“ጁንታ”ም ይረፍ ! - ማላጂ | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

“ጁንታ”ም ይረፍ ! – ማላጂ

1 min read
4

ለወትሮዉ እኛ ኢትዮጵያዉያን በስም እንኳን አንታማም ነበር አሁን አሁን ግን ይህን ድፍን ኢትዮጵያን እና ዓለምን እያነጋገረ ያለዉ እና የዚህ ምክነያት የሆኑትን ግለሰቦች እና ቡድኖች እየተባለንም ፤እያልንም ስመ አለም መጠሪያ እና  መለያቸዉ ”ጁንታ” ሆኗል፡፡

በየመድረኩ ፣ መገኛኛ ብዙኃን እና ከደቂቅ አስከ ሊቅ የአፍ ማሟሻ  “ጁንታ”  ህጻናት ሳይቀሩ በስፋት ስለሚሰሙት የሚበላ የሚጠጣዉም ሆነ የህጻናት ማስፈራሪያ “ጁንታ” ሊሆን ጫፍ ደርሷል፡፡

ለቀናት ከቆየ ምንም እንኳን ዕርግማን ይሁን ምርቃት እምብዛ ባይገለጥልንም በአገርኛ መዝገበ ቃላት ከዕንግድነት ወደ ባለቤትነት ለመዛወር በጣት የሚቆጠሩ ቀናት የሚቀሩት ይመስላል፡፡

የሚገርመዉ ለአፍታ አንኳን የመጠሪያዉ ቃል ትርጉም ፣ መጣኝነት፣ገላጭነት  እና ወቅታዊነትን ማየት አለመቻል ድፍን አበሻ ብዙ ሆኖ ብዙ እና ታላቅ ተጋድሎ እያካሄደ ለህዝብ እና ሰሚ የሚመጥን ስያሜ መስጠት እና ቃሉንም የባዕድ ቃል ስለሆነ ለሳምንት ከተገለገልንበት መመለስ ሲገባን እንደገደል ማሚቴ ማስተጋባት ቋንቋ  እና ሰሚ የማስጨነቅ የባህል እና ቋንቋ ድንቅ ባለቤቶች ሆነን እያለ በተቃራኒዉ የስያሜ ዕጦት የተቸገርን የቋንቋ ድርቅ የመታን ይመስላል ፡፡

“ጁንታ ”-Junta- በቁሙ ሲታይ ፡-መንግስት፣አስተዳደር፣አመራር፣ወታደራዊ ወይም አምባገነን አስተዳደር ማለት ስለሚሆን እና የክልሉ አስተዳርም ህጋዊነት መስጠት እንዲሁም በቦታዉ የተተካዉን የክልሉን የጊዜያዊ አስተዳደር ዕዉቅና መንፈግ ስለሚመስል ጁንታዉ በዘላቂ እና ታዋቂ የአገርኛ ስያሜ ይተካ ፡፡

ብዙዎቻችን ሳይገባን ሌሎች እንዲገባቸዉ ስናስተጋባ እና ህዝብ (ሰሚ) ጆሮ ላይ እንዲደርስ ማድረግ ትዝብትም ፤ጥፋትም ስለሚሆን አቻ እና ገላጭ አገር በቀል ስያሜ ምጋበር እና ተግባር አካታች በማድረግ ስንፈልግ እንደ ክት ልብስ የምናለብሰዉ (ምናከናንበዉ) ሳንፈልግ የምንከተዉ(የምናስቀምጠዉ) ሳይሆን በታሪክ ድርሳን ተከትቦ ከጥዋት አስከ ፍጻሜ ዕለት የነበረዉ እና ያለዉ ምግባር ከተግባር ተሰናድቶ እና ተሰንዶ ለትዉልድ እና ለዓለም ይድረስ ፡፡ የትዉስት ስሙም “ጁንታ ”በነባር ሆነ በአዲስ እና ቋሚ ስም ይተካ ፤ይረፍ የሰዉ ወርቅ ላያደምቅ የምን መጨናነቅ  ፡፡

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!

