‹‹ህወሓት ለሦስተኛ ጊዜ የትግራይ ህዝቡን የጦር ቀጠና አደረጎት! የወያኔ ዓሳራ ግመሎች የጨለማ ጉዞ!›› ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም | ዘ-ሐበሻ Latest Ethiopian News and Point of View 24/7

‹‹ህወሓት ለሦስተኛ ጊዜ የትግራይ ህዝቡን የጦር ቀጠና አደረጎት! የወያኔ ዓሳራ ግመሎች የጨለማ ጉዞ!›› ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

1 min read
2

የኢትዮጵያ ዓየር ኃይል ለትግራይ ህዝብ በሂሊኮፕተር የሠላም ጥሪ ወረቀትና የዩቲዩብ ፍላሾች ቢበትን ህዝቡ ዘንድ መረጃው ደርሶ ይረጋጋል!!!

ሌ/ል ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳዔ፣ የመከላከያ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም የነበሩ፣ ሌ/ል ጄኔራል አቶ ስዬ አብርሃ የመከላከያ ሚኒስቴር የነበሩ፣ ሌ/ል ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት፣ የዓየር ኃይል አዛዢ፣ በሃገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ ካህዲዎች በብልፅግና ፓርቲ መግለጫ ውስጥ ስማቸው አለመካተታቸው የኢትዮጵያን ህዝብ አሳዝኖል፡፡ እነዚህ ከሃዲዎች ላለፉት አርባ ስድስት አመታት የሃገር ክህደት በመፈፀም፣ ጦርነት በመጫር ህዝብ በመጨረስ፣ የሃገር ደህንነትን ለውጭ አሳልፎ በመሸጥ፣ ዛሬም ጦርነቱን አስለኩሰው ከመቐለ መኮብለላቸው ይነገራል፡፡ ከመቐለ ወዴት ኮበለሉ? እንዴት ሊወጡ ቻሉ የማይታመን ሲሆን እዛው መቐለ ትግራይ እንዳሉ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች አበጋዞች መንግሥት TPLF WARLORDS STATE የወያኔ ፋሽስታዊ አስተዳደር በኢትዮጵያ የትግራይ ህዝብ ላይ በመጫን ኢትዮጵያን ዳግም መግዛት እንችላለን በሚል የፖለቲካ ሴራ በማማከርና ለመተግበር የሰሜን እዝ  መከላከያ ሠራዊት ኃይልን በግፍ በመረሸን፣ ከባድ መሣሪያዎች በመዝረፍ፣ የባንኮች ገንዘብ  በመዝረፍ፣ በማይክድራ የአማራ ተወላጆች ላይ ጆኖሳይድ በመፈፀምና አጠቃላይ ጦርነት ጭረው የሃገር ክህደት ፈፅመዋል፡፡

ሌ/ል ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳዔ፣ ሌ/ል ጄኔራል አቶ ስዬ አብርሃ፣ ሌ/ል ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት፣ በስልጣን ዘመናቸው በባንክ ስርኣቱ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ባንኮቹን ለአንድ ዘር እንዲያበድሩ በማስገደድ አዘርፈዋል፣ ሃገሪቱን ጂኦ ፖለቲካል ስርዓት በዘር በመሸንሸን ድንበርና ወሰን በዘር በማካለል ከፋፍለው ለመግዛት የዘር ፌዴራሊዝምን በመስበክ ብዙ ህዝብ እንዲሞት፣ እንዲታሰርና እንዲሰደድ አድርገዋል፡፡ ‹‹የህገ-መንግስቱ›› አይነኬ ነው! እያሉ በማቅራራት ብዙ ግፍ ፈፅመዋል፡፡ ያለ ሳይንሳዊ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ትምህርት የጀነራል መኮንን ማዕረግ  ሌተናል ጄኔራል ማዕረግ በሙስና ስለተሠጣቸው በከንቱ ሲሸልሉና ሲያቅራሩ ታይተዋል፣ በዚህ የማህም ስራቸው ነው በዚህ ጦርነት ወያኔ ያሸንፋል ብለው በማማከር የትግራይን ህዝብ ለጦርነት የዳረጉት በዚህ የተሳሳተ አማካሪነታቸው  በፍርድ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡

 • የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)ከ1975 እስከ ግንቦት 1991 እኤአ 17 አመታት የሽምቅ ውጊያ አካደዋል፡፡ ከደደቢት በርሃ አስር ሆነው ሰባት ዲሚትፎርና ነጭ ቃታ ቤልጅግ  ታጥቀው፣ ምሽግ ቆፍረው፣በደፈጣ ውጊያ፣ በቆረጣ ስልት፣ አንዱን ለአስር፣ አስሩን ለአንድ በጦርነት ገጥመው ፣ ስልሳ ሽህ የትግራይ ልጆች ተሠውተውና ብዙ ሽህ የአካል ጉዳተኞች ሆነው ደርግን አሸንፈው በድል አድራጊነት ሥልጣን ያዙ፡፡
 • የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኢህአዴግ አገዛዝ ከ1992 እስከ ግንቦት 2018 እኤአ 27 ዓመታት ኢትዮጵያን በአምስት የምርጫ ዘመናት አስተዳድረዋል፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ ኢትዮጵያንና ኤርትራን በመርህ አልባ ግንኙነት አለመግባባት በተፈጠረ የበድማ  ጦርነት መቶ ሽህ ወታደሮች እንዲያልቁ  ሆኖል፡፡
 • የብልፅግና ፓርቲ ከ2018 እስከ 2021 እኤአ ለሦስት አመታት ኢትዮጵያን በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ በምርጫ ዶክተር ዐብይ አህመድን መሪ አድርጎ ከመረጠ ማግስት ህወሓት በማኩረፍ መቐለ መሸገ፡፡ ህወሓት በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ አልደመርም ብሎ  ዳግም ሥልጣን ላይ ላይ ለማውጣት የፖለቲካ ሴራ ውስጥ በመግባት በትግራይ ውስጥ የሚገኘውን የሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮችን በትግርኛ ተናጋሪዎች ሌሎችን በተኙበት በማሳረድ በተለይ የአማራ ተወላጆችን በመግደል ታሪክ ይቅር የማይለው የሃገር ክህደት ፈፅመዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በትግራይና በኢትዮጵያ ጦርነት ተጀመረ፡፡ በሽዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ህይወታቸውን አጡ፣ ንብረትና ኃብት በመውደም ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን የዓለም የጦርነት ስልት በረቀቀ መንገድ የሚከወነው በዓየር ኃይል ተዋጊ የጦር አይሮፕላኖችና በሰው አልባ ድሮኖች በጂፒኤስ አስተማማኝ ኢላማ መችነት ወያኔ የዘረፋቸው ከባድ መሣሪያዎች ታንኮች፣ ሚሳኤሎች፣ ሞርታሎች፣ ስታሊን ኦርጋኖች፣ የጦር መጋዘኖች ወዘተ በመውደም ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘመኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂ  ዘመን ነው፣ መረጃ ያለው አሸናፊ ነው፣ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ የሌላት ወያኔ አሸናፊ ልትሆን አትችልምና በሠላም እጅ ሠጥቶ ለፍርድ መቅረብ አማራጭ የለውም፡፡  ወያኔ በድሮ ጭንቅላቱ ከደደቢት በርሃ በሽምቅ ውጊያ ዳግም ሥልጣን ለመያዝ ያስባል ዘመኑ ተቀይሮል በሰው አልባ ድሮዎኖች ከመቀጥቀጥና ማለቅ አያልፍምና ህዝብ አታስጨርሱ እንላለን፡፡
 • ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሠሩት መኖሪያ ፎቅ ከሠላሳ እስከ አርባ ሚሊዮን ብር ይገመታል፡፡ የወያኔ መንግሥት አምስት መቶ ካሬ ሜትር መሬት በነፃ ሰጥቶቸው ነበር፣ ቤቱ ሃያ ሽህ ዶላር እንዳከራዩት ታውቆል፡፡
 • ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ እንዳሉት ‹‹ከሁለት ዓመት በኃላ በምርጫ የሚፈልገውን መምረጥ እንደሚችል ይተማመናል፡፡ ስለዚህ ቤት ማቃጠል፣ ሰው መግደልና ኢንዱስትሪ ማፍረስ ይቆማል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህ ሂደት በራሱ ወንጀልንና ትክክለኛ የፖለቲካ ጥያቄን ይለያል ብዬ አስባለሁ፡፡ በወንጀል መንገድ እሄዳለሁ በሚሉ ላይ የፀጥታ ኃይሉ ያለምንም ማቅማማት ዕርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ ላለፉት 27 ዓመታት የቆየ ህዝብ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት መታገስ አይችልም ብዬ አላስብም፡፡›› በማለት ለሪፖርተር ጋዜጣ የካቲት 4 ቀን 2010ዓ/ም ሠራዊቱን እንዲገድል ጥሪ አስተላልፈዋል፣ ለሠራዊቱ የሰው ነፍስ አትግደል፣ አስለቃሽ ጢስ ተጠቀም!፣ ወደ ሰማይ ተኩስ!፣ ካልሆነ ከእግሩ በታች ተኩስ፣ ብለው አልመከሩም ነበር፡፡
 • ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሠሩት መኖሪያ ፎቅ ከሠላሳ እስከ አርባ ሚሊዮን ብር ይገመታል፡፡ የወያኔ መንግሥት አምስት መቶ ካሬ ሜትር መሬት በነፃ ሰጥቶቸው ነበር፣ ቤቱ ሃያ ሽህ ዶላር እንዳከራዩት ታውቆል፡፡
 • ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ የራያ ቢራ ፋብሪካ ሲያቆቁሙ ከንግድ ባንክ 970 ሚሊዩን ብር ብድር መውሰዳቸውና ራያ ቢራን ለቢጂአይ ዓየር በዓየር መሸጣቸው ይታወቃል፡፡ አሁን ደሞ ለቢጂአይ ኢትዮጵያ አዋሽ ባንክ 750 ሚሊዮን ብር ብድር እንዲሰጠው በማመቻቸት ቢጂአይ በራያ ቢራ ውስጥ ካለው የ42 በመቶ ድርሻው በተጨማሪ፣ቀሪውን አክሲዬኖች ለመግዛት ከ5 ቢሊዮን ብር ለባለአክሲዮኖቹ ለመክፈል የዓየር በዓየር ንግድ ጻድቃን የባንኩን ብድር በማመቻቸት በሙስና ተነክረው ነበር፡፡
 • /ል ጄኔራል አቶ ስዬ አብርሃ፣ የህወሓት መስራች፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የፖሊት ቢሮ አባል የነበሩ ሲሆን ቀጥሎም የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር የነበሩ፣ የኢፈርት ዋና ሥራ አስኪያጅና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ አባል በነበሩበት ጊዜ አየር መንገዱን ከኤርትራ አየር መንገድ ጋር ለማቀላቀል ከፍተኛ የሙስና ሴራ የፈፀሙ ከሃዲ እንደነበሩ ታሪካቸው ይመሠክራል፡፡
 • /ል ጄኔራል አቶ ስዬ አብርሃ፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን፣ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በደርግ አገዛዝ ስርዓት የተወረሱ መንግስታዊ ድርጅቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘወወር በ1994 ዓ/ም በአዋጅ የተቆቆመ ድርጅት ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ (ስዬ አብርሃ ወንድም) 05/19/99እኤአ ለእህታቸው ባል አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በአምስት ሚሊዩን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ሽህ ብር (5,273,000 ) ሸጡላቸው፡፡ በኢትዩጰያ የመጀመሪያ የሆነውን ጥንታዊ ሆቴል የሃገር ሃብትና ቅርስ ሆኖ ሳለ በህወሃት/ኢህአዴግ ታሪክን የማጥፋት የቆየ ደመኝነት ለዘመዳቸው እንዲሸጥ አስደርገው ነበር፡፡

አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም፣ በመለስ ዜናዊ ውርስና ቅርስ የሆነው የሙስና ፋብሪካ ምርት አምራች  ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ (ስዬ አብርሃ ወንድም) 05/19/99እኤአ ለእህታቸው ባል አቶ ፍፁም ዘአቡ አስግዶም፣ከሸጡላቸው ውስጥ፡- {1}እቴጌ ጣይቱ ሆቴል በአምስት ሚሊዩን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ሽህ ብር (5,273,000 ) ሸጡላቸው፡፡  {2}የጉለሌ የሳሙና ፋብሪካ በ12/23/1996 አ/ም በ22,370,000 (በሃያ ሁለት ሚሊዩን ሦስት መቶ ሰባ ሽህ ብር) ገዝተዋል፡፡{3}ሐረር ፕሪንቲንግ ኢንተርፕራይዝ ማተሚያ ቤትን በ1,164,000 (አንድ ሚሊዩን አንድ መቶ ስድሳ አራት ብር)  በ10/18/1995 ዓ/ም ገዝተዋል፡፡ በጥናት እንደተረጋገጠው በኢትዮጵያ አይን ያወጣ ሙስና ሌብነት የተጀመረው በመለስ ዜናዊ ፊት አውራሪነት በህወኃት፣ በብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴግ፣ ወዘተ  ዘመን አገዛዝ ሲሆን፣ይህውም  በ1994 ዓ/ም አዋጅ መነሻነት ከመንግሥታዊው ዘርፍ ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘወወር በተቆቆመው ድርጅት ‹‹የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ›› ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ አማካኝነት የህዝብ ሃብት የተሸጠበት ጊዜ ነበር፡፡ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን፣የመንግሥት እርሻዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ሆቴሎች ወዘተ ተሸጡ፣ የከተማ መሬት በሊዝ ስም ተሸጡ፣ የገጠር መሬት ለኢንቨስተሮች ተሸጡ!!! ብሎም የትግራይን ክልል ድንበር ማስፋት ተያያዙት!!! የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለማጣላት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡  በህግ ስም! በአዋጅ  ሰም! ዘረፋ ህጋዊነት እንዲያገኝ ተደረገ፡፡ ዛሬ የምናያቸው ሃብታሞች ትላንት ቁምጣ አድርገው፣ ሸበጥ ተጫምተው፣ ቦንብ ታጥቀው፣ ክላሽ ደግነው በጉልበት ያስገበሩን ወራሪዎች የሃገሩን ኃብት ገና ዘርፍው አልጠገቡም!!! ቪላ ቤት ሰሩ አልጠገቡም፣ ፎቅ ገነቡ አልጠገቡም! ሚሊዮነር ሆኑ አልጠገቡም! ዛሬ የሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊታችንን በመረሸን ከባድ መሳሪዎች ታንኮች፣ ሚሳኤል፣ ላውንቸሮች፣ ወዘተ በመዝረፍ መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጀው ይገኛሉ፡፡

