነበር። አንደኛ እንደጠየቀው ገንዘቡ እንዲደርስ፤ ሁለተኛ ጠ/ሚሩ የሰሙት ጉዳይ ካለ ባህሪያቸውንና መልሳቸውን ለማንበብ እንዲመቸው ነው። ጠ/ሚሩ ግን ተበልተዋል። ልክ 1.3 ቢሊዪን ብሩ መቀሌ እንደገባ እና የጦሩ ስንቅና ደምወዝ በእጃቸው እንደገባ ነበር አፈናና ግድያውን የጀመሩት። ወያኔ ሰው በላ አራዊት ነው። አሁን ወደ ሱዳን ተሰደድ ተብሎ የሚነገረን ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችም በወያኔ ካድሬዎች እየተገፉ የሚሻገሩ እንጂ የትግራይ ህዝብ ስደትን ያውቀዋል ጭራሽ ቤቱን መልቀቅ አይፈልግም። ያው ከሞት ከተረፍን የጀርባ ደጀን ይሆኑናል በማለት ነው በውሸት ቅስቀሳ ህዝባችን የሚያመሳቅሉት። ህዝባችን ሊነቃ ይገባል። ምንም ይሁን ምንም በዘር የተለከፉ ሰይጣኖች ስለሆኑ ድልድይ ከማፍረስ፤ የሃይል ማመንጫዎችን ከመደምሰስ ወደ ኋላ አይሉም። በመሃል ሃገር በወያኔ ጄኔራሎች ስም፤ በአባሎቻቸው፤ በልጆቻቸው፤ በሚስቶቻቸውና በቅምጦቻቸው ያሉ ሃብቶች ሁሉ መወረስ አለባቸው። ማንን እያደሙ የማንን ሃብት ይበላሉ? ሲጀመር በስርቆትና በዝርፊያ የተገኘ ሃብት በመሆኑ ተጣርቶ መያዝ አለበት። አሁን የጤና ጥበቃ ስራውን ትቶ ከግብጽና ከሌሎች ሃገሮች መሳሪያ ለመግዛት የሚደራደረው ቴድሮስ አድሃኖም ሃብቱና ንብረቱ ሊያዝ ይገባል። ደም አፍሳሹ እና ዘረኛ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ አረመኔና ዘራፊ እንደነበር ከእርሱ ጋር ይሰሩ የነበሩ በምሬት ይናገራሉ። በአዲስ አበባ በእምነ በረድ የተሰራው ቤቱ ከህዝብ ገንዘብ የተዘረፈ ለዚያውም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የጋራ ዝርፊያ የተሰማሩ በተከፋፈሉት የተገነባ ቤት ነው። ሃገሩን ክዶ ከወያኔ ጋር መሰለፉ በበላበት መጮኹ ነው። ያለ ምንም ትምህርትና ወታደራዊ ልምድ ጄኔራል፤ ኮሎኔል ገለ መሌ እየተባሉ ከደሞዛቸው በላይ የሚኖሩትን የወያኔ አሽከሮች ሁሉ ጡረታቸው እንዲቋረጥ፤ ምንም አይነት ጥቅማ ጥቅም እንዳይደርሳቸው ማድረግ ተገቢ ነው። የሃገር ውስጥ የገቢና የሃብት ምንጫቸውን ካደረቁ በህዋላ በውጭ በስማቸውንም ሆነ በሌላ መንገድ የደበቁትን ለማጋለጥ ትልቅ ተጋድሎ መደረግ አለበት። በተለይ ያለ ልክ የናጠጡ የወያኔ ባለሃብቶች የእነርሱ ገንዘብ መደበቂያ በመሆናቸው ሊኮላሹ ይገባል። በምንም ሂሳብ የሚታመኑ ሰዎች አይደሉም። የዘመናት ታሪካቸው የሚያስረዳው ይህኑ ነው። አይን ያለው ፈልጎ ያንብብ። የራሳቸው ታጋዪች የሚሉንን። ጀሮ ያለው ይስማ። ስንቱን ነው መርዝ እያበሉ የገደሉት? ስንቱ ነው ታፍኖ የት እንደገባ ሳይታወቅ የቀረው?
