በአዲስ አበባ ባለቤት ያልተገኘላቸው ህንጻዎች 100 መድረሳቸውን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

በአዲስ አበባ ባለቤት ያልተገኘላቸው ህንጻዎች 100 መድረሳቸውን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ

1 min read
1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የከተማዋ ወጣቶች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፣ በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች፣ ታጥረው የሚገኙ መሬቶች እና የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ እየተደረገ ባለው ዳሰሳ እስካሁን 100 ህንጻዎች ባለቤት አልተገኘላቸውም።
ከዚህም በተጨማሪ ታጥሮ የተቀመጠ ከ1 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ባለቤት ሳይገኝለት ቀርቷል።
በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች ላይም ማጣራት እየተደረገ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የከተማዋ ወጣቶች በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንደሚደግፉ እና ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።
በእዮብ ሞገስ
EBC

1 Comment

  1. እንደሚመስለኝ ከብዛቱ ብዛት ያስቀመጡበት የጠፋቸዉ የትግሬዎች ህንጻ መሰለኝ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.