 • ሌተናል ጄኔራል ስዬ አብርሃ፣ ከአሜሪካ መጥተው በመቀሌ ከተማ ከ40 ዓመታት በፊት በቀይ ሽብር ለተገደለው ወንድማቸው መታወሻ ትምህርት ቤት አሰርተው ማስመረቃቸው ይታወቃል፡፡ በትግራይ የቀይ ሽብር ሰማዕታት በሙሉ መታሰቢያ ቢሆን በተሸለ ነበር!!! የወያኔ አጋዚ ጦር የገደላቸው ለጋ ወጣት ሠመዓታት ደም በከንቱ ፈሶ እንደማይቀር የወላጆች እንባ እንደሚታበስ ዘንግተዋል፡፡ በወያኔ መንግሥት ለተገደሉ  ሠማዕታት መታሠቢያ ስንት መታሠቢያ ይቆም ይሆን!! ወያኔ ከደርግ ሥርዓት የተማረው ግድያ ነው፣ የቀይ ሽብር ወንጀለኞች በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር የተደበቁ ሁሉ ለፍርድ ቀርበዋል፡፡ የወያኔ ነጭ ሽብር ወንጀለኞች እጣ ፈንታቸው ይሄው ነው፡፡ በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን እያንዳንዶ የግድያ ማስረጃ ተሰድሮ ቀን ትጠብቃለች፡፡ በወያኔ  ሥርዓት የተገደሉ የጅምላ ግድያ ድብቅ ቦታዎች በትግራይ፣ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሞ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ክልል ወዘተ ተቆፍሮ የሚወጣበት ጊዜ ደርሶል!!!
 • ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔና፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ሁሌም የወያኔ ነፍስ አባት በመሆን በቀውጢ ጊዜ ወያኔን የሚታደጉ ‹‹ህገ-መንግሥቱን የናደውን ወያኔ ሥራ እያዩ ‹‹ህገ-መንግሥት ይከበር!!!›› በሙስናና በኮንትሮባንድ ሥራ ዋነኛ ተካፋይና የሥርዓቱ ተጠቃሚ በመሆናቸው የህዝባዊውን እንቢተኛነትና ተጋድሎ በመኮነን የሰው ነፍስ ከሚጥፉ አጋዚ ጦር ሠራዊት ጥይት በላይ በምላሳቸው የሚናደፉና በብዕራቸው የሚወጉ ናቸው፡፡ ‹‹ምላስ አጥንት የላትም፣ አጥንት ግን ትሰብራለች!!!› የህወሓት መንግሥት ከወደቀ ኢትዮጵያ ትበታተናለች›› ‹‹ኢንተርሃሞይ! የዘር ፍጅት ይከሠታል!!›› ይሉናል፡፡ ‹‹የእርስ በእርስ ጦርነትና የሃይማኖት ጦርነት ይኖራል›ይሉናል፡፡ ህዝቡን አርፋችሁ ተገዙ፣ መሬታችሁን ስጡ፣ ሃብታችሁን ተዘረፉ፣እያሉ በማማከር አድርባይ ምሁራዊ ምክራቸውን በመለገስ ይታወቃሉ፡፡
 • ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሠሩት መኖሪያ ፎቅ ከሠላሳ እስከ አርባ ሚሊዮን ብር ይገመታል፡፡ የወያኔ መንግሥት አምስት መቶ ካሬ ሜትር መሬት በነፃ ሰጥቶቸው ነበር፣ ቤቱ አስር ሽህ ዶላር እንዳከራዩት ታውቆል፡፡
 • ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ የመለስ ዜናዊ መንግሥት ሰባት ወታደራዊ ጀነራሎች፣ 240 ኮነሬሎችና 500 ከፍተኛ ኦፊሰሮች ሻንበልና ሻለቃ ማእረግ ያላቸው ባባረረ ጊዜ ነበር ስልጣናቸውን ያጡት፡፡ መለስ ከትቢያ አንስተናችሁ ጀነራል አደረግናችሁ፣ ዳግም ወደ ትቢያችሁ እንመልሳችሆለን ብሎ  አበበ የተከራዩትን ቤትና ፣ መኪናቸውን ተነጥቀው፣ የቆረጡላቸውን ደሞዝ አሳጥተው  ለማኝ አደረጎቸው፡፡

