ዛሬስ - ትንሽዬዪቱ አብረህት ስታለቅስ ሕወሃታውያኑ ልባቸው ራርቶ ይሆን? -  በየነ ከበደ | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ዛሬስ – ትንሽዬዪቱ አብረህት ስታለቅስ ሕወሃታውያኑ ልባቸው ራርቶ ይሆን? –  በየነ ከበደ

1 min read

ጦርነትን ማንም አይፈልግም። ቢሆንም ግን የሃገርን ድንበር ለማስከበር ጦርነት ይደረጋል። አምባገነን ሥልጣኑን ፈቅዶ ስለማያስረክብ አመጽ ሊከሰት ይችላል። አመጹን ማካሄድ ትክክለኛ ሊሆን ይችላል። ሕወሃት ደርግን አስወግጄ ዴሞክራሲን አሰፍናለሁ ብላ ጨቅላ እየማገደች ወደ ፊት የገፋችው ከፊት ለፊት ተቆልሎ የሚታየውን ወርቅና ብር ለመዝረፍ እንጂ ኢትዮጵያን ለመጥቀም እንዳልሆነ መጨረሻው ተናገረ (the end justify the means)። ሕወሃቶች የአማራን ወጣት ገድለው ለአሞራ ጣሉ። ሕወሃቶች አሲምባ ውስጥ የመሸገውን ኢሕአሠን እንደተኛ ጨፈጨፉት። ይህ ሁሉ ለዘረፋ ነው።

የዛሬ አስር ዓመት ገደማ አንድነት ፓርቲን ተቀላቅለው የነበሩት አቶ ስዬን በሌላ ማህበራዊ ሜድያ አየኋቸው። ጦብያ ዜና (Topia News) ከስድስት ወር በፊት አንድ ቃለ መጠይቅ ይዛ ብቅ አለች። አንዲት ጋዜጠኛ ነች – አቶ ስዬን ጥያቄ አቀረበችላቸው። ጥያቄው በብልጽግና ፓርቲና በሕወሃት መሃከል ባለው አለመግባባት ላይ ያተኮረ ይመስላል። አቶ ስዬ ሰማያዊ ሙሉ ልብስ በሰማያዊ ከረባት ለብሰው ዘና ብለው ነበር ጥያቄውን የሚመልሱት። እዚያ ሠፈር የሚደረግ ጦርነት” አሉ – ኮራ ብለው – ትግራይ ማለታቸው ነው – “ዝም ብሎ የሠፈር ጦርነት አይደለም – real war  ነው። ጋዜጠኛዋ ታዳምጣለች እሳቸው ይናገራሉ። ትግራይ በፌደራል ሠራዊት እንዳትጠበቅ የሚያደርጋት ከሆነ መዘዙ አደገኛ ነው – ይህ ካልሆነ ሁሉም ራሱን የመከላከል መብት አለው – ፌደራል መንግሥቱም መከላከያ ሠራዊትም ይሄን ማወቅ አለበት” ይላሉ ኮስተር ብለው። አቶ ስዬ ሳቅ አሉ ደግሞ፣ ለስለስ ያለች ነበረች አሳሳቃቸው። እኔ ይህን የምናገረው ለማስፈራራት አይደለም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ ነው፣ እዚያ አካባቢ የሚጀመር ጦርነት ተራ የአካባቢ የክልል ግጭት አይደለም – full-fledged war – ነው የሚሆነው – ድንበሩ አይታወቅም – አሁን ያለውን የ social media ጦርነት ጥይት ጨምሪበትና እይው” አሉ ጠያቂዋ ላይ ዓይናቸውን ተክለው። ጦርነት ከተጀመረ አገራችን ሁሉ የአካባቢ ባለጌ የሚጨማለቅባት ኮማሪት ቤት ነው የምትሆነው” – “ይህ ፉከራ አይደለም፣ ስለ ጦርነት ካለኝ እውቀት ነው የምናገረው” – ቀጠሉ – “አንድ ሶርያዊ ጓደኛ አለኝ፣ ቁጭ ብዬ አነጋግሬዋለሁ፣ እነሱ አገር ከሰላሳ በላይ አገሮች እጃቸውን አስገብተዋል፣ የየራሳቸውን ግን ጣጣ ፈጥረዋል፣ መቋጫ ወደ ሌለው ውድመት ነው የሄዱት” አሉ። ወያኔን ማንም ሰው ንክች እንዳያደርግ ማስፈራረት ይመስላል አነጋገራቸው።

