ጭንቅ እና ዕርቅ -  ማላጂ | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ጭንቅ እና ዕርቅ –  ማላጂ

1 min read

የ“ትሕነግ ” አመራር ፣ አባላት እና ተስፈኞች በድሃዉ እና ጎስቋላዉ ህዝብ እና አገር ላይ ለዓመታት ያደረሱት ወደር አልባ ግፍ ሳይበቃቸዉ እኛን በክፉ የሚያስብ ግብዓተ መሬቱን ያፋጥናል ባሉበት አንደበታቸዉ ድርድር ሲሉ መስማት ዞትር እነረሱ የራሳቸዉን ዕኩይ ተልዕኮ እንደሰናይ ነገር አድርጎ መዉሰድ የእነርሱ የግል ባህሪ መሆኑን አመላካች ነዉ ፡፡

የዘመናት የጦር ጠማኝ ምኞት ፣ፍላጎት እና ዝግጅት በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ጉርስ እና ልብስ እየተቀነሰ ከሚገኝ ቀረጥ.፣ ግብር፣ ብድር እና ስጦታ ህዝብ እና አገር ለመጉዳት በሚዉል የጥፋት እና አዉዳሚ መሳሪያ እና ሠዉ ሃይል ማዘጋጀት እና ቀጥታ አገርን በሚጎዳ ጦርነት ጀማሪ መሆን ለህዝብ እና አገር ደህንነት እና ክብር ከማጣት  ከራስ እና ቡድን ፍላጎት የመነጨ የጥላቻ እና የማንአህሎኝ ትኩሳት እንደሆነ እማኝ አያስፈልገዉም ፡፡

ሆኖም የድርጅቱ መሪ የነበሩት ዶ/ር ደ.ጺዮን  በአንደበታቸዉ ህጋዊ አመራር ያለን እኛ ነን የማዕከላዊ መንግስት ህጋዊ መሰረት የለዉም ሲሉ በነበረበት አንደበት እንዴት ዛሬ ለድርድር እና ፖለቲካዊ ችግር መነጋገር ነዉ ሲሉን ምን ያህል ለህዝብ እና አገር ሳይሆን ለራሳቸዉ ራሳቸዉን እንደሚያሳስባቸዉ ያሳየናል ፡፡

እዚህ ጋ ሁላችንም ከሁለቱም አካል ሊረጋገጥ የሚገባዉ  በተለይም ከሁለት ዓመታት በፊት አስካሁን ጊዜ ድረስ አንደኛዉ ሌላዉን ፡-

፩ ኛ) ህጋዊ እና በህዝብ ይሁንታ የተመረጠ መንግስት አልበረም ሲል መባጀቱ፣

፪ኛ) ማንኛዉም የማዕከላዊ መንግስት ሲያወጣቸዉ እና ሲተገብራቸዉ የነበሩትን የአፈፃፀም መመሪያዎች በማጥላላት እና ዉድቅ ማድረግ ፣

፫ኛ) ከመስከረም ፳፭ ቀን ፪ ሽ፲፫ .ዓ.ም ጀምሮ ህጋዊ መንግስት እኔ ነኝ ሲል በነበረበት፣

፬ኛ) የህዝብ እና የማዕከላዊ መንግስት ጥቅም እና ስልጣን በሆኑት ነገሮች በቀጥታ እና በስዉር ጣልቃ በመግባት ተፅዕኖ (አፍራሽ) ነግግር እና ተግባር ሲያሳድር የነበር፣

፬ኛ ) ይህም በጥቂት አስረጅ. የጦር አመራር ማዕረግ የማሳደግ፣ የመመደብ፣የማዘዋወር….የአገሪቱ መሪ ሆኖ እያለ ከማዕከላዊ መንግስት የተላከን ወታደራዊ ባለስልጣን በመጣበት መመለስ(መከልከል)

