ህወሓቶች ድግስ ላይ የነበረው ስካርና ዳንኪራ (በድብቅ የተቀረፀ) | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

ህወሓቶች ድግስ ላይ የነበረው ስካርና ዳንኪራ (በድብቅ የተቀረፀ)

1 min read
5

ህዳር 24-25/2012 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ “የፌደራሊስቶች ግንባር” በሚል የተሰባሰቡት ሰዎች የተናገሩትን በቴሌቭዥን ተመልክተናል። ነገር ግን ብዙዎቻችን ከስብሰባው በኋላ በአንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ የነበረውን የህወሓቶች ድግስ፣ የፌደራሊስቶች ስካርና ጭፈራን በቴሌቭዥን የማየት ዕድል አልነበረንም። ህወሓቶች ከደሃ ህዝብ በዘረፉት ገንዘብ በቅንጡ ሆቴል ውስጥ ድል ያለ ድግስ በመደገስ ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ያመጧቸውን ተላላኪዎች “ብሉልኝ ጠጡልኝ” እያሉ አስተናግደዋል። በመጨረሻም እንደተለመደው የትግሪኛ ሙዚቃ ተከፍቷል። በድግሱ ላይ ያታደሙት ሆድ-አደሮች በስካር እየተወላገዱ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ቪዲዮን እንሆ ብለናል።
ስዩም ተሾመ