‹‹ጁንታው የህወሓት ቡድን የፈጸመው ተግባር የውጭ ወራሪዎች እንኳን ያልፈጸሙት ነው›› - አርቲስት ደበበ እሸቱ | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

‹‹ጁንታው የህወሓት ቡድን የፈጸመው ተግባር የውጭ ወራሪዎች እንኳን ያልፈጸሙት ነው›› – አርቲስት ደበበ እሸቱ

1 min read
2
ዋለልኝ አየለ

አዲስ አበባ፡- ጁንታው የህወሓት ቡድን በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የክህደት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የሀገሪቱን ህዝቦች ለማንበርከክ የሞከሩ ወራሪዎች እንኳን ያልፈጸሙት ተግባር መሆኑን አርቲስት ደበበ እሸቱ አስታወቀ።

አርቲስት ደበበ እሸቱ ጁንታው የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ትቃት አስመልክቶ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቀው ፤ ከሃዲው ቡድን ለ21 ዓመታት ክልሉንና ህዝቡን ሲጠብቅ በነበረው የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት የከሃዲነት ተግባር ከመሆኑም ባሻገር ትውልድም ይቅር የማይለው ነው።

‹‹ተስፋ የቆረጠ ሰው ብዙ ነገር ያደርጋል። ተስፋ ባይቆርጥ ኖሮ፣ አብሮት ሲሰራና አብሮት ሲበላ የቆየ ወንድሙን አይገድልም ነበር። መከላከያ ሠራዊቱ ከኋላዬም ከፊቴም ያለው የራሴው ወገን ነው ብሎ ወገኑን ተማምኖ በተኛበት በሌሊት ክህደት መፈጸሙ ቡድኑ የመጨረሻ ዘመኑ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው ።

“አርቲስት ደበበ እንደሚለው፤ የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የፈፀመው ክህደትና ጭካኔ የውጭ አገር ጠላትና ወራሪ እንኳን ያላደረገው ነው። ጣሊያን አላደረገውም፣ ደርቡሾች አላደረጉትም፣ እንግሊዞች ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስን ለመያዝ በመጡበት ጊዜ እንዲህ አይነት አፀያፊ ድርጊት አልፈጸሙም። የራሳችን ወገን የተባለው ግን እንዲህ አይነት ዘግናኝ ድርጊት ፈጸመ። የሠራዊቱ አባላት ሲወጣ ‹‹ለማን ጥላችሁን ነው የምትሄዱ፣ እባካችሁ ቆዩልን›› ያለ አካል ይሄን ክህደት መፈጸሙ የግድያ ቀን እያመቻቸ ነበር ማለት ነው። ሠራዊቱ ይህ ክህደት እንደሚፈጸምበት ቢያውቅ ጥሪውን ሳይቀበል ይወጣ ነበር። የወገን ጥሪ ሆኖበት ግን ቆይልኝ ሲባል እዚያው ቆየ። ወገን በወገኑ ላይ እንዲህ ሲጨክን ቅስም ይሰብራል።ኢትዮጵያዊ መሆኑንም እንድንጠራጠር አድርጎናል ብሏል።

‹‹እንዲህ አይነት የአውሬነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ነበሩ ለካ ሲመሩን የቆዩት›› ያለው አርቲስት ደበበ፤ እነዚህ ሰዎች የፈጸሙት አጸያፊ ተግባርም መላውን ኢትዮጵያዊ ያሳዘነና ያስቆጣ መሆኑንም ጠቁሟል።

እንደ አርቲስት ደበበ አስተያየት፤ ጁንታው የህወሓት ቡድን ሥልጣን ላይ በቆየባቸው ዓመታት ለጥፋት የሚሆኑትን ገንዘብና ሌሎች ነገሮችን ቢያከማችም ሊያዛልቀው ግን አይችልም። አቅም ይሳነዋል። አሁን ላይ ማድረግ የሚችለው የመሰረተ ልማት ውጤቶችን ማውደም ብቻ ነው። ከአዲስ አበባ ጋር ግንኙነቱ ስለተቋረጠ የገንዘብ ምንጩም ይደርቃል። እስከ አሁን ግን ከዚህ በፊት በሰበሰበው ገንዘብ አፈ ቀላጢዎችን ቀጥሮ በውጭ መገናኛ ብዙኃን ብዙ እያስወራ ነው።

