የወልቃይት ጠገዴ እድር በካርቱም!! | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

የወልቃይት ጠገዴ እድር በካርቱም!!

1 min read
ለ 30 አመታት በወያኔ ምክንያት አገራቸው እንዳይገቡ የተከለከሉ የወልቃይት ጠገዴ ሰዎች እድር በሱዳን ከተማ ካርቱም የሚኖሩ።
የሚገርማችሁ አሁን ፀሃይ የጠለቀባቸው የያኔው ዘመነኞች ወያኔዎች በስደት ከሚኖሩበት አገር ሱዳን በመግባት ስንቱን ወልቃይቴ አሳሰሩት ስንቱን አስገደሉት መሠላችሁ ፤
ይህ አሁን ታሪክ ይሆናል፦
ይህ ” የወልቃይት ጠገዴ እድር በካርቱም” የሚለው ሎጎ ተቀይሮ ፦
“በስደት የነበሩ የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች መንደር” በሚል ይቀየራል።
ትልቅ መንደር ከሁመራ ከተማ ጎን ተመስርቶ በወያኔ ምክንያት በገዛ አገራቸው እንዳይኖሩ የተከለከሉ የወልቃይት ጠገዴ ስደተኞች ይሰፍሩበታል።
እንኳን እኛ አገራችን የሆነው ፦
እነሱም አምጥተው አስፍረውበት ነበር።
የአማራ ክልል መንግስት እና የፌደራል መንግሰት ባስቸኳይ ኮሚቴ አቋቁመው በጁንታው ህወሃት ምክንያት ለ 30 አመት ያክል አገራቸው እንዳይገቡ ተከልክለው በስደት የሚኖሩትን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ተመልሰው ባገራቸው የሚሰፍሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለባቸው። የመኖርያ የከተማ ቦታ የእርሻ መሬት ተሰጥቷቸው በአገራቸው የመኖር መብታቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል።
ርስት በሺህ ዓመቱ
ለባለቤቱ !
(ጎሹ አለበል)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.