የህወሓት/ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ የጦርነት  አዋጅ አውጆል፡፡ ወያኔ የተነጠቀውን በትረ ሥልጣኑን ለማስጠበቅ ቆርጦ ተነስቶል፡፡ የኢትዮጵያ ‹‹ህገ-መንግሥት›› ተጥሶል፣ የክልል መንግሥቶች መብትና ሥልጣን ተሸሮል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች  መንግሥት የሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊትን በግፍ በመረሸን የሀገር ክህደት ፈፅመዋል፡፡ ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣  የወያኔ መንግሥት የፖለቲካ ቤተ ርስት መናጆዎች!!! የወያኔ ፖለቲካ አማካሪዎች ሲሆኑ፣ ሁሌ እንደመስቀል ወፍ ብቅ እያሉ የወያኔ በትረ-ሥልጣን ምሶሶ በሚንገዳገድበት ወቅት ነው፡፡ የፖለቲካ ትንተና ላይ የተመሠረተ ፕሮፓጋንዳ፣ ወያኔ መንግሥት ከወደቀ የዘር ፍጅት ይከተላል!፣ አገር ይገነጣጠላል!፣ ኢንተር ሃሞይ ይከሰታል!! መሬት ይንቀጠቀጣል!፣  ህገ መንግስቱ ይቀልጣል!!!. እያሉ የሚተውኑ እንደ መስቀል ወፍ የሚታዩ ተዋናይ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ ሰለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ፕራይቨታይዜሽን ዘረፋ ተናግረው አያውቁም፣ ስለወያኔ ኢፈርት፣ ሜቴክ፣ ወጋጋን ባንክ፣ ለገደንቢና ኢዛና ወርቅ፣ ስለ ሙስናና ኮንትሮባንድ ንግድ፣ የከተማና ገጠር መሬት ቅርምት ወዘተ ተናግረው አያውቁም፡፡  የወያኔ መንግሥት የፖለቲካ ቤተ ሥልጣን ነገረፈጆች ሲሆኑ የወያኔ ፖለቲካ ሩጫ በፍጥነት ጦርነት ያሳወጁት ወሳኚ መሃል ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ በወያኔ ስርዓት ጋሻ ጃግሬነትና፣ የነፍስ አባትነት፣ጥብቅናቸው ይታወቃሉ፡፡