4 Comments

 1. ጁንታ፣ ጁንቶ፣ ጁንትዬ
  ዶ/ር ዐቢይ ያሳደገችውን ወያኔን በስሟ እና በተግባሯ “ሕወሃት አሸባሪ” ለማለት ለምን ይቀፍፈዋል?
  የሥነ ልቡና ባርነት ?
  ሕወሃት ለሻዕቢያ፣ ኦህዴድ ደግሞ ለሕወሃት ጥልቅ የሆነ የአሽከርነት ሥነ ልቡና ያሳያሉ። የቅኝ ግዛት ሀገር ዜጎች የቅኝ ግዛቱ ዘመን ካለፈ በኋላም አንዳንድ ጊዜ የበላይ ሆነውም ለቀድሞው ቅኝ ገዥያቸው ጌታዬ ጌታዬ የሚል ዝንባሌ አይለያቸውም። ለምሳሌ አንድ ሱዳናዊ የለንደንን ስም ሲጠራ ስለ ሆነች ከተማ ሳይሆን ስለ መንግሥተ ሰማያት የሚያወራ ነው የሚመስለው። የድሮ ኤርትራውያንም ስለ ሮም እንደዚሁ። የእንግሊዝ ዘሮች (አሜሪካን ጨምሮ) ስለ ፈረንሳይ ተመሳሳይ የኅሊና ስግደት ያቀርባሉ።
  በነገራችን ላይ ሕወሃት እስከ 1990 የፈረንጆቹ ድረስ በአሸባሪነት “የክብር መዝገብ” ስሟ በደማቁ የሰፈረ ነበረች።
  ዛሬ ግን ይሄን ሁሉ ኢትዮጵያዊ አርደው፣ ሀገርን አዋርደው አፉን ሞልቶ በአሸባሪነት ከመፈረጅ፣ የቁልምጫ ስም አውጥቶ የሕወሃትን ድርጅታዊ ወንጀል መሸፋፈን መርጧል። የሕወሃቱ ጉዲፈቻ ዐቢይ አህመድ። ጁንታ፣ ጁንቶ፣ ጁንትዬ ይላታል። ሀገሬው በማያውቀው ስም። የጭማቂ ዐይነት ይሁን የመኪና መለዋወጫ ለሀገሬው የማይገባ ቋንቋ። መሪው ተናገረው ሕዝቡ ተቀባበለው። የቀድሞ አለቆቹን የማያስቀይም ስም ከየት ፈልጎ እንዳመጣ ይገርማል።
  ሌላው ዓለም በሙሉ የሕወሃት ደጋፊ እየሆነ ነው ምናምን እያሉ የሚያላዝኑ ካድሬዎች ደግሞ አየሩን አጨናንቀውታል። ሌላው ዓለም አንተን እያረደህ እያዋረደህ የምታንቆለጳጵሰውን የምታሞካሸውን ምን ብሎ ይርገምልህ? ወይስ ማይካድራን ሕወሃት አይደለችም የፈጸመችው? ኦህዴድ በሷ ከሚያላክከው ከሁለት ዓመቱም ሽብር ነጻ ነች ማለት ነው? የዐቢይን ሥልጣን መገዳደሯ ብቻ ከሆነ ወንጀሏ በስሱና በቁልምጫ ብትያዝ አያስደንቅም። የታረደና የተዋረደው የሀገር ሠራዊት፣ ለጠላት የተጋለጠው የሀገር ደህንነት፣ በስለት ታርደው በየትቦው የተጣሉት ንጹሐን ወገኖች፣ ይህ ሁሉ ወንጀል አሸባሪ የማይስብለው በሕወሃትና በኦህዴድ መሥፈርት ብቻ ነው። ምክንያቱም በነሱ መስፈርት አሸባሪ እስክንድር ነጋና አስቴር ናቸው። እኒህኞቹ የነሱን በሀገር ክህደት ሥራ ላይ የተጠመደ ልብ ስለሚያሸብሩባቸው።
  ለነገ የማትረፍ ቁማር?
  የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠላት ለተለያየ የግል የሥልጣን ስሌት ሲባል ለነገ የማሳደር ቁማር ከንቱ መሆኑን ከወያኔ መማር ያስፈልጋል። ወያኔ ሻዕቢያን በኢትዮጵያ ሠራዊት ከመደምሰስ (በባድሜ ጦርነት ጊዜ) በማትረፏ እንዳሰላችውና እንደቆመረችው ላሰበችው የክፉ ቀን መሸሸጊያ አልሆናትም። ሀገርን ለጥፋት ያበቃ የክህደትን ድርጅት በፖለቲካ ቁማር ለነገ ማስቀመጥ ነገ ሀገርና ኦህዴድንም ለጥፋት የሚዳርግ የሞኝ ብልጠት ነው የሚሆነው።