“የውጭ መገናኛ ብዙኃን የሚወሰደውን ህግ የማስከበር ሥራ የእርስ በርስ ጦርነት አስመስለው የሚያቀርቡት በጁንታው አፈ ቀላጤዎች የሚነገ ራቸውን መሆኑን የገለጸው አርቲስት ደበበ፤ ኤምባሲዎች እውነታቸውን መናገር እንዳለባቸው አሳስቧል። ቡድኑ በውጭ አገር ወንጀል በሚሰራባቸው ባንኮች ባስመጠው ገንዘብ ‹‹ሎቢስት›› ቀጥሯል። እነዚህ ተቀጣሪዎች ተደማጭነት ያላቸው ናቸው፤ ነጭ ለነጭ ደግሞ ይተማመናሉ። እነዚህ ተቀጣሪዎች ግን የጁንታው ገንዘብ ሲቋረጥ ይከስማሉ። አሁንም ሀሳባቸውን የቀየሩ አገራትና መሪዎች ታይተዋል። በተለይም ኤርትራ ላይ ሮኬት ከተኮሰ በኋላ የቡድኑ ጠብ ፈላጊነት ዓለም በሙሉ ተረድቶታል” ብሏል።

አሁን መንግሥት እያደረገ ያለው ህግ የማስከበር ሥራ የትግራይ ህዝብ ላይ የተነሳ ጦርነት ሳይሆን የትግራይን ህዝብ መደበቂያ አድርጎ የተቀመጠ ወንጀለኛን መፈለግ ነው ያለው አርቲስት ደበበ እሸቱ፣ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እስኪቀርቡ ድርስም የኢትዮጵያ ህዝብ ከመንግሥት ጎን ቆሞ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው አሳስቧል።

‹‹እንደ ትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያን ባንዲራ

የሚያከብር አላውቅም፤ እኔ ባየሁት፤ ልጅ ሲወለድ የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው ከቤታቸው የሚሰቀለው፣ ሰርግም፣ ክርስትናም፣ ለቅሶም ሲሆን የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው የሚውለበለበው›› ያለው አርቲስት ደበበ፤ የትግራይ ህዝብ በህወሓት ቡድን ለደረሰበት በደል የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኑ ሊቆም እንደሚገባም አሳስቧል።