  ወያኔ ድልድይ አፈረሰ፤ ወያኔ ሰው ጠፍሮ አስሮ ገደለ፤ ወያኔ ህጻናትን ወደ ጦርነት አስገባ ወዘተ ይባላል። ያለ መረጃ ቢለፈልፉት ዋጋ ቢስ ነው። አለም እንዲያውቀው ሁሉ ነገር በባለሙያ ተሰባስቦ ለህዝባችንና ለአለም መቅረብ መቻል አለበት። አሁን ሁሉ ነገር ፍንትው ብሎ ይታያል። እነ ጀዋር ለምን ወያኔ አፍቃሪ እንደ ነበሩ ገባኝ። ለካ የኦነግ ጦር ከአስመራ በመቀሌ በኩል ሲመለስ ወያኔ ትልቅ አቀባበል ያደረገለት የተሳሰሩበት ነገር በመኖሩ ነው። ለካ በመሃል ሃገር በቆንጭራና በገጀራ አማራው እየተለየ የታረደው ወያኔ ጋ ቂጣቸውን ገጥመው ነው። አይ ሃገር በተልኮ መኖር። ሰው ገድሎ ሬሳ ላይ መጨፈር። ዶ/ር መራራን ጨምሮ የኦነግ አመራሮች ለካ በአዲስ አበባ ይህንና ያን ሲሉ የነበሩት በመቀሌ ያሉት ስውር ወታደሮቻቸው ሁኔታ እንዳይታወቅ ነበር። ይገርማል። ሁሉም ነገር ወደ ብርሃን ሲመጣ በበርሚል የተደበቀው ገንዘብና የጦር መሳሪያ በከተማ እንደ ቆሻሻ መጣል ተጀመረ።
  እነዚህ የታገድት የወያኔ ኩባኒያዎች ባህርን በጭልፋ እንዲሉ እንጂ ገና ብዙ አለ። በየከተማው ያሉ ሱቆች፤ ም/ቤቶ፤ ሆቴሎች፤ የማመላለሽና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ወዘተ በወያኔ ሰንሰለት ውስጥ ናቸው። ጥብቅ ማጣራት ማድረግ አስፈላጊ ነው። የበላበትን እጅ ነካሽ ወያኔ አብቅቶለታል። በውጭና በሃገር ውስጥ በተለይም በመ/ቤቶችና በወታደራዊ ተቋማት ካልፈረሰ ለሃገርና ለህዝብ ፈተና መሆናቸው አይቀሬ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ከመረጃ ጋር ለአለም የጤና ጥበቃ ስለ ወያኔው ተላላኪ ዶ/ር ቴድሮስ ደብዳቤ በመጻፍ ሥራውን በመተው የመሳሪያ ነጋዴ መሆኑ ማሳወቅ አለበት። እኛም ጽፈናል። መልስም ተሰቶን እየተከታተሉት እንደሆነ አውቀናል። እሱን ብቻ ሳይሆን ረዳቱንም ጭምር። ብርሃነ ከሃገር ከገባ መታሰር አለበት። እርግጥ ነው ከግብጽ መሳሪያ በግዢም ሆነ በልመና ሞክሯል። ሌሎችንም እዚህ ላይ መጥቀስ የማንፈልጋቸውን ሃገሮችን እየሞከረ ነው። ከሃዲ ሌባ ነው። ግን ወያኔ ሆኖ ሌባና ከሃዲ ያልሆነ ማግኘት አይቻልም። በቃኝ!

