ታሪክ ራሱን ደገመ ጥንት ኢንፍሎዌንዛ ዛሬ ኮሮና | ዘ-ሐበሻ: Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ታሪክ ራሱን ደገመ ጥንት ኢንፍሎዌንዛ ዛሬ ኮሮና

1 min read

ጥንቃቄ ፣መተባበር እና በመንፈስ መጠንከር ትላንትም ዛሬ ያሻግራል

ሰሞኑን የኮሮና ቫይረስን (ሳንባ ቆልፍ) አስታኮ የማይፈተሽ የታሪክ መዛግብት የለም። ስፓኒሽ ፍሉ ይባል የነበረው እና የዛሬ መቶ ዓመት 50 ሚሊዮን ሕዝብን ህይወት የቀጠፈው ተላላፊ በሽታን ጨምሮ ከዚያ በሁዋላም እየተፈጠሩ እንደ አቅማቸው እየገደሉ የሄዱትን ጨምሮ ከአነሳሳቸው ጀምሮ በወቅቱ እስከ ተደረጉ መከላከያዎች ከታሪክ ማህደር እየተፈተሸ ቀርቧል።
በዚያን ግዜም ስፓኒሽ ኢንፍሎዌንዛ በአገራችንም ብዙዎችን ገድሎዋል።በምዕራቡ ዓለም እንደ ዛሬስ ሰው ከቤቱ እንዳይወጣ፣ትምህርት ቤቶች፣መሰብሰቢያዎች ፣መዋኛ ስፍራዎች ሁሉ ተዘግተዋል። ዛሬ ለምን የዕምነት ተቋማት ተዘጉ ብሎ አምባጉዋሮ እንዲፈጠር ከማበረታታት ይልቅ ለጥንቃቄ ተብለው የተወሰዱት እርምጃዎች ላይ ማተኮር እና ተግባር ላይ ማዋል ይገባል።

ከሰለጠነ አገር ሄዶ ተለይተህ ቆይ ሲባል ጉቦ ሰጥቶ ማምለጥ ፣ሥራ ቀርቶ ተደብቆ ተሳብሰቦ መጠጣት እና መብላት፣ቤተ እምነት ሲዘጋ ከሚገባው በላይ ቤት ውስጥ ሰው አጨናንቆ አምልኮ ለመፈጸም መሞከር ከራስ አልፎ የሌሎችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ወንጀል ነው። ሕዝቡ ራሱን መጠበቅ አለበት ሲባል ይህን የሚፈጽሙትን ጭምር መከላከል ሲችል ነውና

አስቀድመው ተናግረዋል የተባሉ ጸሐፍት እና በትንቢቱ የሚታወቀው ኖድትራዳሞስ ሁሉ ይጠቀስ ነበር። በዚያም ዘመን ህዝብ ቤቱ እንዲከት መመሪያ ወጥቶ እንደነበር ማስረጃዎች ያሳያሉ። በአደባባይ አፍን ሸፍኖ መሄድም ተስተውሎዋል። ከዚያ ሁሉ ችግር በሁዋላ ሕይወት ቀጥሎ እዚህ ደርሶዋል።

የተነሳውን የኮሮና ቫይረስ ችግር ከምጽዓት ጋር እያጣቀሱ ከማሸበር እና ከመሸበር የሚቻለውን ጥንቃቄ እያደረጉ፣ከሞቱት ይልቅ የዳኑት ቁጥር የሚባልጥ መሆኑን እያሰቡ የዚህ ሁሉ ምስጢር ብርታት እና ጥንቃቄ መሆኑን ማስተዋል ይገባል።

የህክምና ሰዎችን ምክር መስማት፣በቻሉት ሁሉ የቫፕረሱን ስርጭት ለመግታት መሞከር ከራስ አልፎ ለሌሎችም ማሰብ ይገባል።
ከታሪክ ማህደር የሚጠቀሱ ማስረጃዎችን እዚሁ አግኝተን ለግንዛቤ አምጥተናቸዋል። ያንብቡት ሼር ያድርጉት
ጥንቃቄ አይለየን

ህብር ራዲኦ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.