እንደ ታደሰ ወረደ አይነቶቹ በኢንቨስትመንት ስም የተንደላቀቀ ኑሮ | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

እንደ ታደሰ ወረደ አይነቶቹ በኢንቨስትመንት ስም የተንደላቀቀ ኑሮ

1 min read
2
“እንደ ታደሰ ወረደ አይነቶቹ በኢንቨስትመንት ስም ያለምንም ማስያዣ 40 ሚሊዬን ብር በመውሰድ አሜሪካ የተንደላቀቀ ቪላ ሰርተው ልጆችና ሚስቶታቸውን እያኖሩ እዚህ የድሃ ልጆችን እየገደሉ ነው”
– አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ረዳ
**************************
እንደ ታደረ ወረደ አይነቶቹ የህወሓት ጁንታ ቡድን አባላት ያለምንም መያዣ ከባንክ እስከ 40 ሚሊዬን እየተበደሩ እና የአገርን ሃብት እየዘረፉ በሰበሰቡት ሃብት በአሜሪካ እና አውሮፓ እንዲሁም ዱባይ የተንደላቀቀ ቤት ሰርተው እያኖሩ እዚህ የድሃውል ልጅ እየገደሉ ናቸው” ሲሉ የቀድሞው የህወሓት ታጋይ እና የትግራይ ክልል የሽግግር ምክር ቤት ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት እና የድርጅት ንቅናቄ ዘርፍ ውስጥ የሚሰሩት አቶ ሊላይ ኃይለማርያም ተናገሩ፡፡
አቶ ሊላይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት፤ እንደ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ ደብረጽዮን፣ አባይ ጸሃዬ፣ ታደረሰ ወረደ እና ሌሎቹም የህወሓት ጁንታው አመራሮች የአንዳቸውም ልጅ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም፡፡ ሚስቶቻቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሉም፡፡
አቶ ሊላይ እንደሚናገሩት፤ አሁን በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት የእነሱ ልጆች፣ የእነሱ ዘመዶች እና የእነሱ ሚስቶች ናቸው፡፡ የዚህ ጁንታ ቡድን ቤተሰቦችን በተመለከተ አንድም ሰው ትግራይ ውስጥ ቀርቶ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቶ አፍሪካ ውስጥ የሉም፡፡ ከዱባይ፣ ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ ውጪ አንድም ቤተሰባቸውን ማግኘት አይቻልም፡፡ እናም የእነዚህን ጁንታ ቡድኖች እድሜ ለማራዘም እያደናገሩት አሁን ግንባር ላይ እያዋደቁት ያለው የድሃውን ሚስኪን ልጆች ነው፡፡
ለምሳሌ፣ ደብረጽዮን፤ ጦሩን እንደዘረፈ በተናገረበት አንደበት “ትግራይን እሳት እናደርጋታለን” ሲል ተደምጧል፡፡ በዚህ መልኩ ትግራይን እሳት እናደርጋለን የሚለው ደብረጽዮን ሁለት ልጆቹ አሜሪካ ናቸው፤ የመጀመሪያ ሚስቱም አሜሪካ ነው ያለችው፡፡ ሁለተኛዋም ሰሞኑን ልጁን ይዛ ለመውጣት እየሞከረች ነዉ:፡ ቤተሰቡብን የሚያሸሸው የተሸነፈው የጁንታው አለቃ ሰሞኑን “ትግራይን እሳት እናደርጋታለን” ሲል ከርሟል፡፡ “እናቃጥላታለን” ነው ያለው፡፡ ትግራይ መቃብራቸው ትሆናለች ነው ያለው፡፡
ሆኖም በሚነደው እሳት የሚቀጠሉትም ሆነ ነደው የሚሞቱና የሚቀበሩት ወገኖች አሜሪካና አውሮፓ ያሉ የእነርሱ ልጆችና ቤተሰቦች ሳይሆኑ ድሃው የትግራይ ህዝብና ልጆች ናቸው፡፡
እናም ይህ ሰው ትግራይን ምድረ በዳ ለማድረግና ትግራይን ለማጥፋት በትግራይ ህዝብ ላይ የክተት ጦርነት አውጇል፡፡
ታደሰ ወረደ የሚባለውም፣ 40 ሚሊዬን ብር ያለምንም ማስያዣ (ኮላተራል) ጋምቤላ እርሻ አርሳለሁ ብሎ ወስዶ ለልጆቹ የተንደላቀቀ ቪላ ቤት ነው አሜሪካ ገዝቶ ልጆችና ሚስቱን አሜሪካ የሚያኖረው፡፡ እሱ ግን እዚህ የድሃ ልጆች እየገደለ ነው ያለው፡፡ እሱ ራሱ ያደራጃቸውንና ያሰማራቸው ተላላኪዎች አማካኝነት ነው ነዉ በቦምብ፣ በሳንጃ፣ በጥይት ለሀገር ሉዓላዊነት የቆሙ የሀዝብ ልጆችን በክህደት የረሸናቸው፡፡
በመሆኑም ይህ ከሃዲ ቡድን በትግራይ ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ላይ ትልቅ ክህደት ተፈጽሟል፡፡ ይሄን ሲያደርጉም አንድም ልጅ እና ቤሰቦቻቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ አድርገው አይደለም፤ ውጪ አድርገው የድሃውን ልጅ ግንባር ላይ በማሰለፍ የጥይት እራት በማድረግ ነው፡፡ ሙሉ መረጃውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ያገኛሉ::
በወንድወሰን ሽመልስ
(ኢ.ፕ.ድ)