አዲስ ዘመን ህዳር 12/2013

2 Comments

 1. With all due respect,
  Yes, it is self-evidently and vividly known that the very inner circle of TPLF is the very originator , narrator, activator and mastermind of the bloody ethnocentric political system which we have gone through and continued going through in a much more devastating manner both in an extensive and intensive manner .
  It is very ridiculous for us to keep talking and writing about this very and very clear and straightforward tragic political game without coming up with a real sense of creating a practical situation by which we should be truly and patriotically make it to come to its end. We are still making ourselves busy in just decrying this very evil-driven war of our own making and crying hard for not only those innocent compatriots who are directly devastated by this war of which its purpose is said to be just to eliminate very few members of the inner circle of TPLF , not to come up with a very determined way of eliminating the constitution and the federal system which is still controlled by people whose hands are not free from the very priceless blood of countless innocent citizens for about three decades . Is this not deeply painful and sad? It is absolutely nonsensical to let more and more of innocent people shed their priceless blood just to see those few TPLF’s inner circle either to surrender or being killed, and then to allow politicians of Prosperity whose hands are stained with the very blood of countless innocent citizens continue the same bloody political system they have been involved for about three decades.
  I do not understand why we are not courageous enough to come out publicly and say that injustice in some somewhere is injustice anywhere? Yes, TPLF is an evil-driven political entity that must be dealt accordingly! But we have to be courageous enough to unequivocally condemn and fight the very tragic situation that has been very rampant in regions particularly in Oromia and Benishangul if we are truly concerned about a deeply painful injustice in our country. SO, where were you sir when those countless citizens have been and are being killed and mutilated in those regions? Believe or not, it is because of this very cynical political behaviors of our own that the very tragic politically motivated crimes continued uncontained. And this very dirty double standard behavior and position of ours will never bring a real sense of stability and peace and socioeconomic environment at all! I hate to say but I have to say that it is the people like me and you who are driven by not the principle of getting real democratic change but by a much uncontrolled emotional and irrational thinking and action that significantly contributes to where we are now. You cannot help the people in their struggle to make their dream of fundamental democratic change a reality while you make yourself the worshiper of the prime minister whose political personality and behavior is not only so infantile but also highly hypocritical and narcissist.
  I know there may be many compatriots who consider this comment of mine as a taboo or simply hatred especially at this time of war. I beg to disagree that it is this kind of very clumsy and stupid way of our political thinking and belief that has made us victims and captives of delusional, hypocritical, dishonest, conspiratorial and of course cruel ruling elites for a long period of time and still not able to have a breakthrough for the better.
  So, if you are serious enough about this very devastating political game being played by the same people whose hands are stained with the very blood of countless innocent citizens and about the senseless war triggered by the very evil-minded of TPLF’s inner circle, speak out clearly and loudly that injustice by certain political entity and injustice somewhere is injustice everywhere. Help the people with regard to the very critical question of what is really the very aim or goal of the war? It is said to be to either kill or capture few cruel and stupid members of the inner circle of TPLF. Really? I hate to say but I have to say that you repeat this very nonsensical way of dealing with our politics that has been and keep being practiced by EPRDF, now Prosperity politicians. Let’s us have a real sense of independent and consequential idea or recommendation. Let’s try hard to get out our clumsy and opportunist political thinking and behavior if we really want to see a desirable out come!

 2. የኢትዮጵያ ህዝብ በአብዛኛው ሠራተኛ ገበሬ ነው። ግብርና ላይም ከባድ የአካል እንቅስቃሴዎችን አድርጎ በስተመጨረሻ ያገኘውን ቤተሰብ ይመራበታል የማንበብ እና የመፃፍ ሥራዎች የሉበትም። በኢትዮጵያ ሁሉም የቤተሰብ መሪ ለሚያስብል በሚያስደፍር ደረጃ ልጆቹን ሲመራ የቀለም ትምህርት ሊያስተምር ልጆቹን ሲሰድ እዛ ተማሪ ቤት ምን ሲማሩ እንደሚውሉ ወላጅ አያውቅም። ለሰላሳ አመታት የትግራይ ጁንታዎች አስተማሪ ሆነው ከበው ልጆቻችንን ምን ምን አይነት መርዝ እንደመረዙብን አናውቅም። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እድሜው ከአርባ አመት በታች ነው። ከሀያ እስከ አርባ እድሜ ያለው ምን አይነት አሰቃቂ ክህደት እና ጭካኔ ዛሬ ላይ ወያኔ ጁንታዎች ሰሩ ብትለው እምብዛም አይገርመውም ምክንያቱም በወያኔ አስተማሪዎች እራሱ ላይ ሲደርስበት ያደገበት የኖረበት ነገር ነው እንዲያውም የተገረምን ባዮቹ መገረም ነው ይልቁን ይህን ትውልድ የሚገርመው ወያኔ ጁንታ ዛሬ ከሰራው ክህደት ፣ አረመኔነት……ይልቅ ።

  በሌላ ሀገር እኮ የወላጅ እና የአስተማሪ ምክክር ስብስባ parent teacher conference በየወሩም ሆነ በየሳምንቱ ይካሄዳል። በእኛ ሀገር ልጆቻችንን ለጁንታ የቀለም ትምህርት አስተማሪዎች በጉዲፈቻ ሰጥተን አመት ከአመት ሲመርዙብን ሠላሳ አመታት ሆናቸው። እንደሌላው ሀገር ወላጅ ከልጆቹ ጋር ትምህርት ቤት ሄዶ ወላጅ ክፍላቸው ገብቶ ሲውል በእኛ ሀገር ሰምቼም አላውቅም። በሌሎች ሀገሮች ወላጅ ክፍል ውስጥ እየገባ ወላጅ የልጆቹን አስተማሪን ሲታዘብ ሲገመግም እና ሲያግዝ መዋል በጣም የተለመደ ነው። ይህ ባህል ዛሬ ነገ ሳይባል ዘንድሮ ሊጀመር ይገባዋል።