  የመነጠል ሙከራ?
  ሕወሃት ላይ ጥቃት በሚሰነዘርበት ወቅት ታችኛውን መዋቀር ለመነጠል ሲባል ቢደረግና አመራሩን የታችኛው እርከን እንዳይተባበረው ለማድረግ ቢሆን ትርጉም ይሰጣል። ሕወሃት ግን በአንድ እዝ ያለልዩነት ወይም ያለ አንጃ ሀገር የወጋ ድርጅት እንደመሆኑ የላይኛውን አመራር አጽድቶ የታችኛውን ነጥሎ መተው ምንም ፋይዳ የለውም።
  ሕወሃትን ከነመዋቅሩ እና አስተሳሰቡ በቦታው አስቀምጦ፣ ትግሉ የትግራይን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት ነው የሚለው በሕዝቡ ማላገጥ ነው የሚሆነው። ሕዝቡን መቅጣት ነው የሚሆነው። ይህም የትግራይ ሕዝብ ሕወሃት እንዳሳመነችው የሕወሃት የግል ንብረት የሆነ ሕዝብና ማንም ለዘላለም ሊታደገው/ሊያስጥለው የሚችል እንደሌለ የሚያረዳው ነው። ይህ እርምጃ የሚያሳየው ጠቡ በዶ/ር ዐቢይና በነደብረ ጽዮን ቡድን እንጂ ሀገርን በክህደት ለጥፋት ባመቻቸ ድርጅትና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል እንዳልሆነ ነው።
  ይህ ድርጅት ደግሞ እንደ አንድ ልብ የሚመክሩ እንደ አንድ አካል የሚሠሩ መቶ ሺህ አባላትን ይዞ የተንቀሳቀሰና ከሥልጣን ተወግዶ እንኳን በጉልህ የተነጠለ አንጃ የሌለው አንድ ክፍለ ጦር ለመደምሰስ ከፍተኛ ምሥጢራዊነትን ጠብቆ የተሳካ ወታደራዊና የደህንነት ዘመቻ ማካሄድ የቻለ ነው። አባላቱም ከአዲስ አበባ በቀጭን ትእዛዝ ሲጠራቸው የሚመጡ፣ ሲያስከዳቸው የሚከዱ በአባላቱ ላይ ከዳር እስከዳር የተሟላ ቁጥጥር ያለው ድርጅት ነው። ይህንን ድርጅት ያረጀ ቆዳውን አውልቆ ሙሉ አካሉን መተው እንደ እባብ በአዲስ ቆዳ ታድሶ እንዲከሠት ማድረግ እንጂ እባብነቱን ወይም መርዛማነቱን ማስቀረት አይደለምና በትክክለኛ ስሙና ሥራው “አሸባሪው ሕወሃት” ተብሎ በአሸባሪነት ተከሶ፣ እንደ ናዚ ፓርቲ ሊወገዝ፣ ሊታገድ፣ ሊሰረዝ ይገባል።
  ሕወሃት የላከቻቸው አሸባሪዎች ተያዙ ይሉናል። ላኪያቸው ሕወሃት ግን አሸባሪ አይደለችም። በምርጫ ቦርድ እውቅና ያላት ጁንትዬ ናት።
  በይ ጁንትዬ ሥራሽ ያውጣሽ!

 2. ወንድም ጥሩ ብልሀል ። በቋንቋችን ሁሉን ለመግለፅ ሲቻል ሆን ተብሎ አማርኛን ለማበላሸት የማይፈነቀል ድንጋይ የለም። ባሁኑ “ጁንታ”ቃል ደሞ የተፈለገው ፣ባንድ ጠጠር ሁለት ወፍ ነው።ባንድ ወገን የመንግስት ፍላጎትን ሽኩቻ ና ከጦርነቱ በዃላ ሕወሐትን መልሶ አቋቁሞ አማራውን መልሶ ለማጥቃት ነው። ይሄም የሌባ ዓይነ ደረቅ አይነት መሆኑ ነው።

 3. የሰውልክ፣
  ጭፍን ድጋፍ ማንንም ዐይጠቅምም ።ይህን እያላችሁ ነው ሰውየውን ገደል የከተታችሁት።ታሪክ የማያስተምርህ ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.