 3. የእነዚህ ዝርፍያ ቡድን ድርጅቶች ዕገዳ ቢዘገይም አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ ድርጅቶች እኮ ስንቱን ምስኪን ድርጅት እና ተቋማትን ከገበያ ውጪ በማድረግ በሞኖፖል ገበያውን ተቖጣጥረው ስንቱን ከገበያ ውጪ አድርገዋል፡፡ ይህ እራሱ በሙስና ኮምሽን መጣራት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ የፖለቲካ አቅም ለመፍጠር ኢኮኖሚውን መቆጣጠር በሚል የዝርፍያ ፖሊሲ አገሪቷን ወደ መቀመቅና ችግር ከተዋታል፡፡ መቀሌንም ፓሪስ ለማድረግ፡፡

  ባንክ ብሎክ ማድረግ ተገቢ ሲሆን ሌላ ያላቸውን Financial Source በመለየት ማቋረጥ ይገባል፡፡ በውጪ አገር ባንኮች ያለ ዶላርና ሃብት እንዲታገድ በማድረግ ለዝች ደሃ አገርና ህዝብ ኢኮኖሚክ ማሻሻያ እንዲውል ከአሁኑ መሰራት አለበት፡፡ አገራችን ለአለፉት 30 ዓመታት በተቀነባበረ ዝርፍያ ባይፈፀምባት ኖሮ ድሮ በነመለስ የዲስኩር ፖሊሲ የነፍሰ ወከፍ ገቢን መካከለኛ ለማድረስ በውሸት ሲያልሙት የነበረው በተቻለ ነበር፡፡ ስንት Infrastructures, Schools, Health Center ወዘተ ለዚህ ምስኪን ህዝብ በተሰራ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ከጁንታው ነፃ ስትወጣ ብዙ የሚጣሩ ስራዎች ለመንግስት ይኖራሉ Fair Distribution of Income እንዲኖር፡፡ ስንቶቹስ የነሱ ንክኪ ድርጅቶችና ግለሰቦች ዘርፈዋል፣ ከብረዋል ከዚች ምስኪን አገር፡፡
  ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡

 4. የእነዚህ ዝርፍያ ቡድን ድርጅቶች ዕገዳ ቢዘገይም አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ ድርጅቶች እኮ ስንቱን ምስኪን ድርጅት እና ተቋማትን ከገበያ ውጪ በማድረግ በሞኖፖል ገበያውን ተቖጣጥረው ስንቱን ከገበያ ውጪ አድርገዋል፡፡ ይህ እራሱ በሙስና ኮምሽን መጣራት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ የፖለቲካ አቅም ለመፍጠር ኢኮኖሚውን መቆጣጠር በሚል የዝርፍያ ፖሊሲ አገሪቷን ወደ መቀመቅና ችግር ከተዋታል፡፡ መቀሌንም ፓሪስ ለማድረግ፡፡ ባንክ ብሎክ ማድረግ ተገቢ ሲሆን ሌላ ያላቸውን Financial Source በመለየት ማቋረጥ ይገባል፡፡ በውጪ አገር ባንኮች ያለ ዶላርና ሃብት እንዲታገድ በማድረግ ለዝች ደሃ አገርና ህዝብ ኢኮኖሚክ ማሻሻያ እንዲውል ከአሁኑ መሰራት አለበት፡፡

  አገራችን ለአለፉት 30 ዓመታት በተቀነባበረ ዝርፍያ ባይፈፀምባት ኖሮ ድሮ በነመለስ የዲስኩር ፖሊሲ የነፍሰ ወከፍ ገቢን መካከለኛ ለማድረስ በውሸት ሲያልሙት የነበረው በተቻለ ነበር፡፡ ስንት Infrastructures, Schools, Health Center ወዘተ ለዚህ ምስኪን ህዝብ በተሰራ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ከጁንታው ነፃ ስትወጣ ብዙ የሚጣሩ ስራዎች ለመንግስት ይኖራሉ Fair Distribution of Income እንዲኖር፡፡ ስንቶቹስ የነሱ ንክኪ ድርጅቶችና ግለሰቦች ዘርፈዋል፣ ከብረዋል ከዚች ምስኪን አገር፡፡

  ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.