2 Comments

 1. ዳያስፖራ ቢያብር አድኖ የእነርሱን ማንነት የት የት እንዳሉ መዝግቦ መያዝ አለበት። ኢንተርፖል ያግዛል ካስፈለገ ። ሌባ ሌባውን በየኤምባሲው ስለሰገሰጋቸው አብይ ከወያኔ የግፍ ቀንበር ዳያስፖራው ነፃ አልወጣም ገና ። ዳያስፖራው ሊያብርባቸውም አልተቻለውም። ልክ ትግራይ በአሁኑ ደቂቃ ከወያኔ ነፃ ለመውጣት እንደምትፋለመው ዳያስፖራውም መፋለም አለበት ከቀንደኛ ከኢህአዴግ ሪፎርም ያልነካቸው ወንጀለኞች አምባሳደሮች ፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በዳያስፖራ ሹማምንት እና ከመሳሰሉት …… ነፃ ለመውጣት። ዳያስፖራው ነፃ የሚወጣበት ቀን ናፍቆታል ።

  በትግል ያኔ ብቻ ዳያስፖራው ነፃ ይወጣል። ትግልን የሚቀለብሱ በየኤምባሲው እየገቡ ወሬ የሚያቀብሉ ዳያስፖራዎችም አብዛኞቹ ሴቶች ዳያስፖራዎች እንዲታቀቡ መፍትሄ መፈለግ ግድ ይላል። አለበለዛ ዳያስፖራው በሰልፍ እየወጣ ስለ ፍትህ መከበር የሚጮኸው ነጋ ጠባ በተግባር አይተረጎምም።

 2. በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ የሆኑት ጄኔራል አሜሪካንን ጥገኝነት ጠየቁ
  November 21, 2020

  የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

  በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት ወታደራዊ አታሼ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ፍስሀ ኪዳኔ ከኃላፊነት ተነስተዋል።

  ጀኔራሉ ከሐላፊነት እንደተነሱ በሀገር መከላከያ ሚኒስትር በኩል ደብዳቤ እንደደረሳቸው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውም ታውቋል።ሜጀር ጄኔራሉ ፍስሀ ኪዳኔ በሐገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ እዝ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።

  የምዕራብ እዝ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት በሰሜን ጎንደር ጭልጋና መተማ አካባቢ ከሱር ኮንስትራክሽን ጋር በመተባበር የቅማንትና የአማራ ህዝቦችን ግጭቶች በበላይነት መርተዋል።

  ሜጀር ጀኔራል ፍስሀ ኪዳኔ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ከመምራት በተጨማሪ በወቅቱ በቦታው የተሰማራውን የመከላከያ ሰራዊት ከተልዕኮው ውጭ በመስጠት ላስፈጸሙት የሰባዊ መብት ጥሰቶች በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል።

  አሁንም ከተሰጣቸው ሐገራዊ ተልዕኮ በማፈንገጥ በተለያዩ አለም ሀገራት ከሚገኙ ኤምባሲዎች ጋር በሚስጢር በመገናኘት የወንጀለኛው ትህነግን ተልዕኮ ሲያስፈጽሙ መቆየታቸው ታውቃል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የዓለም ሀገራት የኤምባሲ አመራር ሆነው በሃላፊነት የሚሰሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ሲሉ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚነስትር ከፍተኛ ባለስልጣን ገልፀዋል::
  ­

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.