የሚዲያ ሚዛናዊነት እንዲጠበቅ ጽንፈኝነቱ ሊገታ ይገባል | ዘ-ሐበሻ: Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

የሚዲያ ሚዛናዊነት እንዲጠበቅ ጽንፈኝነቱ ሊገታ ይገባል

1 min read

በሃገራችን ኢትዮጲያ ከጥንቱ ባህላዊ ሚዲያ እስከዘመኑ የኢንተርኔት ሚዲያ ድረስ የቅን ሃቀኛ ሚዛናዊ የሚዲያ ስዎችን ጥረት ላመሰግን እወዳለሁ:: ነፍስ ሳውቅ ባደግሁበት  በደርግ ተወርሶ ለስደት የተዳረገው በስደት ሳለ ስከታተለውና መጨረሻም በሃገር ቤት በስነጽሁፍ ዘርፉ ያገለገልኩበት የብስራተ ወንጌል ቆይቶ የምስራች ድምጽ የመገናኛ ዘዴዎችን ልዘክር እፈልጋለሁ:: በልጅነተ ዘመኔ በዚያ ጣቢያ ያስተማሩኝ ዶክተር አወይቱ ሲሜሶ ዶክተር ንጉሴ ተፈራ  ጋዘጠኞች ሰለሞን ተሰማ ዘውዱ ታደሰ ዳሪዎስ ሞዲ ሰለሞን ገብረሰላሴ ጸሃይ ታደሰ ምንጊዜም አልረሳቸውም::

በንጉሱ ዘመን የነበረውን አፈና በመቃወም  ብዙ ጊዜ በመከሰሰስ ይቀጣ የነበረው ጋሼ ጳውሎስ ኞኞና  ቆይቶም የደርግን የወረራ የጭፍጨፋ  ግፍ በድንቅ ብእሩ ያጋለጠው የኦሮማይና የሌሎች ድንቅ መጽሃፍት ደራሲ በአሉ ግርማ ዘላለም ሲታወሱ ይኖራሉ:: በሌላው ጫፍ በአጼው ዘመን የነበረውን ግፍ  የደርጉን ጭፍጨፋ የወያኔን ዘረኘነት የብልጽግና ተብዬውን ግድፈት የተፋለሙትን ሁሉ አከብራለሁ::

የሃገራችን የበኩር ስነጽሁፍ ድርጅት የምስራች ድምጽና የደራሲያን ማህበር መስራች በዘረኞች የተገፉት ደራሲ አማረ ማሞን በዚህ አጋጣሚ ለሰጡት ትልቅ ድጋፍ በባልደረቦቼ ስም ላመሰግን እወዳለሁ::

በሌላ መልኩ ግን የንጉሱን  የደርግን የወያኔንም ሆነ የብልጽግናን በጎ ነገር ማየት የተሳናቸውን  የሚዲያን መርህ የጣሱትን ግን አይን ይማር አንደበትን ይፈውስ ማለት ፈልጋለሁ:: ባለሁበት ሃገር ማህበረሰብ ዜናዎች በሚዛናዊነት ሲቀርቡ ሳይ የሃገራችን ሚዲያዎች ጽንፈኘነት በአንድ በኩል ያለውን መንግስት በጭፍን ማወደስ በሌላ በኩል ያሉ ተቃዋሚን ብቻ ማወደስ በጣም ያመኛል:: በዚህ በኩል በሚዛናዊነት ሲያቀርቡ የማያቸው የዘሃበሻ ሄኖክ የኣውስትራሊያው ሬድዮ ዘጋቢ ካሳሁን ሰቦቃን ሳላመሰግን ማለፍ አልችልም::

ውድ የሚድያ ማህበረሰብ ሚዲያ ወይም መገናኛ ብዙሃን የህዝቡን የማወቅ መብት የሚያስከብር ለሃገርና ለህዝብ ሰላም ጤንነት ብልጽግና የሚያጎናጽፍ ነውና ከጽንፈኝነት እንውጣ:: የሚወደስን ላማወደስ የፐለቲካ የሃይማኖትትና የዘር ብሄረሰብ  ወገናዊነት ኣይገድበን::  ታላቁ የኢትዮፒያ ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ስለታሪክ የሰጡትን መርህ ለዜናም እናድርገው ታሪክ በታሪክነቱ ይዘገብ ዜና በዜናነቱ ከሁሉም አቅጣጫ በሚዛናዊነት ይቅረብ::

ሰሞኑን በጣም ያሳዘነኝ ከለየላቸው ዘረኞች የባሰው በኢትዮጲያ በትልልቆቹ ብሄረሰቦች በኦሮሞና በአማራ ባህሎች ታሪኮችና መሪዎች ላይ የሚደርስ ያልተገባ የስም ማጥፋት ነው::  በአንዱ ብሄርሰብ ላይ የሚደረገው ስም ማጥፋትና የታሪክ ግድፈት የሁሉም ለመሆኑ ከእኔ ከድብልቁና ከመሰሎቼ የበለጠ የሚያውቅ የለምና ያንዱን ትልቅነት ብቻ የሌላውን ጥፋት ብቻ የሚዘግብ ብእር የፈውስ ዘንድ የሃገራችን ሚዱያ ያለፈ ግድፈት በደል ላይደገም ያለፈ በጎ ስራ ሊደገም ሊዘከር ይነሳሳ ዘንድ ምክሬን አስተላላፋለሁ::

ቻፕሊያን ኣኤዲ አደርፍስ ሃብቴ መካሻ ከኦማሃ ነብራስካ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.