ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ #የብልፅግና ፓርቲ የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ ያደረጉት ንግግር | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ #የብልፅግና ፓርቲ የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ ያደረጉት ንግግር

1 min read
8

 


ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ብልፅግና ፓርቲ ኢህአዴግ ከሚባል የበሰበሰ እንቁላል ውስጥ ሰብሮ የወጣ አዲስ ህይወት ነው፣ ኑ ተቀላቀሉን ብለው ለሌሎች ድርጅቶች ጥሪ አድርገዋል። የፓርቲው ፕሮግራም የተረቀቀ መሆኑንና ኢትዮጵያን ለአስር ዓመታት የሚያሻግር እሳቤ በውስጡ ያካተተ መሆኑን ተናግረው፣ የፕሮግራሙን ሰነድ ከፍ አድርገው አሳይተዋል። ከሰነዱ ሽፋን ማየት እንደሚቻለው የወደፊቱ የብልፅግና አርማ ከላይና ከታች አረንጓዴ ከመሀል ነጭ መሆኑን የሚጠቁም ይመስላል። በኢትዮጵያ እሳቤ አረንጓዴ ልምላሜና ብልፅግናን ነጭ ሰላምን ስለሚወክል የፓርቲውን እሴት የሚወክል አድርጎ መውሰድ ይቻል ይመስለኛል። አቢይ፣ ከስሜትና ከምኞት ውጡና በእውቀትና እውነት ደግፉን ማለታቸውን ወድጄዋለሁ፣ ተመልሼ ስሜታዊ እስክሆን ድረስ ማለት ነው። ለእኔ ስሜት መከበር ያለበት የህይወት አካል ነው። በህይወቴ ልምድ ከአእምሮዬ ይልቅ ልቦናዬ የነገረኝ ለእውነትና ሃቅ የቀረበ መሆኑን ደጋግሜ የፈተንኩት ጉዳይ ነው። ልቦና ደግሞ ከአእምሮ ይልቅ ለስሜት ቅርብ ይመስለኛል። ስሜት ደመነብስ አይደለም፣ በህይወትህ ካስጠነቀርከው ሃቅ ተነስቶ የሚመራህ ድባብ ነው። ደመነብስና ከሱ የሚመነጨው ተግባር ራስን ጠብቆ ለማዳን የሚደረግ አልሞትባይ ተጋዳይነት ስለሆነ ከእንስሳት የምንጋራው ነው። ልቦና ግን ምጡቅና ጭምቅ ነው። አእምሮህ በአንድ አቅጣጫ ሲመራህ፣ ልቦናህ ሌላ የሚነግርህ፣ አእምሮህ ብልጣብልጥና ጥቅምህን ያካተተ ሲሆን፣ ልቦናህ ግን ካንተ መጥቆ ተፈጥሮንና ሃቅን ያማተበ ሆኖ ይሰማኝል። ያሬዳዊ ሶፍስትሪ እንዳትሉት አደራ!
Yared Tibebu