፭ኛ) በሰሜን ዕዝ የሆነዉን እና የተከሰተዉን ማድረግ እና እንዲሁም ሌላዉን የክተት ጥሪ ማድረግ ፤

፮ኛ) ብቸኛየፌደራሊዝም እና ህገ መንግስት ሞግዚት አድርጎ የመመልከት ፣

፯ኛ) ማዕከላዊ መንግሰት አገርን እና ህዝብን ከሚገመት ቀዉስ ለመከላከል ላደርገዉ ብሄራዊ ጥሪ ምላሽ እኛን የነካ  ሞቱም ፤መቃብሩም እዚህ ነዉ በማለት የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ትስስር ክር እንደተቆረጠ እና የሁሉም ነገር ዕጣ ፈንታ በእጃቸዉ እንደሆነ ሲነግሩን የነበረዉ በቀናት ዉስጥ ያ ሁሉ የጦር አምጣ ዝግጅት እና ምኞት የት አድረሰዉት ነዉ “ድርድር ንግግር” ማለት ፡፡

ጦርነት በየትኛዉም ጊዜ እና ቦታ የማንም ምርጫ ሊሆን እንደማይችል ሲያዉቁ  በራስ አገር እና ህዝብ ላይ ጦር መስበቅን እና ማስፈራራትን ምርጫ እና ፍትሃዊ (መፍትሄ ስልጣን) ብለዉ ሲዘምሩ እንዳልነበር ድርድር ከጭንቅ  የተከሰተ የጭንቀት መዉጫ  ድንግርግር ወይስ ከአንጀት ያልሆነ ከአንገት በላይ ዕርቅ ፡፡

ለመሆኑ ድርድር በአገር እና ህዝብ ደም እና ህልዉና እንዴት እና አስከመቸ ይሆናል ፡፡

በርግጥ ኢትዮጵያ ዉስጥ  በህዝብ እና አገር ላይ በተለያየ ጊዜ በቀደሙት መንግስታትም ሆነ በቅርብ የሚደረጉ በደሎች በዓይነት እና መጠናቸዉ ቢለያዩም እንዲህ ዓይነቱ ብሄራዊ ቀልድ(ኮሜዲ) ግን የህዝብ ነን የሚሉ ነገርን ግን ከህዝብ ፊትም ሆነ መካከል መገኘት ለማይችሉ ፤ የማይፈልጉትም ወደዉ ሳይሆን ለህዝብ እና ለአገር ካለቸዉ ዕይታ እና ግምት ማነስ /መቀነስ የሚመጭ የብልጠት አስተዳር እሳቤ የዕሾክ ፍሬነት ነዉ ፡፡ ህዝብ እና መንግስት አጋም እና ቀጋ ሆኖ መኖር ለነዕርሱ የሥልጣን ጊዜ መሸመቻ  ዋና የፖለቲካ ዘመቻ አካል አድርጎ ማሳብ ድርጅታዊ ባህል እነና ልምድ ሊሆን ይችላል ሆኖም  በብልጠት አገር እና ህዝብ ለመምራት የሚቻልበት ዘመን ግን አይመስለንም እና በነበረ እና ባፈጀ የብልጠት የፖለቲካ አካሄድ እንደገና መብለጥ የሚቻል አይሆንም ፡፡ ሁሉን እና ያለፈዉን ለህዝብ እና ለታሪክ ሰጥቶ ዳግም ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በአንድነት እና በነጻነት ፀንተዉ ለመኖር ጠንቅ የሚሆን ሁሉ ከስር እና ምንጭ ማድረቅ ግን ዳግም የማይገኝ በአንድ ክፍለ ዘመን የሚከሰት አጋጣሚ ነዉ እና ወደ ኋላ ማየት ሊሆን ቀርቶ ሊታሰብ አይገባም  ፡፡

ከጭንቅ ቀድሞ መጨነቅ(ማሰብ)  እንጅ ለጭንቅ ማለፊያ ዕርቅ “ ሳል ይዞ ስርቆት ፤ ቂም ይዞ ፆሎት ” እንዲሉ አበዉ  ይህ ለፅድቅ ሳይሆን  በአብሮነት ለዉድቀት እና ፅልመት እንዳይሆን ፡፡

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.