  እኛ ሀገር ልጆቻችንን ትምህርት ቤት ሰደን እኛ እዛ ምን እንደሚደርስባቸው ለማወቅ ዝርም አንልም በእዚህም የተነሳ ጄኔሬሽን አጥተናል። በሰሜን እዝ ካምፕ ወታደሮቻችንም የወያኔ ‘የቀን’ ጅቦች ባሉበት ሰደን ዝር ብለን ስለደህንነታቸው መረጃ ባለመስበሰባችን ነው እንዲህ የተዋረዱት ። ከጁንታ ካምፕ በመጡ የጁንታ አስተሳሰቦች እየተመሩ አቅመ አዳም እድሜ የደረሱ ልጆቻችንን ህግ ለማስከበር ሄደው ምን እንደሚደርስባቸው ለማወቅ ዝር ባለማለታችን የደረሰውን አይተናል እያየንም ነው። ስንት እንደሞተ እንኳን እውነት እንደማንሰማ ትግራይ ጁንታ ተሸነፈ በሁዋላም ቢሆን እንደማንሰማ እወቁት። ቀድሞውንም ጅቦች ቀን መውጣት እንዳውም ተፈጥሮዋቸው አይደለም። በሌሊት የሚያንቀላፋ ማጥቃት የጅብ ተፈጥሮ ነው።

  አሁን ላይ ገበሬው ተጭበርብሮ ልጆቹን እንዲማግድ ተደርግዋል። ልጆቹም በአስክዋላ እያፈነ ሲመርዛቸው እና ሲያሰቅያቸው የኖረውን ወያኔ ለመበቀል እድል ስላገኙ በእልህ ተነስተዋል አላንገራገሩም ። ሰንኮፍ ነቅለን ተከታዩ ትውልድ እንደእኔ ካልተሰቃየ መስዋዕት ብሆን አይቆጨኝም በሚል ተነስትዋል።

  ለዚህም ነው በየቤታቸው ያሉ ከአሁኑ ዋናው መታሰብ ያለበት ጉዳይ መሆን ያለበት እንዴት ነው ወላጅ ቀጣዩ ትውልድ ምን ተምሮ በማን ተምሮ እንደሚውል በማረጋገጥ ተፈጥሮአዊ ግዴታውን የሚወጣው። ” አንብቡ ፣ አጥኑ ፣ የቤት ሥራ ሥሩ” እያሉ ልጆችን ሲያሳቅቁ ማምሸት በልጆች እና በወላጆች መካከል ክፍተት ከፍቶ የወያኔ ጁንታ የረጨው መርዝ ያልታጠቀ ገበሬ ህዝቡን ቀርቶ ታጠቀ የተባለውን ወታደር እንዴት ጉድ እንደሰራው አይተናል። የመርዙ ማምከኛ antidote ምንም ሆነ ምንም በፍጥነት ካልተገኘ ለቀጣይ ብዙ ትውልዶች በአስኳላ ትምህርት አማካኝነት መተላለፉ አይቀሬ ነው። ለዚህም መርዙን የቀመሙትን እነ ገነት ዘውዴን እና እነ አብይን ጨምሮ ቢሆን መድሀኒቱን እንዲረጩ ማንቁርታቸውን መጭመቅ ያስፈልጋል።ይህ መጭመቅ ሲደረግም መርዝ በተረኛ መርዝ እንዳይተካ እጅግ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። መድሀኒት ቤት pharmacy መደብር ምልክት የእባብ ስዕል የሆነው እኮ እባብ ማንቁርቱ ተይዞ የተፋው መርዝ በአግባቡ ሲቀመምም ፍቱን መርዝ ማምከኛ antidote መድሀኒት መሆኑ ስለተደረሰበት ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.