እነዚህ ዓሳራ ግመሎች ለህዝብ አሳቢ በመምሰልና ወያኔን የተቃወሙ በማስመሰል፣ የህዝብ አስተሳሰብን ለመበረዝና ለመከለስ ከወያኔ ጎዳ ተመካክረው አደባባይ አዲስ አጀንዳ በማንገብ የሚወጡ፣ የወያኔ የፖለቲካ መናጆዎች በመሆን የህወሓት መንግሥት እንዳይወድቅ የሚያደርጉ የዓሳራ ግመሎች ናቸው፡፡ እነሱ በፈለጉ ጊዜ ሁሉ መገናኛ ብዙሃኖች ይበረገዱላቸዋል፣ ጋዜጦች፣ቴሌቪዝኖች፣ ሮዲዮኖች፣ መፅሄቶች ፣ድረ-ገፆች ወዘተ ሁሉ ለዓሳራ ግመሎቹ፣ ሌተናል ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት፣ ሌተናል ጄኔራል ጻድቃን ገብረ ትንሳዔና፣ አቶ ስዬ አብርሃና፣ መሰሎች ስብከት ‹‹ህገ-መንግሥት ይከበር!!!›› ሠላሳ ሚሊዮን ወጣቶች ሥራ ፈት በሆኑባት ሃገር ወጣቶችን ችግራችሁ ምንድነው ብሎ መጠየቅ የምሁራን ሥራ ነበር!!! ህዝቡ ያመፀው በወያኔ መሬቱን በመነጠቁ፣ በወያኔ ሃብቱን በመዘረፉ፣ በወያኔ መልካም አስተዳደር እጦት፣ በወያኔ የሙስናና ኮንትሮባንድ ንግዳችሁ ይቁም ነው የሚላችሁ፡፡ ሰው ይውደድህ፣ ድንጋይ ይጫንህ!!!›› አበው  የሚሉት ለዚህ ነው፣ የተጠላችሁ ሰዎች ናችሁ፡፡

 

ሌ/ል ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳዔ፣ ሌ/ል ጄኔራል አቶ ስዬ አብርሃ፣ ሌ/ል ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት፣ በፍርድ ይጠየቁ!!!

 

ምንጭ/Source:

Privatization and Public enterprises supervising agency and own competition.

 

2 Comments

 1. Yes sir, you are right!
  But I really do not understand why we have never been and we are not still courageous enough to challenge ourselves with a critical question of who we are , What we are, what we did as citizens of freedom-loving , and why we keep falling apart whenever we face a critical moment of democratic change? Why we disgracefully failed in our more than two years endeavor to stop the nonsensical tragedy of the politics of ethnocentrism? Who gave those evil-driven politicians of ethnocentrism a great chance to get strength and cause unbearably painful consequence? What did we do except making terribly empty rhetoric about the untold sufferings the innocent people have been going and are going through? Is it not deeply nonsensical not to ask our own conscience about our repeatedly nonsensical failures to make any meaningful difference for about three decades as far as a true democratic change is concerned? Who critically challenged and advised the prime minister who has been busy with the making of many acts of cheap popularity including beatifying his parks and streets when millions and millions of innocent people had to go through untold sufferings? Who seriously challenged him about what he was doing whereas TPLF was doing very clear things that could put the country in a very danger we are witnessing now? Which opposition political party tried its best to reverse the very political madness we are witnessing now? Is it not terribly disturbing why and how we became victims of just keep blaming those whose deadly political agenda is crystal clear for so long, but not willing and able to see our own nonsensical failures to meaningfully challenge the very tough situation we found ourselves in? Is it not at least morally stupid to keep blaming those already known brutal politicians of TPLF/EPRDF/Prosperity instead of helping the people to rise up for a true democratic transition that should involve all genuinely concerned stake holders in order to get rid of the very deadly ethnocentric political system of TPLF/EPRDF/Prosperity ? I strongly argue that yes, the inner circle of TPLF must be forced either to come to the negotiation table by admitting its own politically motivated crime or face serious consequences. I equally and strongly argue that politicians of Prosperity, the “new brand” of EPRDF must be forced by the people either to make a fundamental democratic transition possible by abolishing the document (constitution of mutual exclusiveness and destruction) and the killing machine of ethnic federalism, and paving the way for a stable, peaceful, equal opportunity and shared prosperity way of life or to face serious consequences of their own making. I strongly believe and argue that there will never be a real sense of democratic transition and the building of a democratic system with the leadership of those EPRDF/Prosperity politicians whose hands are directly or indirectly stained with the very blood of innocent citizens for almost three decades! Never and never! I wish it could be the case. But the very nature and behavior of this group of politicians have been tested by a very hard reality on the ground. With the exception of those who committed serious politically motivated crimes, all members can be parts of the process and beneficiaries of the outcome. It must be, however, clear that we all desperately need to hold ourselves responsible and accountable for what has gone wrong and what is going wrong as the very political attitude and culture of simply blaming others including those evil-driven politicians of TPLF/EPRDF/Prosperity will never bring any meaningful and long-lasting solution.

 2. Aba Dulla Gemeda , Aster Mamo , Muktar Kedir who are rumored to have Alemayehu Atomssa killed to cover up their looting need to be at least be questioned , along with the other mastermind of Alemayehu Atomssa’s murder Azeb Mesfin herself.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.