አቶ ስዬ ጦርነትን ሲጠሩት የሚመጣ ሂድ ሲሉት የሚሄድ ታዛዣቸው አድርገው ነው መሰለኝ የሚቆጥሩት ሲናገሩ ቆፍጠን ብለው ነው። አቶ ስዬ ቀማኞቹ ለህግ መቅረብ እንዳለባቸው አልጠቆሙም። የሃገሪቱን ምጣኔ ኃብትን ብቻቸውን የተቆጣጠሩት ጓደኞቻቸው ከፍትህ በታች መሆናቸውን እንዲገነዘቡም ጥረት አላደረጉም። ፍትህ እኮ እውነት ነች፣ ማንም አያሸንፋትም። በኅዋ ላይ የሚራመዱ ኃያላኖችም ሆኑ ተራራ አንቀጥቃጮች” እፍትህ ሥር ኢምንት ናቸው። ወያኔ ጠባቂዋ መከላከያ እዝ ላይ ፍጅት ፈጽማ ጦርነት ጀመረች። የአማራ ልዩ ኃይል ሲያሳድዳት ማይካድራ ላይ ንጹሃንን ጨፈጨፈች። ጦርነቱ ተጋጋለ – ሕወሃትም ዛተች፣ ባህር ዳር፣ ጎንደርና ኤርትራ ላይ ሮኬት ወረወረች፣ እዚህም እዚያም ምርኮኛ ስደተኛ ተፈናቃይ በዛ። ጦርነቱ በረታ ሕወሃት እንደ ድሮዋ ድልድዮችን አፈርሳ ተደበቀች – የሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሎች ልዩ ኃይላት ወደፊት እየተሳቡ እመጨረሻ ምሽጓ ተቃረቡ። አቶ ስዬ – ትግራይ ላይ የሚደረግ ጦርነት እንደሌላ ቦታ ጦርነት አይደለም – ሲሉ የግፈኞችን የመጨረሻ ፍጻሜ ከታሪክ አልተረዱ ይሆንየቀዳማዊ ኃይለሥላሴም መንግስት ወድቋል። ደርግም ወድቋል። ሁሉም ፍጻሜ አለው። ሃገር እንደ ሃገር ሕዝብ እንደ ሕዝብ ይቀጥላሉ። በደርግ ጊዜ የነበረው የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕዝባዊ አክብሮት ስለለበሰ እንጂ አዲስ አበባ ዙርያዋን በታንክና ልዩ ልዩ ከባድ መሳርያዎች አጥሮ ውጊያውን ቢቀጥል ኖሮ በሃገር ሃብትና በዜጎች ላይ እጅግ ትልቅ ጥፋት ይደርስ ነበር። የምሥራቁና የደቡብ ሠራዊት ለህዝብ ሕይወት ደንታ ቢስ ሆነው ወያኔን ቢያጠቁ ኖር ሕወሃት በኅልውና መቀጠሏ አጠራጣሪ ነበር። የሠለጠነ ጦር እንዲህ ነው፣ የመንግሥትን ፍጻሜ ይረዳል። ሕዝባዊው ጦር ወያኔ ሠተት ብላ አራት ኪሎ እንድትገባ የማርያም መንገድ ተወላት። ልብ በሉ ሕወሃት ሕዝባዊ ስላልሆነች መቀሌ ዙርያን ከቦ ለያዘው መከላከያ ኃይል እጅ ልትሰጥ አልፈለገችም። ሕወሃት መርህ አልባ ሽፍታ ነች። ቀድሞውንስ ቢሆን ተራመደችበት እንጂ ለትግራይ ሕዝብ ምን ርህራሄ ኖሯት። አቶ ስዬ እዚያ የሚደረግ ውጊያ ልዩ ነው ያሉት ሕወሃት መሬቱን እየለቀቀች ስትፈረጥጥ ሠላማዊውን ሰው ትጨፈጭፋለች ማለታቸው ይሆንወይንስ ደደቢት የተወለደችዋ ወያኔ የመጨረሻዋ ምሽጓን መቀሌ አድርጋ ቀብሯም እዛው ይሆናል ማለታቸው ነውየፍጻሜው ጦርነት ሁሉን ያሳየናል።

ሕወሃት ብዙ ተውኔት ጽፋለች፣ ዛሬ ላይ ግን ተውኔቶቿ አልሰሩም። ሕወሃት መነኩሴ መስላ ትሰልላለች፣ ሕወሃት ዘበኛ፣ ሠራተኛ መስላ ትመርጃለች። ሕወሃት ህገ መንግሥት እያለች ትሠርቃለች፣ ብሄር ብሄረሰብ እያለች ትዘርፋለች፣ አንቀጽ 39 ማስፈራርያዋ ነው። ወያኔ ሽንገላ ላይ ብርቱ ነች። የሚያሳዝነው ደጋጉን ኃይማኖተኛውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠራጣሪ እንዲሆን ማድረጓ ነው። ሕወሃት እስከ ወድያኛው መዝረፍ ነበር መሻቷ ሕዝብ ተነሳባት እንጂ። ሕወሃት ያጠረችውን ቦታ ሳትሰበስብ ሸሸች፣ ያልተመዘገቡ ሕንጻዎቿን ጥላ ሮጠች። ደጋፊዎቿ መሳርያና ቦምድ በየመንገዱ ወረወሩ። ባለቤት የሌለው የታጠረ ቦታ፣ ባለቤት የሌለው ሕንጻ – ሲባል አያስገርምምሕወሃት ያልተገበረችው ሌላ ምን እኩይ አለበመጨረሻ ግን እግዚአብሄር ለማይረባ ዓዕምሮ አሳልፎ ሠጣት። ሕወሃት የምርጦቹን ልጆስ አሜሪካ አስቀምጣ ለትንሺቱ አብረህት 150 ጥይት አስታቅፋ ሂጂ ተዋጊ” አለቻት። አብረህትዬ ንቁ ነች። ወገኖቼ ላይ አልተኩስም” ብላ እጇን ሠጠች። አብረህት፣ የሕወሃትን ደባ፣ ክፋት፣ ሁሉን ነገር እያለቀሰች ነበር የምትናገረው። ሕወሃት ትናንሾቹን ስትሰብክ ትግራይን ሁሉም ብሄር ብሄረሰብ አይወዳቸውም” እያለች ነው። አስተሳሰብን ጋርደው፣ ነጩን ጥቁር በሉ” ብለው አስፈራርተው ለነገዱበት የትግራይ ሕዝብ መቼ ነው ሕወሃቶች ይቅርታ የሚጠይቁትዛሬስ – ትንሽዬዪቱ አብረህት ስታለቅስ ሕወሃታውያኑ ልባቸው ራርቶ ይሆን?

እግዚአብሄር – ኢትዮጵያን መከራሽ ይብቃሽ ይበላት፣ አሜን

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.